Search

Sunday, April 5, 2015

ሂድ አትበይ (ለሜሮን ጌትነት) ሂድ አትበይ እህትአለም....

ሂድ አትበይ
(ለሜሮን ጌትነት)
ሂድ አትበይ እህትአለም....
Abebe Kebede's photo.
መራቅ መልካም ብለሽ መሸሽ አትደግፊ:
አቅፎ ያባበለንን፣ አሻሽቶ ያስተኛንን፤ የእናት እጅ አትግፊ::
ቢሰማሽም ቁጭት ቢደርስብሽ ሀዘን:
ሰው ልቡ ተረስቶ በኪሱ ሲመዘን::
መደጋገፍ ቀርቶ የወደቀን ማቅናት:
ፍቅር ደብዛው ጠፍቶ ነግሶ መቀናናት:
ልብሽን ቢያደማም ይሄን ማየት መስማት::
ሂድ አትበይ እህትአለም፣ እራቅ መድሎን ሽሸው:
የችግሩን ወጀብ የእናት ቤትን አዘን፤ ርቀህ አሳልፈው::
የሰው ከክብር ማነስ የፍትእ መጓደል:
ተቃረንከኝ ተብሎ በአገር ሰው መበደል::
እግ እንኳን ተንቆ ቀሎ እንደገለባ: ታማኝ ሰው
ተገፍቶ ታምኖ ሲሾም ሌባ:: ልክነሽ ቁስል ነው
የልብ ምርዛት: ግን ምንይገኝ ብለሽ ከእናት ቤት
በመውጣት: ምሬት አለ እዚህ አዎ ልክ ብለሻል:
እመም አለ እዚ እውነት ተናግረሻል:
የራስ ለራስ ግፊያው ግፋ ያንገሸግሻል::
ቢሆንም.. ቢሆንም እህት አለም....
በወዳደቀ እሾህ ደጇ ቢበላሽም:
በክፋት ጢሳጢስ ውስጧ ቢጠለሽም:
ቆሸሸች ተብሎ ከእናት አይሸሽም::
ሀገር በሚሏት መስክ በትውልድ ማሳላይ:
ከአበቦቹ ልቆ አረም ፀድቆ ሲታይ::
ብር ከክብር በልጦ ህሊና ሲነገድ:
መታመን ተንቆ መወስለት ሲወደድ::
በሐሰት በኩል ነግቶ በእውነት በኩል ሲመሽ:
ብታዝኚ እውነት አለሽ::
ቢሆንም.. ቢሆንም እህት አለም.......
በወዳደቀ እሾህ ደጇ ቢበላሽም:
በክፋት ጢሳጢስ ውስጧ ቢጠለሽም:
ቆሽሻለች ተብሎ ከእናት አይሸሽም::
ከአስር ፎቆች ጀርባ ሺ ደሳሳ ጎጆ፡
የማጣት ጎተራ የአዘን ኮሮጆ።
በመቶ መንገድ ላይ ሚልየን እግረኝ፡
ጥቂቱ ሰርቶ አደር ብዙ በላተኛ።
ጎንበስ ያለ ደሀ አፍታም የረገጠው:
ያዘነች እናት ፊት እምባ ያጓጎጠው::
አዎ ልክ ብለሻል ያማል ይሄን ማየት:
ግን ይሻል ተብሎ የት ይኬዳል ከቤት::
ድህነት ደዌ ሆኖ ተዛማች በሽታ:
እጅ ተሰናዝሮ ሲያስነፍግ ሰላምታ::
እውነትን ታቅፎ አገር አገር ማለት:
እንደ እርኩሰት ቆጥሮ ሰው ሲዘብትበት:
አዎ እውነት ብለሻል ያማል ይሄን ማየት::
ቢሆንም ቢሆንም እህት አለም.......
በወዳደቀ እሾህ ደጇ ቢበላሽም:
በክፋት ጢሳጢስ ውስጧ ቢጠለሽም:
ቆሽሻለች ተብሎ ከእናት አይሸሽም::Abrham W. Mequanent

No comments:

Post a Comment