Search

Friday, March 8, 2013

አበበ ቢቂላ እና ጋቢው

አበበ በሮም ኦሎምፒክ በማሸነፉና የኢትዮጵያ ስም በማስጠራቱ ትልቅ ኩራት ሆነ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት ተጀምረ፡፡ አበበ በተለያየ ጊዜ ሩጫ ሲያካሄድ እያቋረጠ ይወጣ ጀመር፡፡ ችግር ሲገጥመው ለይድነቃቸው ያማክራል፣ የቡድኑ ሐኪም ዶክተር ፍሬደሪክና ይድነቃቸው በአበበ ጉዳይ ተወያዩና አስመረመሩት ትርፍ አንጀት አለበት፣ እንዲህ ሆኖ መሮጥ አይችልም አሉ፣ ኦፕራሲዮን መሆን አለበት፣ ሁለቱም ወሰኑ ለአበበም ነገሩት፣ ‹‹ እናንተ እንዳላችሁ›› አለ፡፡ ሆስፒታል አስተኙት ኦፕራሲዮን ተደረገ፡፤ጉዳዩ ሌላ ቦታ ተሰማ ጭቅጭቅ ተፈጠረ፡፡ ‹ይድነቃቸውና ፍሬደሪክ አበበን አስቀደዱት›› ተባለ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ወርቅ እንዳታመጣ በማሰብ ነው ተብሎ ተወገዙ፣ አበበ ግን ‹‹ከማንም በላይ እነሱ ለእኔና ለውጤቱ አስበው ነው›› አለ፡፡
 አበበ ገና ኦፖራሲዮኑ ሙሉ በሙሉ ሳይደርቅ ወደ ቶኪዮ ሄደ አበበ በሽተኛ ነውና ጋቢ ለብሶ መሄድ ነበረበት የጃፓን ሐኪሞቸም ህመሙንና ስፌቱን አዩ እንዲህ ሆነህ መንቀሳቀስ አትችለም አሉት፣ አበበ ግን ልዩ ፍጡር ነበር ሮም በባዶ እግሩ ሮጧላ፡፡ ቶኪዮ ላይ ደግሞ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ሳያገግም ማራቶንን ሮጠ የጃፓን ጋዜጦች አበበ በሽተኛ መሆኑን ነው የሚያውቁት በመሮጡ ተገረሙ፣ በማሸነፉም ተደነቁ እውነትም ልዩ ፍጡር ነው አሉ፡፡ ለብሶት የሄደው ጋቢ አሁንም ድረስ እዚያው ጃፓን ይገኛል፣ ሰዎች ጋቢውን ይጎበኙታል ገንዘብ ከፍለው ይለብሱና ፎቶ ይነሳሉ አበበ ሮጦ እንዳሸነፈ ወደ ይድነቃቸው ሄደና ‹‹ ወሬኞችን ጭጭ አደረግናቸው›› አለ፡፡ ሮም ላይ ሲያሸንፍ ደግሞ ወደ ይድነቃቸው ጠጋ ብሎ ‹‹ አንጀቶን አላራስኩትም ?›› አላቸው ያን ጊዜ ምንም ለማያመጡ ለምን ሄዱ ተብሎ ከቤተ መንግሥት ወቀሳ ነበር፣ አበበም የመጀመሪያውን ወርቅ በማምጣቱ ይድነቃቸው ተደሰቱ አበበ የሮጠው መስከረም 1 ቀን ነው ይድነቃቸው የተወለዱት ደግሞ መስከረም 1 ቀን ነው፡፡ ይድነቃቸው ሻምፓኝ ይዘው መጡ፡፡ ‹‹ ለኔም ለአንተም›› አሉት መስከረም 1 ለሁለቱም ልዩ ቀን ነበር፡፡
 
Source:librogk.com

No comments:

Post a Comment