Search

Friday, April 17, 2015

የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ? አጀንዳውም (ርእሰጉዳዩም) ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ወሲባዊ፣ ባሕላዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሰብአዊ፣ ሞራላዊ (ግብረገባዊ) መሆኑ ሲረጋገጥ፡፡

አጀንዳውም (ርእሰጉዳዩም) ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ወሲባዊ፣ ባሕላዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሰብአዊ፣ ሞራላዊ (ግብረገባዊ) መሆኑ ሲረጋገጥ፡፡
Stop-FGM
ጥናታዊ ጽሑፍ!
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አንዳች ጥናት ቢጤ ማድረጌን አምና በግብረ ሰዶማዊያን ጉዳይ ላይ በጻፍኩት ጽሑፍ ሳይቸግረኝ ጠቆም በማድረጌ ብዙኃን መገናኛዎችን የሚከታተሉ ሰዎች በኢሜይልና በስልክ በአካልም ጭምር በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀሁትን ጥናታዊ ጽሑፍ ለንባብ እንዳበቃላቸው እጅግ ወተወቱኝ፤ አይ ረጅም ነው ለመጽሐፍ እንጅ ለዚህ ዓይነት መስተንግዶ አይሆንም ረዘመ ትላላቹህ ብልም ሊቀበሉኝ አልቻሉም ጨቀጨቁኝ እንግዲህ ካልተውኝ ምን አደርጋለሁ ብየ አቀራረቡን ግን ለብዙኃን መገናኛ በሚሆን ቀየርኩትና ተዛማጅ የሆነ ጠቃሚና አስፈላጊ ጉጋይ አክየበት ጽፌላቹሀለሁ ያውላቹህ፡-
ይሄንን ጥናት ያደረኩት ከስድስትና ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በዚህ ጥናት ከ800 ያላነሱ ሰዎች በቀጥታ በሽዎች የሚቆጠሩ በተዘዋዋሪ የጥናቴ ግብአት በማድረግ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ጥናቴን እንደጨረስኩ ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ ወደ ሚመለከታቸው የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቀርቤ የጥናቴን ውጤት በማስረዳት በብዙኃን መገናኛ በጉዳዩ ላይ እየሠሩ ካሉ ባለሙያዎች ጋር በክርክር መልክ ለሕዝብ የሚቀርብበትን መድረክ ስጠይቅ “መንግሥት” አቋም የያዘበት ጉዳይ ስለሆነ አይቻልም፡፡ የሚል ዝግና ለጥናትና ምርምር ዕድል የማይሰጥ ያልበሰለ አቋም በመያዙ ምክንያት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ሳልችል ቀርቸ ቆየሁ፡፡ በጥናቱ የደረስኩበት እውነታና ያለእውቀት እያደር እየተፈጠረ ያለው ጉዳይ ከባድ ሥጋት ላይ ስለጣለኝ ቢያንስ በሕትመትና በመካነ ድር የብዙኃን መገናኛዎች ጉዳዩን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁትም ነው እነሆ፡-
ጥናቱን ለማድረግ ያነሣሱኝና ምክንያት የሆኑኝ ጉዳዮች፡-
