Search

Friday, May 22, 2015

የተሰነጣጠቀ ተረከዝን እንዴት በቀላሉ ማስወገድ እንችላለን? - ማጋራት ደግነት ነው Sharing is caring!



ወይ ማወቅ ደጉ: የጤና አምድ
የተሰነጣጠቀ ተረከዝን እንዴት በቀላሉ ማስወገድ እንችላለን?
(ጤናማ ውበት በቤታችን)
1. ሎሚ glycerin እና ጨው
• ሞቅ ባለ ዉሃ በጥቂቱ የሎሚ ጭማቂ :glycerin: እና ጨው: ከጨመሩ በኃላ እግርን ከ 15-20 ደቂቃ ማቆየት::
• pumice stone ወይም foot scrubber በመጠቀም ቀስ አድርጎ መፈግፈግ::
• 1 ማንኪያ glycerin እና 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ተረከዝን መቀባት:: ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት::
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
2. የአትክልት ዘይት
• እግርን ከታጠቡ በኃላ በደንብ ማድረቅ::
• የአትክልት ዘይት ተረከዝን መቀባት:: ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት::
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
3. ሙዝ
• የሙዝ ልጣጭ በመጠቀም የተሰነጣጠቀውን ተረቀዝ መቀባት::
• ከአስር ደቂቃ በኃላ መታጠብ
4. ቫዝሊን እና የሎሚ ጭማቂ
• እግርን ከታጠቡ በኃላ በደንብ ማድረቅ::
• እግርን ለ 15-20 ደቂቃ መዘፍዘፍ::
• 1 ማንኪያቫዝሊን እና 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ተረከዝን መቀባት::
• ከዚያ ካልስ አድርጎ መተኛት:: (የሚጠቀሙት ካልስ cotten ቢሆን የመራጭ ነው )
• ጥዋት በሙቅ ዉሃ በደንብ መታጠብ
• ይሄን በየቀኑ ተረከዝ ለስላሳ እስኪሆን መደጋገም::
5. ማር
ማር ከማለስልስ በተጨማሪ ፅረ-ባክቴሪያ ጠቀሜታ አለው (ስለ ማር ጠቀሜታዎች ከዚህ በፊት ያካፈልነዉን መመልከት ይችላሉ)
• የተዎሰነ ማር ሞቅ ካለ ዉሃ ጋር መቀላቀል
• እግርን ለ 15-20 ደቂቃ መዘፍዘፍ::
• ቀስ አድርጎ መፈግፈግ::
ጤናዎ ይብዛልዎት!
ማጋራት ደግነት ነው
Sharing is caring!

No comments:

Post a Comment