Search

Wednesday, April 24, 2013

የኢትዮጵያ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የበረራ ማረጋገጫ አገኙ

ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን አቁሞት የነበረውን በረራ በቅርቡ እንደሚጀምር የቦይንግ ኩባንያ አስታወቀ።
የድርጅቱ የኢንጅነሪንግ እና የማርኬቲንግ ክፍል የስራ ሃላፊዎች በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ ኩባንያው በአንዳንድ ድሪምላይነር አውሮፕላኖቹ ላይ ተከስቶ የነበረውን ችግር የቴክኒክ ቡድን በማቋቋም ከፈተሸ በኋላ ለበረራ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጧል።
አለም አቀፉ የበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲም አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ ጥሎት የነበረውን ጊዜያዊ እገዳ አንስቷል።
ባለፈው የካቲት ወር ላይ የጃፓን ዓየር መንገድ በሆኑ  ቦይንግ 787 አውሮፕላኖች ላይ ፥ ከጭስ ማውጫና  ባትሪ ጋር በተያያዘ ባጋጠማቸው የቴክኒክ ችግር  በመላው ዓለም  የሚገኙ  ተመሳሳይ አውሮፕላኖች ከበረራ ታግደው ነበር ።
የቦይንግ  ኩባንያ  ቴክኒሽያኖች ሰሞኑን  ወደ አዲስ አበባ  በመምጣት ለኢትዮጵያ  ዓየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ምርመራና ጥገና  ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ከምርመራና ጥገና  በኋላም አውሮፕላኖቹ ለበረራ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የቴክኒክ ቡድኑ ያረጋገጠው ።
የኢትዮጵያ  ዓየር መንገድ  ያሉት  ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በረራ የሚጀምሩበትን ጊዜ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ የድርጅቱ የስራ ሃላፊዎች ተናግረዋል።

በሞላልኝ ከሳቴብርሃን

No comments:

Post a Comment