Search

Friday, January 25, 2013

ኤፍቢአይ የመረጃ ዋና ቋቶችን በሚዘጋበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞች ላይ የኢንተርኔት አገልገሎት መቋረጥ እንደሚደርስ ተገለጸ

ፍ ቢ አይ አንዳንድ የመረጃ መረብ ላይ ስርቆት የሚፈጽሙ ግለሰቦች  የሚጠቀሙበትን ዋና የመረጃ ቋቶች በሚዘጋበት ጊዜ በአብዛኛው በአሜሪካና በእንግሊዝ የሚገኙት ከ300 መቶ ሺ በላይ  የሚደርሱ ደንበኞች ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ሊደርስ  እንደሚችል  ገለፀ።

እ.ኤ.አ በህዳር  2011 ላይ  ኤፍ ቢ አይ ባካሄደው ዘመቻ  ቫይረስን  በመጠቀም ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደንበኞች ላይ ጥቃት ለማደረስ የተዘጋጁ የመረጃ ቋቶችን  መለየቱን  ያስታወቀ ሲሆን፤ ደንበኞች የተለያዩ ድረ-ገጾችን በሚከፍቱበት ወቅት  ማስታወቂያዎችን እንዲመለከቱ በማድረግ ክፍያ ካልፈጸሙ ጥቃት እንደሚያደርሱባቸው  ይገልጻሉ፡፡

ማስታወቂያ በመልቀቅ በሚፈጽሙት የድረ-ገፅ ጠለፋና ደንበኞችን በማስገደድ በሚፈጽሙት ወንጀል ተግባር ከ14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያገኙ ሲሆን፤ በተጨማሪም በመረጃ ቋታቸው ቁልፍ የሆኑ የድህረ-ገጽ አውታሮችን በቁጥጥራቸው ሥር ያውላሉ።

እያንዳንዱ ድረ-ገጽ የራሱ የሆነ የአድራሻ ስም እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ አድራሻ ወደ ቁጥርነት በመቀየር ከዋና የመረጃ ቋት ጋር ግንኙነት በማድረግ ኮምፒውተሮች ድረ-ገጽን ለመጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል፡፡

በዚህ መሃል የተደራጁት ወንጀለኞች ዋና የመረጃ ቋቱ ላይ ጥቃት በመፈጸም ኮምፒውተሮች የአድራሻ ስሞችን አስገብተው ወደ  ቁጥርነት የሚቀይሩበትን  ሂደት  እንዲስተጓጎል  ያደርጋሉ ፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኤፍቢአይ ወንጀለኞቹ ላይ ክትትል ለማድረግ ከካሊፎርኒያው  አይ ኤስ ሲ ኩባንያ ጋር እየሰራ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሌሎች የደህንነት ተቋማት ጋር በመተባበር የደንበኞች ኮምፒወተሮች ላይ በመረጃ ቋት  አማካኝነት ጥቃት  መድረሱን በማረጋገጥና ተጠቂዎችን የማንቃት ሥራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ጥቃት እንደደረሰባቸው ለማወቅ የሚያስችል  ማጣሪያ በኢንተርኔት  በመለቀቁ  ከአራት ሚሊዮን  በላይ ደንበኞች ላይ  ይደርስ የነበረው ጉዳት  ወደ  300 ሺ መቀነሱን  በዋና የመረጃ ቋት  በሚደርሰው ጥቃቶች  ላይ  የሚሰሩት ድርጅቶች ያወጡት መረጃዎች ያሳያል።

በአብዛኛው በጥቃቱ ኢላማ የሆኑት ኮምፒወተሮች የሚገኙት በአሜሪካ ቢሆንም ሌሎች  እንደ ጣሊያን፣ ህንድ፣ እንግሊዝና ጀርመን የመሳሰሉ ሃገራት ውስጥ የሚገኙ ቀላል የማይባሉ የደንበኞች ኮምፒውተሮች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን መረጃዎች የሚጠቁሙ ቢሆንም በአይ.ኤስ.ሲ ኩባንያ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚያስፈልግም  ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት  የጥቃቱ ምንጭ ናቸው  ተብለው  የተለዩት ዋና የመረጃ ቋቶች  እ.ኤ.አ  ከሐምሌ 9 በኋላ እንዲዘጉ ስለሚደረጉ አንዳንድ የመረጃ ቋቶቻቸው አማካኝነት  የጥቃቱ ኢላማ የሆኑ ደንበኞች ድንገተኛ የሆነ የኢንተርኔት መቋረጥ እንደሚገኝማቸው ተገምቷል።

የኤፍ.ሰ ኪውር ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ሲያን ሱሊቫን በጉዳዩ ላይ  አስተያየታቸውን ሲሰጡ ይህ ችግር ግልፅ እስኪሆን ድረስ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችልና  አንዳንድ የመረጃ ቋቶች በደንብ ተለይተው እስኪያዙ ድረስ ደንበኞች ድረ-ገጾቻቸውን  መጠቀም እንደሚያስቸገራቸውና ግማሹ የመረጃ ምንጭ ሰርቶ ሌላኛው በማይሰራበት ጊዜ ግር ማሰኘቱ እንደማይቀር ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment