በሲዳማ ዞን ጉርቺ ወረዳ ሃይሳ ባራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ትእግስት ዮሃንስ በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን ተገላገሉ ፡፡
ወይዘሮዋ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ ፥ ምጥ ሲጀምራቸዉ በአከባቢያቸው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በማምራት አንድ ልጅ ከተገላገሉ በኋላ በድጋሚ በይርጋለም ሆስፒታል ቀሪዎቹን አራት ልጆች ተገላግለዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት ላይ አምስቱም ልጆች በጥሩ ጤንነት ላይ መሆናቸውን ነው የህክምና ባለሞያዎች የተናገሩት፡፡ ልጆቹ ከአንድ ኪሎ ግራም በታች ክብደት ሲኖራቸዉ አምስቱም ሴቶች ናቸው ፡፡
ከግማሽ ሚሊየን እርግዝናዎች መካከል በአንዱ ይህ አይነት ሁኔታ እንደሚከሰትም ነዉ የህክምና ባለሞያዎች የሚናገሩት ፡፡
No comments:
Post a Comment