Search

Wednesday, April 15, 2015

በወር አበባ ዑደት እርግዝናን መከላከል (በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት) MUST READ


Dr Bethel ዶ/ር ቤቴል ደረጄ's photo.የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች ተፈጥሮአዊ እና ዘመናዊ በመባል ይከፈላሉ። ተፈጥሮአዊ ከሚባሉተ ውስጥ የቀን መቁጠሪያን በመጠቀም እርግዝና ሊፈጠር የሚችልበትን ቀኖች ላይ ከግንኙነት በመታቀብ መከላከል አንዱ ነው።
አጠቃቀሙ
1. ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የወር አበባ የመጣበትን ቀናት ማየት
2. ከቀኖች ውስጥ ቶሎ ከመጣበት ቀን ላይ 21 መቀነስ
3. ከቅናሹ የተገኘው ውጤት ግንኙነት የሚቆምበትን ቀን ያመለክታል
4. የማህጸን ጤናማ ፈሳሽ በዚህ ወቅት ይቀጥናል
5. ፈሳሹ መወፈር ከጀመረ ከ3 ቀን በኃላ ግንኙነት መጀመር ይቻላል
የመከላከል ብቃት
1. እንደየስው ጥንቃቄ ይለያያል (3-80%)
2. የወንድ አጋሮችንም ተባባሪነት ይጠይቃል
3. አንዳንድ የወንድ የዘር ፍሬዎች 5-7 ቀን የሴት አካል ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።
ምሳሌ
ያለፉት 6 ወራት የወር አበባ የመጣበት ቀናት፡ 27ኛ፡28ኛ፡29ኛ፡27ኛ፡28ኛ፡29ኛ ቢሆን
ትንሹ 27 ስለሆነ 27-21= 6። የወር አበባ ከመጣ ከ6ኛ ቀን ጀምሮ ግንኙነት መቆም አለበት ማለት ነው።
ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት

1 comment:

  1. //ከፅሑፉ የተወሰደ//
    ምሳሌ
    ያለፉት 6 ወራት የወር አበባ የመጣበት ቀናት፡ 27ኛ፡28ኛ፡29ኛ፡27ኛ፡28ኛ፡29ኛ ቢሆን
    ትንሹ 27 ስለሆነ 27-21= 6።የወር አበባ ከመጣ ከ6ኛ ቀን ጀምሮ ግንኙነት መቆም አለበት ማለት ነው።
    ??????////ጥያቄ/////???????
    ግንኙነት መፈፀም የሚቻለው ከስንት ቀን በኋላ ነው?

    ReplyDelete