Search

Saturday, April 18, 2015

በደቡብ አፍሪካ በደረሰብን አሳዛኘኝ በደል ሦስት ሃሳቦች አሉኝ ! (አሌክስ አብርሃም) MUST READ AND SHARE SHARE SHARE

በደቡብ አፍሪካ በደረሰብን አሳዛኘኝ በደል ሦስት ሃሳቦች አሉኝ !
(አሌክስ አብርሃም)

1ኛ . የአገራችን መንግስት ጉዳዩን ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ ሌላ ከራሱ ህልውናው ጋር የተያያዘ ጉዳይ አድርጎ ሳይመለከተው የደረሰብንን በደል በአደባባይ ወጥተን እንቃወም ዘንድ ፈቃድ ይስጠን ! ሚሊየን ሁነን እንውጣ መላው አለም ወገኖቻችን ሲጠቁ በየጓዳችን ቁጭ ብለን ግጥም በመፃፍና ‹‹እግዜር የሁናቸው›› በማለት ብቻ ዝም የምንል ህዝቦች አለመሆናችንን ይመለከት ዘንድ የተፈረፀመብንም ወንጀል እጅግ ዘግናኝ እንደሆነ ተረድቶ ሃዘናችንን ይካፈል ዘንድ ሁላችንም ጥቁር ለብሰን አደባባይ እንድንወጣ ጩኸታችንን የምንጮህበት አገር ይፍቀድልን ! መንግስት ፈቃጅe ይሁን ብቻ ሳይሆን የተቃውሞ ሰልፉንም ራሱ ይጥራ !! የአፍሪካ ህብረት መዲና እንደመሆናችን ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ሂደን ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር መስቀል አደባባይ ፊታችን ቁመው መላውን አፍሪካ ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ ጥየቄ እናቅርብ !
2ኛ. ሁላችንም አንድ ጥያቄ እንጠይቅ ‹‹ጃኮብ ዙማ ››ስልጣን ይልቀቁ !! በመላው አለም ያለን ኢትዮጲያዊያን ይህን ጥያቄ እናንሳ …ይህ የዋህ ሃሳብ ይመስላል ግን እመኑኝ ሁሉም አፍሪካዊ መሪ እንደነብሱ የሚወደው ነገር ቢኖር ስልጣኑን ነው ! ይህ ጥቃት ‹‹የስልጣን ልቀቁ ›› ጥያቄ እንደሚያመጣ የተረዳ ማንም አፍሪካዊ መሪ በየአገሩ የሚኖሩ ዜጎቻችንን መጠበቅ ስልጣኑን መጠበቅ መሆኑ የሚገባው በዚህ ቋንቋ ብቻ ነው !!
3ኛ. ፀያፍ ስድቦችን እናቀም … በተለይ ከቅኝ ግዛት ጋር በተያያዘ መላው አፍሪካ የሚያመው ቁስል ያለበት ነው ! ለደቡብ አፍሪካዊያን ነፍሰ ገዳዮች የምንሰነዝረው ስድብ በሌሎችም ወንድምና እህቶቻችን ላይ የሚያሳድረው ጠባሳ መጥፎ ነው ! እዛም ዜጎች አሉን ! የዛሬዎቹ ነብሰ ገዳዮች አባቶቻቸው እንደነሱ አልነበሩም …እኛም አባቶቻችን በቅኝ ገግዛት ወንድሞቻቸውን አልሰደቡም ይልቅ ለነፃነታቸው ከጎናቸው ቆሙ እንጅ !
እንደቀደሙት ጩኸቶች ተድበስብሶ እንዳይቀር በሉ አንድ ጠብ የሚል ነገር አድርገን ተቃውሟችንን በአካል ማሰማት እነንችል ዘንድ ሃሳብ አምጡ ! ሌላስ ምን እናድርግ …ፎቶ ስድብ ባትለጥፉ ደስ ይለኛል ሃሳብ ብቻ አምጡ …ምን እናድርግ …

No comments:

Post a Comment