Search

Monday, March 18, 2013

ቅዱስ ጊዮርጊስ የማሊውን ጆሊባ 2 ለ 0 አሸነፈ

ለአፍሪካ ሻምፕዮን  ሊግ ማጣሪያ ዛሬ አዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስና የማሊው ጆሊባ የተገናኙ ሲሆን ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን ያስቆጠሩት ከእረፍት በፊት ዮናታን ብርሃነና ከእረፍት በኋላ ፍፁም ገብረማርያም ናቸው ።
ቡድኖቹ ዛሬ ያካሄዱት ጨዋታ የመጀመሪያ ሲሆን ፥ የመልስ ጨዋታቸውን ከሁለት ሳምንት በኋላ በማሊ ያካሂዳሉ።
በሌላ ዜና ለአፍሪካ ኮን ፌዴሬሽን ዋንጫ ሱዳን ካርቱም ላይ ከአልሃሊ ሸንዲ ጋር የማጣሪያ ጨዋታ ያደረገው ደደቢት 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
ሁለቱ ቡድኖች ከሁለት ሳምንት በኋላ አዲስ አበባ ላይ የመልስ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።

No comments:

Post a Comment