Search

Monday, April 13, 2015

በኳታር ታምና ያኮራችን እህት

 * ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “

የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት
* ታማኟ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዘለቀው በክብር ተሸለመች
* ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “
ታምና ያኮራችን እህት አንድነት ዘለቀው
ነቢዩ ሲራክ
አንድነት ዘለቀው ትባላለች ፣ አንድነት የ 32 ዓመት ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያዊት ስትሆን በኳታር ዶሀ ውስጥ በሚገኘውና ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ውስጥ በጽዳት ሥራ ተቀጥራ መስራት የጀመረችው እጎአ ከ2011 ጀምሮ ነው ።
Quatar
ታማኟና ታታሪዋ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዙሪያ ካሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በሰፊው እየተሰራጨ ያለው የሚያስደስት መረጃ ማረጋገጫ የተገኘው ግን ከትናንት በስቲያ ነበር ። አንድነት በመታጠቢያ ቤት የዘወትር የጽዳት ሥራዋን በመከወን ላይ ሳለች ሁለት በእንቁ ፈርጥ የተሸላለሙ የጋብቻ ቀለበቶች ታገኛለች ። የከበረ አልማዝ ያጌጡት ቀለበቶች ስለመሆናቸው ጠቋሚ ዋጋቸው የኳታር ገንዘብ QR470,000 US$129,000 ( አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ የአሜሪካ ዶላር) መሆኑ በቀለበቶቹ ላይ ተጽፏልና አውቃለች ። ታማኝ ናትና እንቁ አልማዙ አንድነትን አላጓጓትም ። እናም ሳታመነታ ወዲያውኑ ለምትሰራበት መስሪያ ቤት ኋላፊዎቿ ያገኘችውን የጣት ቀለበቶችን አስረከበች ። ስለ መልካም መግባሯና ታምኝነቷ የከብር ሽልማትን ተቀብላለች !
ሽልማቱን ያስረከቧት የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሲናገሩ አንድነት የቀለበቶች ዋጋ ስላለባቸው ለሁለት ደቂቃ ያህል በእጆችዋ ለማቆየት አለመፈለጓን በእግራሞት የገለጹት ኃላፊው ኢትዮጵያዊቷ አንድነት ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “I believe in my life that honesty is the best policy.” ማለቷን ጠቅሰዋል !
ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አስተዳደሩ የአንድነትን ታማኝ ሰራተኝነት በአደባባይ ከመመስከር አልፈው ጠቀም ያለ የገንዘብ ዳረንጎት እንዳደረጉላት ከኳታር ዶሃ የአንድነትን ታማኝነት የተሰጠውን ክብር አስመልክተው ባሰራጯቸው መረጃዎች አስታውቀዋል !
አንድነት ከዚህ ቀደምም ትሰራበት ከነበረው አል ሙክታር የጽዳት ኩባንያ Al Mukhtar Cleaning company በጽዳት ስራ ላይ እንዳለች ውድ እቃ አግኝታ ለአለቆቿ በማስረከብ ታማኝነትቷን ማረጋገጧ በመገናኛ ብዙሃኑ ተወስቷል … !
ደስ አይልም ? ኮራሁብሽ እቱ !
ከብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ!
ነቢዩ ሲራክ
source:zhabesha

No comments:

Post a Comment