Search

Monday, March 4, 2013

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንቱን መረጠ

አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም በድጋሚ ለሚቀጥሉት አራት አመታት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን እንዲመሩ በድጋሚ በፕሬዝዳንትነት ተመረጡ።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቢሾፍቱ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ፥ አቶ ብርሃነን በሙሉ ድምጽ መርጧል።
አቶ ብርሃነ ባለፉት 4 አመታት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፥ ብቁ የሰው ሃይልና የጠነከረ አደረጃጀት እንዲሁም ጠንካራ ገንዘብ አቅም እንዲኖረው ማስቻላቸው ይነገራል።
ኮሚቴው የራሱ ዘመናዊ ቀልጣፋ አደረጃጀት እንዲኖረው አዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ ዘመናዊ ህንጻ ገዝቷል።
በየዘርፉም አስፈላጊ ሙያተኞችን በማሰባሰብ አቅሙን ለመገንባት መሰረት እንደጣሉ የሚነገርላቸው አቶ ብርሃነ የፖለቲካል ሳይንስ እና የህግ ምሁር ናቸው።
ሃገራቸውንም በተለያዩ ከፍተኛ ቦታዎች አገልግለዋል።
ለቅርጫት ኳስ ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ሲሆን የተጠቆሙትም ከቅርጫት ካስ ፌዴሬሽን ነው።
ጠቅላላ ጉባኤው በውሎው ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ተመልክቷል ፤ ከእነዚህ መሃል የ2012 እቅድ አፈጻጸም ፥ የኦዲት ሪፖርት መርምሮ በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን አዳዲስ አራት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትንም መርጧል።
ለአባላቱም የስነ ምግባር ደንብ መመሪያ አጽድቋል።
ኮሚቴው በመጨረሻም የቢሾፍቱ ኦሎምፒክ መንደርን መርቋል።

No comments:

Post a Comment