ስለ ፍቅር
አንድ ወጣት ፍቅረኛውን ሞተር ሳይክሉ ላይ አፈናጦ በሰአት 160 ኪሎ ሜትር ይከንፋል።
ልጅት፦ እባክህ ፍጥነት ቀንስ የኔ ፍቅር፤ ፈራሁ እኮ
ልጅ፦ እንድንዝናና ብዬ ነው
ልጅት፦ ኖ ፍቅር አይቻልም፤ በጣም አስፈሪ ነው፤ ፕሊስ ፍጥነት ቀንስ
ልጅ፦ እሺ እንድቀንስልሽ እንደምትወጂኝ ንገሪኝ
ልጅት፦ መልካም፤ አፈቅርሀለሁ የኔ ቆንጆ። እሺ አሁን ቀንሰው የኔ ፍቅር
ልጅ፦ ሳም አድርጊኝ
[ልጅት፦ ወገቡን እንደያዘች ሳም አደረገችው]
ልጅ፦ የራስ ቆቤ (ሄልሜቴ) አልተመቸኝም ቆረቆረኝ። አንሺልኝና አንቺ አጥልቂው
በማግስቱ አንድ የአገሬው ጋዜጣ እንዲህ የሚል ወሬ ይዞ ወጣ
አንድ ሞተር ሳይክል በፍሬን ብልሽት ምክንያት ከአንድ ሕንፃ ጋር ተላትሞ ሞተሩን ሲያሽከረክር በነበረው ወጣት ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አብራው የነበረችው ፍቅረኛው ግን ተርፋለች። እውነታው ደግሞ ሞተሩን ያሽከረክር የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ፍሬን እንደተበላሸበት ሲያውቅ እሷ እንዳታውቅ በማድረግ የመጨረሻ የፍቅር ቃሏን ተቀብሎና የስንብት ሰላምታዋን ከሰጠችው በኋላ የራስ ቆቡን እሷ እንድታጠልቅ በማድረግ እሷ በህይወት እንድትኖር ራሱን መስዋዕት አድርጓል።
No comments:
Post a Comment