Search

Friday, May 10, 2013

የቤት ፈላጊዎች መስፈርትና የምዝገባ መመሪያ ይፋ ተደረገ

የአዲስ አበባ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ  የ 40 በ 60 ፣ የ 10 በ90 እና 20 በ80 የጋራ መኖሪያ  ቤት ፈላጊዎች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታና የምዝገባ ስነ ስርአት ይፋ አደረገ ፡፡ በዚህም መሰረት የ 10 በ 90 እና የ 20 በ 80  ምዝገባ ከሰኔ 3 እስከ 21 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት በሁሉም ወረዳዎች ይደረጋል ፡፡
የ 40 በ 60 ምዝገባ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ከሀምሌ 5 እስከ 17  የሚካሄድ ሲሆን በማህበር ለሚደራጁ ደግሞ ምዝገባው  ከ ሀምሌ 15 እስከ 30 የሚካሄድ ይሆናል ፡፡
ለመንግስስት ሰራተኞች ደግሞ በተለየ ሁኔታ  117 ወረዳ በሚል ምዝገባው ለብቻ የሚካሄድ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ አሳውቋል ፡፡
ለምዝገባ ብቁ ለመሆንም በቢሮው የሚከተሉት መስፈርቶች ተቀምጠዋል ፡፡
* እድሜው/ዋ ከ 18 አመት በላይ የሆነ
* በከተማው ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ አመታት የኖረና እየኖረ ያለ።
* የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ አመታት በስራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ  የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ፥ ማስረጃው ቦታውን ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ካቀረበ ብቁ ይሆናል፡፡
 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

No comments:

Post a Comment