Search

Wednesday, August 19, 2015

በማልቀስ የምናገኛቸው አስገራሚ የጤና በረከቶች

በማልቀስ የምናገኛቸው አስገራሚ የጤና በረከቶች

መቼስ በከፋንና ባዘንን ወቅት፣ የፍቅር ግንኙነታችን ሲቋረጥ፣ አሳዛኝ ፊሌሞች ስንመለከት፣ ከመጠን በላይ ስንደሰትና በሌሎችም ምክንያቶች  ስሜታችንን ፈንቅሎ የሚወጣው እንባችን አስገራሚ የጤና ጠቀሜታዎችስ እንደሚያስገኝልን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
በአማካኝ በቀን 280 ግራም በዓመትም 30 ጋሎን እንባ ከአይናችን እንደሚፈስ ጥናቶች ያመለክታሉ።
በካሊፎርኒያ ሳኔ ጆሴ የስነልቦና ባለሙያ ሳይኮቴራፒስት የሆኑት ሻሮን ማርቲን እንደሚሉት ማልቀስ (ማንባት) እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፤ ማልቀስ ጭንቀትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ማድረጉ ደግሞ ከሁሉ ጎልቶ የሚታይ ጠቀሜታው ነው ብለዋል።
ማልቀስ ከሚያስገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎች ዋና ዋናዎቹን ስንቃኝ፦
1. ከሰውነታችን አላስፈላጊ ኬሚካሎችን ያስወግዳል፣
እንባ የአዕምሮ መታደስን ብቻ ሳይሆን የሚያመጣው ከሰውነታችን  ጎጂ  ኬሚካሎች በእንባ አማካኝነት እንዲወገዱ ባማድረግ ጭንቀትንም ሆነ መብሰልሰልን ያስወግድልናል።
ዶክተር ዊሊያም የተሰኙ የዘርፉ ተመራማሪ እንደሚናገሩት እንደ ላብ እና ሽንት ሁሉ እንባም አላስፈላጊና ጎጂ (toxic) ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ጠቃሚ ነው።
2.ባክቴሪያን ይገላል፣
እንባ በእናት ጡት ውስጥ የምናገኘውንና ሊሶዚም የተሰኘውን ባክቴሪያን በተፈጥሮ የመግደል አቅም ያለውን ንጥረ ነገር ይዟል።
ሊሶዚም እስከ 95 በመቶ ባክቴሪያን ከአምስት እስከ 10 ደቂቃ ባለ ጊዜ ውስጥ የመግደል ሀይል አለው።
እ.ኤ.አ በ2011 የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው ሊሶዚም የአብዛኛዎቹን ባክቴሪያዎች  የላይኛው ግድግዳ ክፍል (cell walls) ከጥቅም ውጪ በማድረግ ባክቴሪያው እንዲሞትና እንዳይራባ ያደርጋል።
3. የእይታ ችሎታን ያሻሽላል፣
እንባ የእይን ኳስንና የአይን ቆብን በማለስለስ የእይታ ችሎታችን እንድሻሻል የሚያደርግ ሲሆን፥ አቧራን የመሳሰሉ ቆሻሻዎችን በማስወገድ ጭምር የተሻለ እይታ እንዲኖረን ያግዛል።
እንባ በተጨማሪም የአይን እንቅስቃሴ እንዲቀላጠፍ ይረዳል።
4. ጭንቀትን ያስወግዳል፣
ማልቀስ ከነበርንበት ስሜት በመውጣት እረፍት እንዲሰማንና ሸክሙ ቶሎ እንዲቀልልን በማድረግ ጭንቀትን እንድናስወግድ ያግዘናል።
የጭንቀት መንስኤ የሆኑ ሆርሞኖች ከሰውነታችን  የሚወገድበት መንገድ እንደመሆኑም  ያስጨነቀን ነገርን ለመርሳት እንደመሳሪያ ሆኖ ያገለግለናል።
ይህም ጭንቀትን ተከትለው የሚመጡትን እንደ ራስምታት፣ ከፍተኛ የደም ግፊት የመሳሰሉት እንዳይከሰቱብን ያደርጋል ማለት ነው።
5.ጥሩ ባህሪ (ሙድ) እንዲኖረን ፣
ማልቀስ ከየትኛውም ሰውሰራሽ ነገር በተሻለ ባህሪን (ሙድን) በማስተካከል ረገድ አቻ የለውም።
ባህሪያችንን በማስተካከል ረገድ ተመራጭ መሆኑን ነው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008 በአሜሪካ ደቡብ ፍሎሪዳ የተደረገ ጥናት ያመለከተው።
እንባ ጭንቀትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ተመልሰን በዚያው ሴሜት ውስጥ እንዳንገባ በማድረግ ረገድም ሚናው ላቅ ያለ ነው።

 from : FBC       

No comments:

Post a Comment