Search

Saturday, June 1, 2013

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ ወደቆ ያገኘውን 3.4 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ አስረከበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ መንገደኛ የጠፋ 184 ሺህ ዶላር ወይም ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ  ለባለቤቱ አስረከበ፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጽዳት ስራ የሚሰራው ብርሃኑ ጀምበሩ የተባለው የ21 አመት ወጣት ሥራውን ሲያከናውን የተጠቀለለ እቃ ያገኛል ፥ብርሃኑ ጥቅሉ  ገንዘብ መሆኑን ቢያቅም ለበላይ ኃላፊዎች ማስረከቡን ይናገራል፡፡
የገንዘቡ ባለቤት በኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ንግድ የተሰማሩና ዜግነታቸው ጋምቢያዊ የሆነው መንገደኛ ወደ ሆንግ ኮንግ ጉዞ ሲያደርጉ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ነበር በተሳፈሩበት አውሮፕላን ላይ ገንዘባቸውን ረስተው የወረዱት፡፡
ለክፍያ ያዘጋጁት ገንዘብ  ከአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ተሳፍረው ሆንግኮንግ እስኪደርሱ ድረስም መጥፋቱን  አላወቁም ነበር፡፡ግለሰቡ ገንዘባቸው መጥፋቱን ባወቁ ቅፅበት ግን፥ ለአየር መንገዱ አግባብ ባለው መስመር ገንዘባቸው መጥፋቱን ያሳውቃሉ፡፡
በዚህም በትናንትናው እለት ካሉበት ቦታ መጥተው ገንዘባቸውን ለመረከብ በቅተዋል፡፡በኢትዮጵያ አየር መንገድ ታሪክም ይህን የሚያክል ከፍተኛ ገንዘብ ለባለቤቱ ሲመለስ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment