” ዋሊያዎቹን ለማሰልጠን ለፌዴሬሽኑ ማመልከቻ አስገብቻለሁ፤ ከ4 አመት በፊት የጀመርኩትን እንድጨርስ እድሉ ይሰጠኝ” —–>አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊት
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን ማሰናበቱ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ ለስፖርት ቤተሰቡ ሳያሳውቅ የተለያዩ የአገር ውስጥ አሰልጣኞች በእጩነት መታሰባቸው መሰማቱ ይታወሳል። ለኢትዮ- ኪክ በደረሰው ታማኝ መረጃ መሰረት የቀድሞ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቤልጂዬማዊው ቶም ሴንትፊት በእጩነት ለመወዳደር ማስረጃዎቻቸውን አንደላኩ በመስማታችን ጉዳዮን ለማጣራት አሰልጣኙን አነጋግረናል። እንድታነቡት እንጋብዛለን:–
ኢትዮ-ኪክ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ማሰረጃዎትን ለፌዴሬሽኑ እንዳስገቡ ሰምተን ነበር፤ የተባለው ነገር ምን ያህል እውነት ነው?
አሰልጣኝ ቶም:- የተባለው መረጃ ትክክል ነው። ኢትዮጵያን በጣም እወዳታለው። ስለዚህም ዶኩመንቶቼን ለፌዴሬሽኑ ሰሞኑን አስገብቻለው። በ2011 ኢትዮጵያ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ባሬቶ መባረራቸው እኮ በይፋ ፌዴሬሽኑ ለህዝብ ሳያሳውቅ እንዴት እርሶ ማመልከቻዎቱን ላኩ ?
አሰልጣኝ ቶም:- እኔ ከሳምንታት በፊት ጭምጭምታ ሰምቼ ነበር። ይሄ እንደሚሆን ደግሞ ከአንድ አመት በፊት አውቅ ነበር፣ በተጨማሪም ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለኝ። ስለዚህ ልኪያለው።
ኢትዮ-ኪክ:- ዋሊያዎቹን ድጋሚ የማሰልጠን እድሉን ቢያገኙ ምን የተለየ ነገር ለማድረግ አቅደዋል?
አሰልጣኝቶም:- በ2011 የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ስረከብ የተሸነፈ ቡድን ነበር። በናይጄሪያ 4-0 እና በጊኒ 4-1 ነገር ግን ቡድኑን ከተረከብኩ በኃላ ከናይጄሪያ ጋር 2-2 አቻ ወጥተን በጊኒ ጠባብ ውጤት 1-0 ተሸነፍን። ከዛ ቀጥሎ ከማላዊ 0-0 ማዳጋስካርን 4-2 አሸንፈናል። የኢትዮጵያን ተጨዋቾችን አውቃለው፤ባህሉን እና አሰተሳሰባቸውን ስለዚህ ከአራት አመት በፊት የጀርኩት ስራ እንድጨርስ እድሉ ይሰጠኝ። የማሰልጠን እድሉን ካገኘው ደግሞ አላማዬ የማሰለጥነውን ቡድን ለAFCON የአፍሪካ ዋንጫ እና ለ2018 የአለም ዋንጫ ማብቃት ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- ማሪያኖ ባሬቶም እኮ ለአፍሪካ እና ለአለም ዋንጫ ዋልያዎቹን አበቃለው ብለው ነበር ?
አሰልጣኝ ቶም:- ትክክለኛ አሰልጣኝ ከተገኘ ይቻላል።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ትክክለኛ አሰልጣኝ አይደሉም እያሉኝ ነው?
አሰልጣኝ ቶም:- በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ አሳብ ከመስጠት ብቆጠብ እና ጉግል ላይ መላሹን ማየት….
ኢትዮ-ኪክ:- ከአራት አመት በፊት ለምን ከስራዎት ተባረሩ?
አሰልጣኝ ቶም:- በ2011 ቡድኑ መልቀቅ መለየት አልፈለኩም፤ ነገር ግን የኢት.እግርኳስ ፌዴሬሸን በወቅቱ የምንከፍልክ ገንዘብ የለንም አሉኝ። ባለፈው አመትም ፈልጌ ነበር። እኔ በጣም ለቦታው የምመጥን አሰልጣኝ ነኝ። በአፍሪካም ሆነ በአውሮፖም በቂ ልምድ አለኝ። የ UEFA Pro የአሰልጣኝነት ፍቃድ አለኝ፤ በአለም ላይ አንድ አሰልጣኝ ሊኖረው የሚገባው ትምህር አለኝ። በ UEFA- A እና UEFA -B ዲግሪ ፤ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ኮርስ ፤ Skill Development ስልጠና እና የስፖርትሳይኮሎጂ የዮኒቨርስቲ ዲግሪ አለኝ። በአፍሪካ የሚገኙ አምስት አገራት አሰልጥኛለው። ቁጥራቸው 37 የሚደርሱ በፊፋ እውቅና ባላቸው ጨዋታዎች ያሰለጠንኩት ቡድን አንድም በሜዳው የተሸነፈ የለም።
ኢትዮ-ኪክ:- ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ድጋሚ እድል ይሰጠኝ እያሉ ነው?
አሰልጣኝ ቶም:- አዎ !የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በድጋሚ ማሰልጠን እፈልጋለው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ሻምፖዮናዋ ናይጄሪያ ጋር ተጫውቶ ጥሩ ውጤት እንዲያመጣ ያደረኩኝ ነኝ ። በ2011 እኮ በFIFA ድህረገፅ እና ኪክ ኦፍ ደቡብ አፍሪካ ድህረገፅ ላይ ኢትዮጰያ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ እና በ2014 የአለም ዋነጫ ማጣሪያ እንደምታልፍ ቀድሜ ተነግሬ ነበር። ይህን ያልኩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጠልቄ ስለማውቀው ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- የኢትዮ.እ ፌዴሬሽን ላስገቡት የአሰልጣኝነት ጥያቄ የሰጦት ምላሽ ካለ?
አሰልጣኝ ቶም: – የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምላሹን እንኳን ገና አልነገሩኝም እየጠበኩ ነው።
ኢትዮ-ኪክ:- አሰልጣኝ ቶምን በአንባቢዎቼ ስም አመሰግናለው!
source : zhabesha
No comments:
Post a Comment