Search

Friday, December 7, 2012

ምኒሊክ



".... ዘመናዊ ኢትዮጵያን የፈጠረ ሰው ነው:: "

+
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን አውቶሞቢል የነዱና ፔርፌክት ድራይቨር የሚለውን የመጀመሪያውን የመንጃ ፈቃድ የተቀበሉ
+
የመጀመሪያውን የእህል ወፍጮ መኪና ያስመጡና በወቅቱ ወፍጮው ጋኔን ነው ተብሎ ሰው
በመሸሹ ጋኔን ያለመሆንኑን ለማሳየት ቆመው እህል ያስፈጩ
+
የመጀመሪያውን ስልክ አስገብተው ጋኔኑ ከዙፋኑ ይውጣ ብለው የዘመኑ
ጳጳስ ጭምር ከባድ ተቃውሞ ቢያነሱባቸውም ታግለው ስልክን የመሠረቱ
+
የመጀመሪያውን ብስክሌት መንዳት ተምረው ባለቤታቸውንም በማስተማር ሴቶች ከመሸፋፈንና ከማፈር እንዲወጡ የታገሉ
+
የመጀመሪያውን ሆቴል ከፍተው ሚስታቸውን ወጥ ቤት አድርገው በገንዘባቸው መኩዋንንት እየጋበዙ ሆቴል መብላትን ያስተማሩ
+
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ 1881/ በአዋጅ አረን ቢጫ ቀይ እንዲሆን ያደረጉ
+
ለመጀመሪያ ጊዜ ፎቶግራፍ ማንሳትና፣ ፊልም አጥቦ ማተም የተማሩ
+
የተለያዩ አበቦችንና ጽጌረዳዎችን ከኤሮፓ እያስመጡ እስካሁን የምንጠቀምባቸውን ልዮ ልዩ አበቦችን ያራቡ
+
የኮክ፣ የእንጆሪ፣ የወይን እና የመሳሰሉትን የአትክልት ልዩ ዘሮችን እያስመጡ ያራቡ
+
እስከ ዛሬ ለኢትዮዽያ ትልቅ ጥቅም እየሰጠ ያለውን ባህር ዛፍን አስመጥተው የተከሉና ያባዙ
+
በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የውጭ አገር ትምህርት ቤት የከፈቱ
+
የመጀመሪያውን የሙዚቃ ትምህረት ቤት የከፈቱ
+
ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ያስገቡ
+
ከጂቡቲ አዲስ አበባ የባቡር ሀዲድ አዘርግተው የመጀመሪያውን የባቡር አገልግሎትን ያስጀመሩ
+
የመጀመሪያውን ዘመናዊ የመንገድ ሥራ ያስጀመሩ
+
የመጀመሪያውን የፖስታ ድርጅትን የከፈቱ
+
ሰው ሲባል እኩል ነውና ማንም ሰው ሰውን ባርያ እንዳይል ብለው የባርያን ነፃነት ያወጁና ሰው እንደከብት እንዳይሸጥ የታገሉ
+
ሴት ልጅ በወላጆችዋ ምርጫ ሳይሆን በፈቃድዋ የመረጠችውን ባል እንድታገባ ያወጁና ለሴት ልጆች ነፃነት የታገሉ
+
ሠራተኛ በሥራው እንዳይበደል አዋጅ ያስነገሩ
+
ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ አስገዳጅ ሕግ ያወጡ
+
የተሠራ ጨርቅ ከማስመጣት ይልቅ ድር እያስመጡ ማሠራት እንደሚረክስ አውቀው የመጀመሪያውን ድር ማስመጣትን የጀመሩ
+
የመጀመሪያውን የጥይት ፋብሪካን ያቁዋቁዋሙ
+
ቧንቧ ውሃ
+
ሕክምና፣ ሆስፒታል፣ ፋርማሲ
+
ባንክ፣ ገንዘብ
+
አረቄ
+
የሙዚቃ ሸክላ
+
ማተሚያ
+
ጋዜጣ
+
ፖሊስ(ዘበኛ)
+
የጽሕፈት መኪና
+
ሲኒማ
+
ጫማ
+
ፍልውሃ
+
ትምባሆ
+
የመጀመሪያውን ....

No comments:

Post a Comment