Search

Thursday, February 21, 2013

በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ የአራት ሰዎች ህይዎትን አጠፋ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋሲል ፋርማሲ አካባቢ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ የአራት ሰዎች ህይዎት አለፈ።
በአደጋው ቁጥራቸው ያልታወቁ ቤቶች እና 1 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ወድሟል።
በዚህ አደጋ 10 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት እና የበርካታ ሰዎች ህይወትንም መታደግ ተችሏል።
እሳቱን ለማጥፋት ከአዲስ አበባ ከተማ ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ፥ 60 የእሳት አደጋ ሰራተኞች በ6 ተሽከርካሪዎች በመታገዝ 89 ሺህ ሊትር ውሃ መጠቀማቸውን በኤጀንሲው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ለመስጠት 5 አምቡላንሶች የተሰማሩ ሲሆን ፥ አደጋው ከጥንቃቄ ጉድለት የተከሰተ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

No comments:

Post a Comment