Search

Tuesday, March 12, 2013

የሆሊውድ የፊልም ባለሙያዎች በማንዴላ ላይ ለሚሰሩት ፊልም አዲስ አበባ ገቡ


 የደቡብ አፍሪካና የሆሊውድ የፊልም ባለሙያዎች በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪና የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የስጦታ ሽጉጥ ዙሪያ የፊልም ቀረጻ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ማንዴላ በቀዳማዋ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በቀድሞው የኮልፌ ማሰልጠኛ ተቋም ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠናን ለ8 ሳምንታት ተከታትለዋል።
በወቅቱ ማንዴላ የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው ደቡብ አፍሪካ ሲመለሱ ፥ ከቀዳማዊ ሃይለስላሴ በስጦታ መልክ የተበረከተላቸውን የስጦታ ሽጉጥ ይዘው ነበር።
ማንዴላ በአፓርታይድ ስርአት አራማጆች በሮቢን ደሴት በታሰሩበት ወቅት በስጦታ የተበረከተላቸውን ሽጉጥ ከመሬት በታች ቆፍረው ቀብረውት ነበር።
ይሁን እንጅ ማንዴላ ከ27 አመታት የእስር ቆይታ በኋላ ከእስር ቤት ሲወጡ በስጦታ ያገኙትን ያንን ታሪካዊ ሽጉጥ በአካባቢው በተካሄዱ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ምክንያት ሊያገኙት አልቻሉም።
የሆሊውድ የፊልም ባለሙያዎችም ይህህነ ታሪክ በመንተራስ የፊልም ቀረጻ ለማድረግ በማሰብ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ፊልሙ ለመላው አለም በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በፊልሙ ስራ ውስጥ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የሚሳተፉ ሲሆን ፥ የፊልሙን የኢትዮጵያ ቀረጻ ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅትም በአብዛኛው ተጠናቋል።
የፊልም ስራውን አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተም ዛሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር ቤት በዝግጅቱ አስተባባሪዎች መግለጫ ይሰጣል።

በወንድወሰን አንዱዓለም

No comments:

Post a Comment