Search

Tuesday, May 21, 2013

በጣና ሃይቅ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይዎት አለፈ

ትናንት ከቁንዝላ ወደ ደልጊ 102 ሰዎችን አሳፋሮ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በመግለበጡ እስካሁን አምስት ሰዎች መሞታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ደልጊ መዳረሻ ስፍራ በግምት 150 ሜትር ርቀት ላይ  ፥ ተሳፋሪዎችን ለማውረድ ሲቃረብ  ጀልባው የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበትም ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት።
የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ለባልደረባችን ኤልያስ ተክለወልድ እንደነገሩት ፥ የአደጋው መንስኤ እስካሁን በእርግጠኝነት ባይታወቅም  ፤ ተሳፋሪዎቹ ለመውረድ እየተዘጋጁ ሰለነበር በአንድ ስፍራ መከማቸታቸው የሚዛን መዛባት አስክትሎ ለአደጋው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ፋሲለደስ በመባል የምትጠራውን ጀልባ ሲያሽከረክር  የነበረው ካፒቴን በህይወት የተረፈ ሲሆን ፥ ለፖሊስ በሰጠው ቃልም ይህኑኑ አረጋግጧል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት ምናልባትም በህይወት የተረፈ ካለ እና ተጨማሪ አስከሬኖችን የማፈላለጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ይህ አይነቱ አስከፊ አደጋ ሲያጋጥም የመጀመሪያው ነው ያሉት ኮማንደር ዘመነ ፥ በቀጣይ ትክክለኛውን መረጃ በማጣራት ምክንያቱን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።
 (ኤፍ ቢ ሲ)

No comments:

Post a Comment