Search

Wednesday, April 15, 2015

መካንነት (በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)


በሳይንሳዊ ትርጉ፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምንም አይነት የእርግዝና መከላከያ ሳይጠቀሙ ማርገዝ አለመቻል ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ በየሳምንቱ 3-4 የግብረ-ስጋ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል።
መካንነት በወንድም ሆነ በሴት ላይ ሊከሰት የሚችል ችግር ነው። 50% የሚሆነው በሴቶች ምክንያት፡ 35% በወንዶች ሲሆን ቀሪው 15% በሁለቱም ወይንም ባልታወቀ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ለዛሬ በሴቶች ላይ ሲከሰት ያለውን መንስኤና መፍትሄዎቻቸውን እናያለን።
የመካንነት መንስኤዎች
ሀ. የእንቁላል ማመንጨት ችግር
ለ. የማህጸን ቱቦ ችግር
ሐ. የማህጸን እና የማህጸን አፍ ችግር
ሀ. የእንቁላል ማመንጨት ችግር (40%)
በጤናማው የስነ-ተዋልዶ ሂደት ውስጥ የሚኖረው ወቅቱን የጠበቀ የእንቁላል ማመንጨት ስርአት ሲዛባ የሚፈጠር የችግር ዓይነት ነው።
የሚገለጡበት ሁኔታ ፡
1. ዑደቱን ያልጠበቀ የወር አበባ
2. እንቁላሉ ከተመረተ በኃላ ያለመለቀቅ
3. የእንቁላል ቁጥር መቀነስና የተያያዘ የምርት መቀነስ
ሕክምናው፡
1 እና 2 - በሆርሞን ማስተካከል የሚቻለውን መሞከር
3 - እንቁላል ከሌላ ሰው በመውሰድ የሚደረግ ሕክምና
ለ. የማህጸን ቱቦ ችግር (40%)
40 በመቶ የሚለው አሀዝ በዓለም አቀፍ ደርጃ ሲሆን በሀገራችን ደግሞ ከዚህም ይበልጣል። ብዙን ጊዜ በኢንፌክሽን ምክንያት በሚፈጠር ጠባሳ(ቲቢን ያጠቃልላል); ቀድሞ በተደረገ ኦፕሪሽን ምክንያት ቱቦው ሊደፈን ወይም ሊጎዳ ይችላል።
የተመረተውን እንቁላል ወደ ማህጸን እዳያልፍ ወይንም የወንድ የዘር ፍሬዎች ወደ እንቁላሎቹ እንዳያልፍ ያደርጋል። በመሆኑም እርግዝና አይፈጠርም።
ምርመራው ፤ የማህጸን ራጅ
መፍትሔዎች
1. የተደፈኑትን ቦታዎች ለይቶ ለመክፈት መሞከር (laparascopic surgery)
2. በጠባሳ ተይዞ ከሆነ በማስለቀቅ ማስተካከል
3. በኦፕሪሽን የማይስተካከል ከሆነ በልዩ ሕክምና ጽንሱን ማህጸን ውስጥ ማስቀመጥ።
ሐ. የማህጸን ችግር(Uterine factors)
በማህጸን ውስጥ ጤናማውን ቅርጽ ወይም አቀማመጥ ላይ ለውጥ የሚያመጡ
1. የአፈጣጠር ችግር
2. በማህጸን ውስጥ የሚያድጉ እጢዎች
3. የማህጸን ጠባሳ
የሚያመጣው ችግር ፡ ጽንስ እዳይፈጠር መሰናክል ይሆናሉ፡ ጽንሱ ቢፈጠር እንኳን እዳያድግ ያደርጉታል።
መፍትሔው፡ ኦፕሪሽን በማድረግ ማስተካከል
መ. የማህጸን አፍ ችግሮች
እጢዎች ወይንም የወንድ የዘር ፍሬን የሚያጠቁ ንጥረ-ነገሮችን በማምረት እንዲሞቱ ሊያደርጉ ይችላል።
መፍትሔው
1. አካላዊ የሆኑትን ኦፕሪሽን በማድረግ ማስተካከል
2. የወንድ የዘር ፍሬን የሚያጠቁ ንጥረ-ነገሮች ካሉ እነሱን አልፎ እንዲገባ የማድረግ ዘዴን መጠቀም(IUI)።
ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት

No comments:

Post a Comment