Search

Wednesday, May 13, 2015

ኢትዮጵያዊው ዶክተር፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው ህይወታቸው አለፈ

ኢትዮጵያዊው ዶክተር፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው ህይወታቸው አለፈ


ዶክተር መስፍን አርአያ ይባላሉ። የታወቁ የፖለቲካ ሳይንቲስት እንደነበሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። በኒው ዮርክ ሃንተር ኮሌጅ ለብዙ አመታት አስተምረዋል ። አሜሪካዊት አይሁድ አግብተው የሁለት ልጆች አባትም ነበሩ። ። ከኤርትራ ወላጆች የሚወለዱት ዶክተር መስፍን የኢህአፓ አባል በመሆን አብዛኛውን ዕድሜያቸውን በትግል እንዳሳለፉ ይነገራል። አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ እንግሊዘኛ እና የደች ቋንቋ ይናገሩ እንደነበርም ታሪካቸው ያሳያል። ከዚህ ሁሉ አመት አገልግሎትና ቤተሰብ ምስረታ በሁዋላ ግን የዶክተር መስፍን መጨረሻ አሳዛኝ ነበር ። ምክንያቱ በትክክል ባይታወቅም፣ ብቸኛ ሆነው፣ ያለቤተሰብ፣ ያለዘመድ፣ መጠጊያ አጥተው፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው፣ ኒውዮርክ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። የዶክተር መስፍን አርአያ መጨረሻ እንዲህ መሆኑን አሳዛኝ ነው ይላሉ የሚያውቁ ሰዎች ሲናገሩ። አንዳንዶቹም ዶክተር መስፍን ጸባዩ ሲቀየር፣ መጠጥ ሲያበዛ፣ ከሰው መጣላት ሲጀምር ምን ሆነ ብለው ለማናገር፣ ለማገዝ፣ ለማሳከም አልተሞከረም ሲሉም ይቆጫሉ። ዛሬም ሰዎች ጸባያቸው ሲቀየር፣ የሌለባቸውን ነገር ሲያመጡ ምን ሆኑ ብለን ልንጠጋና ልንረዳቸው እንጂ፣ ልንሸሻቸው አይገባም ፣ ሰዎች ከመሬት ተነስተው አጉል ሱስ ውስጥ ሲገቡ፣ ራሳቸውን ሲጥሉ፣ ከመውቀስና ከመፍረድ ፣ ቀርቦ ማናገርና ችግራቸውን ለመረዳት መሞከር ተገቢ ነው። -

No comments:

Post a Comment