Search

Friday, April 17, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በአዲስ አበባ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትን በኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ አነጋገሩ

ሚያዚያ 9 2007
kelela
አሁን ከአዲስ አበባ በደረሰን ዜና መሰረት
የሰማያዊ ፓርቲ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካውያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድብደባ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ለደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትን ቅሬታቸውን ገለጹ::
ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካ ነጻነት እና ለጥቁር ህዝቦች በመላ ያደረገችውን ወለታ አስታውሶ በተለይ ከደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያውያኖች ውለታ ምላሹ ይህ መሆን እንደማይገባው አስረግጠው ለባለስልጣናቱ እስታውቀዋል::
የቀድሞው ደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ማንዴላ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ይህንን የደቡብ አፍሪካውያን ተግባር ከማውገዛቸውም በላይ በ24 ሰዓት ውስት ፈጣን እርምጃ ወስደው ችግሩን በሰላም ሊፈቱት ይችሉ እንደነበር አስታውሰዋቸዋል::
ማንዴላ ለጥቁር ህዝብ አንድነት ወንድማማችነት እና ነጻነት ያደረጉት የረጅም ግዜ ትግል እንዲህ በአጭሩ ተፈረካክሶ ሲወድቅ በህይወታቸው እያሉ ማየት የማይፈልጉት እንደነበር ለባለስልጣናቱ አስታውሰዋቸው በአሁን ወቅት ስልጣን ላይ ያለውን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ለችግሩ አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ እና ኢትዮጵያውያን ዜጎች በአስቸኳይ ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር  እና ሌሎች በሀገሪቱ የሚኖሩትን ስደተኖች ደህንነት ማስጠበቅ እንዲችሉ  በአዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ጥያቄ አቅርበዋል::
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ሜሮን አየለ website

No comments:

Post a Comment