Search

Friday, May 17, 2013

ከሽሮ ችርቻሮ ወደ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባለንብረትነት ተሸጋገሩ

ከ200 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተሠራው ሆቴላቸው ቅዳሜ ይመረቃል
በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ አንዲት ወይዘሮ ከሽሮ ችርቻሮ ሸያጭ ተነስተው በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የፊታችን ቅዳሜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሆቴሉ ቃል አቀባይ በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ወይዘሮ አማረች ዘለቀ የተባሉ የአምስት ወንዶች ልጆች እናት ያሠሩት ይኼው ሆቴል፣ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉዋቸው 70 የመኝታ ክፍሎች ሲኖሩት በደቡብ ክልል በዓይነቱ የመጀመርያው ነው ተብሏል፡፡


ሆቴሉ ባለ አሥር ፎቅ መንታ ሕንፃዎች ሲኖሩት፣ ከ250 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ከቃል አቀባዩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ወይዘሮ አማረች እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ እጃቸው ላይ በነበረው የአስቤዛ ገንዘብ ሽሮ ገዝተው በችርቻሮ መሸጥ በመጀመራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ ዓይነቱ እንቅስቃሴያቸው ከጥቂት ዓመታት በኋላ እየጐለበተ መጥቶ በመሐል ሐዋሳ ላይ “ሴንትራል” የሚል መጠሪያ ያለው አንድ መለስተኛ ሆቴል አቋቁመዋል፡፡ በዚህም ሳይገቱ ይህንኑ መለስተኛ ሆቴላቸውን ወደ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ለማሳደግ መብቃታቸውን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment