Search

Monday, April 20, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ ጠየቀ

• በአስቸኳይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅም ጠይቋል
ሰማያዊ ፓርቲ አይ ኤስ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መግደሉን ተከትሎ ባወጣው የሀዘን መግለጫ መንግስት በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣና በጭካኔ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ለማሰብ በአስቸኳይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው በሀዘን መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹የድርጊቱ ሰለባዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ግብፅ የሚገኘው ኢምባሲ አላረጋገጠም፣ በርግጥ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እየጣርን ነው›› በማለት ለሰለባዎቹ እውቅና ላለመስጠት እና ተገቢዉን እርምጃ ላለመውሰድ መፈለጉ ‹‹እንደ ሀገር አፍረናል፡፡ በተለመደው መልኩ አንድ መንግስት ነኝ የሚል አካል ሊያደርግ ይገባው የነበረውን ሚና ባለመወጣቱም ብዙዎቹን አስቆጥቷል፡፡›› ብሏል፡፡
ፓርቲው በሀዘን መግለጫው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በድጋሜ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት እያወገዘ፤ መንግስት በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ዜጎችን ደህንነትን የማስጠበቅ ግዴታውን በጥብቅ እንዲወጣ እያሳሰብን የግፍ ሰለባ ወገኖቻችንን ለማሰብ በአስቸኳይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅ እንጠይቃለን፡፡ በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ በተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና በጉዳዩ ልባቸው ለተሰበረ ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ይመኛል፡፡›› ብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment