Search

Thursday, December 27, 2012

Marvelous Tower


Crescent Moon Tower in Dubai (project under construction)

JANO BAND



Music that transcends culture and time with a new Rock edge has a name: JANO. Jano formed in 2011 with the mission to transform traditional African music and to shape the future of rock ‘n roll. Born and raised in Ethiopia, the band’s ten members share a musical passion with them since early childhood days. In January 2012, JANO completed their first full LP titled, ERTALE, written in the Ethiopian language of Amharic. Their soulful music focuses on the topics of love, adventure, loss and the journeys we all take through life, played with the African rhythm of their youth as the backdrop to a new, vibrant rock sound. 


Rocking the music industry at home in Africa and abroad, JANO’s music has been heralded as “totally new” with “exceptional vocals and production quality.”

JANO is produced by the team who brought Ziggy Marley & the Melody Makers over 15 years of musical success, including five Grammy’s and American Music awards, lead by Addis Gessesse and now Rock the World Music.

All it takes is a listen to know that the future of rock is JANO.


Monday, December 24, 2012

የአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር አውቶቡስ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

የትራንስፖርት ዋጋው ከታክሲ ዋጋ ያነሰ ነው ተብሏል
አሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር በአዲስ አበባ የግል የከተማ አውቶብስ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ሃያ አምስት አውቶቡሶችን ባለፈው ረቡዕ ወደ አገር ውስጥ እንዳስገባ ተገለፀ፡፡ እያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገዙት አውቶቡሶች ባለፈው ታህሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡ ሙሉ በሙሉ በአውሮፓ ሞተር የተሰሩትና ቻይና ውስጥ የተገጣጠሙት አውቶቡሶች፤ 100 ሰው የመጫን አቅም እንዳላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አቶ አዲል አብደላ የአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሣቢ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ 
አውቶቡሶቹ የቴሌቪዥን ስክሪን ያላቸው፣ የመንገደኛውን ምቾት የሚጠብቁና ለአገራችን አየር በሚስማማ መልኩ የተገጣጠሙ መሆናቸውንም አቶ አዲል ገልፀዋል ፡፡ ድርጅቱ በመጀመሪያው ዙር ሃያ አምስት አውቶቡሶችን ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ሲሆን በቀጣዮቹ አራትና አምስት ወራት ሌሎች ሃያ አምስት አውቶቡሶችን ለማስገባት እንዳቀደ ተገልጿል፡፡
አውቶቡሶቹ የሚሰማሩበት መስመርና የትራንስፖርት ዋጋው በቀጣዩ ሣምንት ይፋ የሚደረግ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያው የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበና ድርጅቱንም አትራፊ በሚያደርግ መልኩ እንደሚተመን የተናገሩት አቶ አዲል፤ ዋጋው ከሃይገር ባስ ከፍ ያለ፣ ከታክሲ ያነሰ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
አሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክስዮን ማህበር ከአመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር የመቅረፍ አላማ አንግቦ የተቋቋመና ታዋቂ ባለሀብቶችና አርቲስቶች የሚገኙበት አክሲዮን ማህበር ነው፡፡
በአዲስ አበባ በተለይ በስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ ላይ ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም የተነሳ ነዋሪዎች ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

soldier

Soldier's Duties
·         A soldier must be loyal to his country
·         All soldiers have a moral and legal obligation or duty to obey the lawful orders of the officers and leaders appointed over them.
·         Soldiers have unique responsibilities based on rank, duty position and even geographical location. They must treat all people with respect and dignity. It is recognized that everyone has something to offer to the success of the unit.
·         Service is done without the thought of reward or recognition


በሩብ ዓመት ብቻ ከ72ሺ በላይ ዜጐች ወደ አረብ አገራት ተጉዘዋል

ከ1ሺ በላይ ህገወጥ ኤጀንሲዎች አሉ ተባለ
ባለፈው ሩብ የበጀት ዓመት ከ72 ሺ በላይ ዜጐች ወደ አረብ አገራት እንደተጓዙ ተገለፀ፡፡ 72ሺ 438 ዜጐች ወደ ሳውዲ አረቢያና ኩዌት የተላኩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 68ሺ 474 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 3ሺ 964 የሚደርሱት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስትር መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በመ/ቤቱ ተመዝግበውና ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ዜጐችን ወደተለያዩ የአረብ አገራት የሚልኩ ህጋዊ ኤጀንሲዎች ቁጥር 300 ሲደርስ ከ1ሺ በላይ በህገወጥ መንገድ ዜጐችን የሚልኩ ደላሎች አሉ፡፡
መ/ቤቱ ከተለያዩ ኤጀንሲዎች የጉዞ ፕሮሰሳቸውን አጠናቀው እና ባጅ ወስደው የመጡለትን ተጓዦች ተቀብሎ የሥራ ውላቸውን የማጽደቅና ስልጠና የመስጠት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ታህሣስ 11 ቀን 2005 ዓ.ም በመ/ቤቱ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከሃያ በላይ ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 16 ዓመት የሆኑ ህፃናት የጉዞ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ለስልጠናው ወደ ሚ/ር መ/ቤቱ መጥተው እንደተገኙ ተገልጿል፡፡
ህፃናቱ ዕድሜያቸው 26 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፓስፖርት ይዘው መገኘታቸውን የጠቆሙት አቶ ግርማ፤ ሕፃናቱ በሰውነት አቋማቸውም ሆነ በስነልቡናቸው ለሼል ዝግጁ የሆኑ አለመሆናቸው በመረጋገጡ ጉዟቸው እንዲሰረዝ ተደርጐ የማጣራት ሼል እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲዎች ከሚ/ር መ/ቤቱ ፈቃድ በሚወስዱበት ወቅት ወደ ውጪ አገር ለሼል የሚልኳቸው ዜጐች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆናቸውንና ጠያቂው አገር በሚፈልገው የዕድሜ መጠን ላይ የደረሱ መሆናቸውን በማረጋገጥ መላክ ይኖርባቸዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ከህግና አዋጅ ውጪ ህፃናት ልጆችን ወደማያውቁትና መብታቸውን ለማስከበር ወደማይችሉበት አገር ለሼል መላክ ህገወጥ አሠራር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ ተግባር በዜጐች ህይወት መቀለድ በመሆኑ ሚ/ር መ/ቤቱ አጥብቆ እንደሚቃወመውም ተናግረዋል፡፡
ህፃናቱን በመመልመል ለጉዞ ካዘጋጁአቸው ኤጀንሲዎች ጋር ግምገማ እያካሄዱ መሆኑንና ጉዳዩን በማጣራትም በቅርቡ እርምጃ እንደሚወሰድ፣ ቁጥጥሩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ግርማ ተናግረዋል፡፡
ዜጐችን ወደተለያዩ አገራት የመላኩ ተግባር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ሲሆን ባለፈው አመት ብቻ 198ሺ 667 ዜጐች ወደተለያዩ አገራት ለሼል እንደተላኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Thursday, December 20, 2012

የትያትር መግቢያ ዋጋ ጭማሪ ውዝግብ

የትያትር ባለሙያዎቸ ወደ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዳራሽ ለስብሰባ ሲገቡ
*በ15 ብር ማሳየት ለመንግሥት ትያትር ቤቶችም ያንሳል - የቢሮው ሃላፊ
*ቢሮው የግል ኢንተርፕራይዞችን ዋጋ የመተመን አግባብ የለውም - አርቲስት ገነት አጥላው
“ቁርጥ ያለ ምላሽ ስጡን፤ዋናው ማነቆ ያለው እናንተ ጋ ነው - አርቲስት ሽመልስ አበራ
በጐረቤት ሀገራት እንኳን አርቲስቶች በግል አውቶሞቢላቸው ይጓጓዛሉ እንጂ ታክሲ አይጠቀሙም የሚሉት የአገራችን የትያትር ባለሙያዎች፤እኛ ግን ስንሞት እንኳን የሬሳ ሳጥን መግዣ እየቸገረን በመዋጮ ነው የምንቀበረው ሲሉ ያማርራሉ፡፡ ባለፈው ሰሞን የትያትር ቤት መግቢያ ዋጋ ላይ የ100 ፐርሰንት ጭማሪ አድርገው ከትያትር ቤቶቹ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ተግባራዊ ሳይሆን የቀረባቸው የግል የትያትር ኢንተርፕራይዞች፤ከዘጠኝ አመት በፊት በነበረው የትያትር መግቢያ ዋጋ አሁን ማሳየት የሚሞከር አይደለም ባይ ናቸው፡፡ ከኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ የትያትር ፕሮዳክሽን ዋጋ፣ የማስታወቂያ እና ተያያዥ ወጪዎች ከእጥፍ በላይ በመናራቸው ዋጋ ሳንጨምር መስራት አንችልም ይላሉ፡፡ በነፃ ገበያ ውድድር መርህም የሕዝቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ጭማሪ አድርገን 15 ብር በሰው የነበረውን የትያትር መግቢያ 30 ብር አድርገናል ሲሉ በአዲስ አበባ አስተዳደር ሾር ላሉት ሁለት ትያትር ቤቶች እና በፌደራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሚተዳደረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ማሳወቃቸውን ይገልፃሉ፡፡ የመንግሥት አካላቱ ችግሩን እንደሚጋሩ ቢያምኑም በዚህ መልኩ ዋጋ መጨመሩን አልተቀበሉትም፡፡ በዚህም ሳቢያ በተከሰቱ አለመግባባቶች በግል ኢንተርፕራይዞች የሚታዩ ትያትሮች ተስተጓጉለዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሁሉንም ወገን የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም እንዳልሆነ ባለፈው ማክሰኞ የግል ኢንተርፕራይዞች ከመንግስት ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የትያትር ኢንተርፕራይዞችን ችግር እንደሚጋሩ የገለፁት የመንግስት ሃላፊዎች፤ ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪውን ግን አልተቀበሉትም - “ዋጋ ለመጨመር ጊዜ ያስፈልጋል” በሚል፡፡
የማክሰኞውን ስብሰባ የመሩት የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረፃድቅ ሐጐስ፤ “የዋጋ ጭማሪ የጠየቃችሁት ሥራችሁን ቀጥላችሁ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፣ ቢሮው እናንተ ከመጠየቃችሁ በፊትም ጥናት እያደረገ ነው የትያትር መግቢያ ዋጋ ከፊልም መግቢያ ዋጋ አንሷል፡፡ ከሥራው አድካሚነት አንፃር ዋጋው ከፊልም መግቢያ መብለጥ ነበረበት፤ጥያቄአችሁ ትክክለኛ ነው” ብለዋል፡፡
የትያትር መግቢያ ዋጋ 15 ብር ሲደረግ በህዝብ ተቋማት ደመወዝ ተከፍሏቸው የሚያዘጋጁ የትያትር ባለሙያዎችን እንጂ የግል የትያትር ኢንተርፕራይዞችን ታሳቢ ተደርጎ እንዳልሆነ የጠቆሙት የቢሮው ሃላፊ፤ በ15 ብር ማሳየት ለመንግሥት ትያትር ቤቶችም እንደሚያንስ ተናግረዋል፡፡
ሆኖም የግል ኢንተርፕራይዞች በእንዲህ ያለው መልኩ ዋጋ መጨመራቸው የመንግሥት ትያትር ቤቶችን አላማ እንደሚያንኮታኩት አቶ ገብረፃድቅ ገልፀዋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙት ሌላው የቢሮው ኃላፊ ደግሞ ትያትሮች ኪሳራ ላይ ናቸው የሚለው እንደማያስኬድ ጠቁመው፤ ጭማሪ ማድረግ ካስፈለገም ይሄን ማድረግ የሚችለው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ትያትር ፕሮዲዩስ አድርጐ እንዳከሰረው የተናገረው ጋዜጠኛና የማስታወቂያ ባለሙያ ሳምሶን ማሞ፤እዚህ ዋጋ አትጨምሩ እየተባለ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋጋ በመጨመር ለአንድ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ አስር ሺህ ብር ማስከፈሉ በአንድ ሀገር ሁለት ስርአት አለ ወይ ያሰኛል ብሏል፡፡ “ከያንያኑ ሲሞቱ የሬሳ ሳጥን መግዣ እንኳን የላቸውም --- አርቲስቱ ከማኪያቶ ዋጋ አንሷል” ያለው ሳምሶን፤ ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አመታት ለችግሩ መፍትሄ ባለመስጠቱ የሕዝብ አደራ አልተወጣም ያሰኛል ሲል ወቅሷል፡፡
ቢሮው የግል ኢንተርፕራይዞችን ዋጋ የመተመን አግባብ እንደሌለው የገለፀችው አርቲስት ገነት አጥላው በበኩሏ፤የመንግሥት ትያትር ቤቶች እና የግል ትያትር ኢንተርፕራይዞች የዋጋ አሀድ (Cost component) እንዲሁም የአንድ ትያትር ከሌላ ትያትር የዋጋ አሀድ አንድ አለመሆኑን ጠቅሳ፤ ብዙ ሰዎች የሚተውኑበትን ‘ሕንደኬ’ ትያትርንና አራት ወይም አምስት ሰዎች የሚተውኑበትን ሌላ ትያትር በአንድ የዋጋ ሚዛን ማየት ይቻላል ወይ በማለት ጠይቃለች፡፡ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ደግሞ የትያትር ባለሙያዎች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ ምን ይስሩ የሚል ጥያቄ ካቀረበ በኋላ “ሕዝብን ማገልገል ሌላውን ሕዝብ መበደል ነው እንዴ?” ሲል አስተያየቱን በጥያቄ ገልጿል፡፡
የመንግሥትና የግል ትያትር ኢንተርፕራይዞች በእኩል መታየት የለባቸውም ያለው አርቲስትና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ፤ የግል ኢንተርፕራይዞች ደግ አባት ስላላቸው ደመወዝ በነፃ ከሚከፈላቸው በርካታ የመንግሥት ትያትር ቤቶች ባለሙያዎች ጋር ሊነፃፀሩ አይገባም ብሏል፡፡ ትያትር በግል ፕሮዱዩስ ማድረግ እንደማያዋጣም ሲገልፅ፤ ሙስናና መጓተት ባይኖር ኖሮ የትያትር ፅሁፎችን ከግል ትያትር ኢንተርፕራይዞች ይልቅ ለመንግሥት ትያትር ቤቶች መስጠት እንደሚመርጥ ተናግሯል፡፡
በፊልምና በትያትር አዘጋጅነቱ የሚታወቀው አርቲስት ቢኒያም ወርቁ፤በትያትር መኖር እንደማይቻል እንደውም እዳ ውስጥ እንደሚከት ካብራራ በኋላ በአዲስ አበባ ትያትር ቤቶች ለግል ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡት ቀናት የተመልካች ቁጥር አናሳ የሆኑባቸው እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡
የሚቀርበው ትያትር ደረጃውን የጠበቀ ነው ወይ የሚለውን ከዋጋ ጋር ማንሳት ተገቢ ነው ያለው የኢትዮጵያ ትያትር ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚደንት አንጋፋው አርቲስት ደበሽ ተመስገን በበኩሉ፤በዚህ ስብሰባ ላይ የትያትር ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች ቢገኙ ጥሩ ነበር፡፡
ለደራሲና አዘጋጅ ቁርጥ ክፍያ ከፍሎ ትያትር ቤቱ በራሱ ዋጋ ማሳየት ይችላል ብሏል፡፡በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረፃድቅ ሀጐስ “መሰናክሎቹ ተጠንተው በጋራ ውይይት መፍትሄ እንፈልጋለን፣ የትያትር ዋጋውንም ጉዳይ ቢሆን ሰው ስጡንና በጋራ ይጠና” ያሉ ሲሆን የሃላፊውን መፍትሄ ተከትሎ የተናገረው አርቲስት ሽመልስ አበራ፤ “ቁርጥ ያለ ምላሽ ስጡን፤ዋናው ማነቆ ያለው እናንተ ጋ ነው፡፡ ትያትር ቤቶች ማቅረብ ያልቻሉትን ነው የግል ኢንተርፕራይዞች እያቀረቡ ያሉት፡፡ ትያትር ቆሟል፡፡ ገቢ ቆሟል፡፡ በዚህ እየተጐዳ ያለው መንግሥትም ጭምር ነው” ብሏል፡፣
ኃላፊው በሰጡት ምላሽም “ለማቆም እንገደዳለን ማለታችሁ ስህተት ነው፡፡ መፍትሄ እስኪገኝ በገባችሁበት ውል ቀጥሉ፡፡ ችግሩ ይሰማናል፤ ከምትሰጡን ሰዎች ጋር በአጭር ጊዜ እንወስናለን” ቢሉም ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ “አቶ ገብረፃድቅ ኮሚቴ ሳያስፈለገው ዛሬውኑ ብትወስን አርቲስቱ ዘለአለም ያመሰግንሃል” ሲል ተማፅኗል፡፡ አርቲስት ገነት አጥላውም “ይጠና ሲባል አጥኚው ማነው?” ብላ በመጠየቅ “የሚያጠኑት የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው፡፡ እኛ ጉሮሮ ላይ ተቁሟል፡፡ የዋጋ ጭማሪው አጥንተን የገባንበት ነው፤ የመንግሥት ገቢና ሕዝብ ከትያትር የሚያገኘው ጥቅም ታጥቷል” ብላለች፡፡ ከተመልካቾች መካከል ትያትሮችን ተመልክቶ ጋዜጦች ላይ በመፃፍ የሚታወቀው ዳዊት ንጉሡ ረታ “ተመጣጣኝ ክፍያ ቢኖር ጥሩ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑም ወጪ ለመቀነስ በሚል ብቻ በትያትር የሚሳተፉ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ የትያትሮችን ደረጃ እያወረደ ነው፡፡ ከመግቢያ ዋጋ ጭማሪው በኋላ ይሄ ባይቀጥል ደስ ይለኛል” ያለ ሲሆን ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ብዙነሽ ወንድሙ “የትኬት ዋጋ ቢጨምር ጥሩ ነው፡፡ የጥበብ ዋጋ ወረደ፡፡ የዋጋው መውረድ አንዳንዴ የተመልካች ቁጥር ይቀንሳል፡፡ ጥሩ ትያትር እስካየሁ ድረስ ዋጋ ተጨምሮ ከያንያን ቢጠቀሙ ደስ ይለኛል” ብላለች፡፡
በግል ኢንተርፕራይዞች የሚታዩ ትያትሮች በመቋረጣቸው ሌሎች ተመልካቾች ማግኘት አልቻልንም፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር እየታዩ ካሉ ስምንት ትያትሮች አራቱ፣ በሐገር ፍቅር ትያትር እየተዩ ካሉት ሰባት ትያትሮች ሦስቱ በአዲስ አበባ ማዘጋጀ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ከሚታዩት ሰባት ትያትሮች ስድስቱ በግል የትያትር ኢንተርፕራይዞች የቀረቡ ናቸው፡፡
የትያትር ባለሙያዎቹና የቢሮው ሃላፊዎች የማክሰኞ ውይይት ባለመግባባት ከተቋጨ በኋላ “መብታችን ሆኖ ለምንድነው የምንጠብቀው?” ያሉት አርቲስቶች ውይይቱን ለብቻቸው እንደቀጠሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Wednesday, December 19, 2012

ተቀናቃኞቹ እስራኤልና ኢራን በኤርትራ ወታደራዊ ካምፖች መሥርተዋል›› ስትራትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ

ጋዜጣው ሪፖርተር

ለረዥም ጊዜ የቆየና ሼር የሰደደ የፖለቲካ ፍጥጫ ውስጥ የሚገኙት እስራኤልና ኢራን የቀይ ባህር አካባቢን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ፉክክር ማየሉን፣ ለዚህ ፍላጐታቸውም በኤርትራ ወታደራዊ ካምፖችን ማቋቋማቸውን መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ወታደራዊ የስለላ ድርጅት ስትራትፎር ግሎባል ኢንተለጀንስ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ገለጸ፡፡ የስለላ ተቋሙ ዲፕሎማት ምንጮችን በመጥቀስ እንደገለጸው፣ እስራኤል ወታደራዊ ካምፕዋን በኤርትራ ግዛት በዳህላክ፣ በምፅዋና በአምባ ሳወራ አካባቢዎች መሥርታለች፡፡

እስራኤል በኤርትራ መሬት ላይ ወታደራዊ ካምፖቿን የመሠረተችው በቀይ ባህር አካባቢ ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመሰለል፣ በተለይም ደግሞ በአካባቢው የኢራንን እንቅስቃሴ ለመከታተል አቅዳ ነው ሲል ሪፖርቱ ይተነትናል፡፡

ኤርትራ ከእስራኤል በተጨማሪ የኢራን ወታደራዊ ካምፖችን ማስጠለሏን የሚጠቅሰው የስትራትፎር ሪፖርት፣ የእስራኤል በዚህ አካባቢ መገኘትም ኢራን በቀይ ባህርና አካባቢው የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመብለጥ በአካባቢው ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል የጦር ኃይል መገንባት መሆኑን ያስረዳል፡፡

ሮኬቶችንና የተለያዩ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን የጫኑ መርከቦች በቀይ ባህር አድርገው ወደ ሱዳን ከዚያም ወደ ግብፅ እንደሚጓዙ፣ በመቀጠልም በየብስ ወደጋዛ እንደሚያመሩ ሪፖርቱ ይጠቅሳል፡፡

ኢራን ወታደራዊ ካምፕዋን በኤርትራ ግዛት ውስጥ መመሥረቷም ባብ ኤል መንዳብ የተባለውን የቀይ ባህር ስትራቴጂካዊ ቦታና ወደ ስዊዝ ካናል የሚወስደውን የውኃ መሾመር ለመቆጣጠር ዋነኛው ወታደራዊ ፍላጐቷ መሆኑን ይገልጻል ይላል ሪፖርቱ፡፡

ኤርትራም ለሁለቱ ተቀናቃኝ አገሮች ግዛቷን በመፍቀድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጥቅም እንደምታገኝ የስትራፎር ትንተና ያስረዳል፡፡

በተለይም ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ድጋፍና የጦር መሣሪያዎችን እንዲሁም ከኢትዮጵያ በኩል ሊሰነዘርባት ከሚችል ወታደራዊ ጥቃት ራሷን ለመከላከል ይረዳት ዘንድ የአየር ኃይሏን አቅም ለማጐልበት የእስራኤልን ድጋፍ በተለዋጭነት ልትጠይቅ እንደምትችል ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም በእስራኤልና በአሜሪካ መካከል ያለውን ወዳጅነት በመጠቀም ከአሜሪካ ጋር ያላትን የተበላሸ ፖለቲካዊ ግንኙነት ማደስ ሌላኛው የኤርትራ ፍላጐት ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

እስራኤል በተለያዩ ጊዜያት የሱዳን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከአየር መምታቷን፣ ከወራት በፊት ደግሞ በካርቱም አቅራቢያ የሚገኘውን ዮርሙክ የተባለ የጦር መሣሪያ ማምረቻን ከግዛቷ ባስወነጨፈችው ሮኬት ማውደሟን የሚገልጹ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

Tuesday, December 18, 2012

ታንዛንያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ለመግዛት ጥያቄ አቀረበች

Tanzania Request to buy electric power from Ethiopian Electric Power Corporation

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 4.45 ቢሊዮን ብር ብድር ፈቀደ
በውድነህ ዘነበ

ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ጥያቄ ቀረበች፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሼል አስፈጻሚ አቶ ምሕረት ደበበ መንግሥት የታንዛንያን ጥያቄ ተቀብሎ የሽያጭ ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር ይጀምራል ብለዋል፡፡

ታንዛንያ ከኢትዮጵያ ኃይል የምታገኘው ኢትዮጵያና ኬኒያ በጋራ እየዘረጉት ካለው 433 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ መሾመር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከታንዛንያ ጋር የምትደርስበት የኃይል ሽያጭ ስምምነት በራስ ፍላጎት የሚከናወን ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ መሾመሊ በኬንያ የሚያልፍ በመሆኑ ግን ኬኒያ የተወሰነ ክፍያ ይኖራታል ሲሉ አቶ ምሕረት ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በወረቀት ላይ ገዝፎ የቆየው የምሥራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት ዕውን ወደ መሆን ቀርቧል፡፡ ኢትዮጵያን ከኬኒያ የሚያገናኘውን የኃይል መሾመር መገንባት የሚያስችለው ፕሮጀክት በርካታ የፋይናንስ ተቋማትን እየሳበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከኬኒያ ጋር የሚያገናኛትን የኤሌክትሪክ መሾመር ለመዘርጋት ከዓለም ባንክ 243 ሚሊዮን ዶላር (4.45 ቢሊዮን ብር) ብድር አግኝታለች፡፡ ይህንን የብድር ስምምነት ባለፈው ዓርብ ታህሳስ 5 ቀን 2005 ዓ.ም. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ዧንግ ዚ ቼን ተፈራርመዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሾመር ግንባታው ከደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተነስቶ ኬኒያ ድረስ የሚዘረጋ ነው፡፡ ኬኒያ የምሥራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ መረብ አካል በመሆኗ፣ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ከምሥራቅ አፍሪካ እስከ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች ጋር ያገናኛታል፡፡

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ከኬኒያ ያገናኛል ይባል እንጂ በሁለቱ አገሮች ብቻ የሚወሰን አይደለም የሚሉት አቶ ምሕረት፣ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ አገሮችን ያገናኛል፡፡ የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ አገሮችን በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመርም ያገናኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያላትን የመደራደር አቅም እንደሚያሳድግ አቶ ምሕረት ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱም ከአምስት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ ነዳጅ ለምታቀርብላት ጎረቤት ሱዳን አንቶ መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ ጀምራለች፡፡ ይህ የሙከራ ጊዜ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ሁለት መቶ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለሱዳን የምታቀርብ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከጥር ወር በኋላ በሁለቱ አገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይመረቃል፡፡

ኢትዮጵያ የኬኒያ የጠረፍ ከተማ ለሆነችው ሞያሌ መጠነኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስጠት የጀመረች ሲሆን፣ በቅርቡ የሚጀመረው የኤሌክትሪክ መሾመር ሲጠናቀቅ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬኒያ ትልካለች፡፡ ወደ ኬኒያ የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ መሾመር ግን እስከ ሁለት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ጂቡቲም 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እየላከች ነው፡፡ ከፍተኛ መጠን ኤሌክትሪክ ለጎረቤት አገሮች መላክ መጀመሯ ከአገሮቹ ጋር ያላትን የመደራደር አቅም እንደሚያሳድገው አቶ ምሕረት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኬኒያ የኤሌክትሪክ መሾመር ዝርጋታ ወጪ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፣ ለኬኒያ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ብድር ሰጥተዋል፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር

Monday, December 17, 2012

Nature of Plants



The Nature of Plants tells how plants adapt to the challenges of their habitats. Plants may live in places that provide too little rainfall, yet they thrive, either by evading drought, like the animals that live in deserts, or by tolerating the scarcity. There are plants that use other plants, climbing on them, strangling some, living in their leafy canopies, or parasitizing them. And The Nature of Plants explores the love-hate relationships that plants have with animals, some feeding on plants but others drawn into serving plants by pollinating them, scattering their fruits and seeds, or being eaten themselves.

Giant Tea pot Topiary