በየብዙኃን መገናኛውና በግል ውይይት ከጎልማሳነት እስከ ሽምግልና የዕድሜ ደረጃ ያሉ ሰዎች ሲያወሩ እንደምንሰማው ‹‹አየ በእኛ ጊዜማ!›› እያሉ ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ በሚል ቅኝት በዘመናቸው የነበረውን የወጣትነት ሕይዎት ሲያወጉ የነበራቸው ሥነ-ሥርዓት፣ ሥነ-ምግባርና ግብረ-ገብነት፤ የፍቅር ጓደኝነት (ከንፈር ወዳጅነት) ቢመሠርቱም እንኳ ወሲብ እስከመፈጸም የማይደርስና ከወሲብ በመለስ የተገደበ ቁጥብነት የሰፈነበትና ኃላፊነት የተሞላበትን የጉርምስና ሕይዎት አሁን ካለው መረን የለቀቀ ከነበረው ፍጹም የራቀ የወጣትነት ሕይዎት ጋር ሳነጻጽር ይሄንን ለውጥ ምን ሊያመጣው ቻለ? ብየ እራሴ ስጠይቅ፡፡ ይሄንን አንድ ባሉልኝ፡፡
ሌላው ደግሞ ቀደም ሲል ሙሽራው ሙሽሪት ተብለው ተድረው ሙሽሮቹ ደናግላን መሆናቸው የሚያጠራጥር አይሆንም ነበር፡፡ ምንም እንኳ ከስንት አንድ በተለያየ ምክንያት ልጃገረድ ያልሆነች ቢያጋጥምም ቅሉ፤ በአንጻሩ አሁን አሁን ግን እግዚአብሔር ልጃገረድ መፍጠር አቆመ እንዴ? እስኪባል ድረስ ልጃገረድና ድንግል ሙሽሮች ማግኘት ነዳጅ በሀገራችን ፈልጎ የማግኘትን ያህል ከባድና አስቸጋሪ ሆኖ ቁጭ ማለቱ እንዴ! ጭራሽ ማኅበራዊ ሕይዎታችን እየተሸረሸረና ግለኝነት እየተስፋፋ ጎረቤት ከጎርቤት ጋር እንኳ አብሮ እየኖረ የማይተዋወቅ እስከመሆን የደረሰ መሰብሰብና መራራቅ መከተት በተፈጠረበት ዘመን? እንደቀድሞው መቀራረቡ፣ አብሮ መብላት መጠጣቱ፣ መጫወት መደባደቡ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆች ርቀው የሚሄዱበት ጉዳይ ሲያጋጥምም  ጎረቤትን አምኖ ልጆችን ለጎረቤት አደራ ጥሎ በማይኬድበት ዘመን? በተለያዩ የማኅበራዊ ሕይዎት ኩነቶች የጎረቤት ልጆችን ባሳተፈ መልኩ በመረዳዳት በመተጋገዝ በማይከወንበት ዘመን? ጋፍኛ (የተገላቢጦሽ) ለዚህ የማያጋልጥ ከፍተት ሳይኖር እንዴት እንዲህ ዓይነት ችግር ሊያጋጥም ቻለ? ሁለት አትሉልኝም?
ሌላው ትንሽ ከበድ የሚለውና አሳዛኙ ነገር ሴት ለአቅመ ሔዋን ደረሰች ከሚባልበት የዕድሜ ክልል በጣም በቀደመ የእድሜ ዘመን የወላጅን ምክርና ማስፈራሪያ፣ የዘመኑንም አደጋ ወደ ጎን በመተው ክብረ ንጽሕናቸውን የትም በሜዳ የሚጥሉና ለመጣልም የሚቋምጡ ሕፃናት እኅትና ልጆቻችን ቁጥር በርካታውን እጅ እየያዘ መምጣቱና በብዙኃን መገናኛዎች ከሚደመጡ መረጃዎች እየሰማነው እንዳለውም በ12 እና 13 ዓመት ዕድሜ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ሆን ብለው እየተጣሉ እየወጡ የዝሙት ተዳዳሪነትን ሕይዎት እየተቀላቀሉ ያሉ ሕፃናት ቁጥር አስደንጋጭ በሆነ አኀዝ እየጨመረ መሆኑና ተጣልተው የሚወጡበት ምክንያትም ለዚያ የሚያበቃ ሆኖ አለመገኘቱ የፈጠረብኝ ጥያቄ፡፡ ሦስት አላቹህ?፡፡
ሌላ ደግሞ ልጨምርላቹህ ቀድሞ የማይሰማ የማይታይ የነበረ፤ መቸም ሁሉም በምንም ነገር ላይ አንድ አይሆንምና ከተሰማም አልፎ አልፎ ከስንት አንድ በተለያዩ ምክንያቶች ይፈጸም የነበረው ለጊዜው የወንዱን ትተነው ምክንያቱም ባሕላችን ሴትን ልጅ የክብር መገለጫ ያደረገ ከመሆኑም በላይ በሴት ልጅ የሚደርስ ችግር ጠባሳው ወይም ችግሩ ሕይዎቷን ለዘለቄታው ችግር ላይ ይጥላልና  ከዚህም አንጻር ባሕላችን ከወንድ ልጅ ይልቅ ሴትን በብዙ አጥርና ጫና ያጠረ ያሠረ በመሆኑ ቀደም ሲል ሴቶች ያደርጉታል ተብሎ የማይታሰብ የነበረው የሴቶች ለትዳር ታማኝ ያለመሆን ችግር ዛሬ ዛሬ ግን የተለመደና ‹‹ታዲያ ምን አዲስ ነገር አለው?›› በማለት ጭራሽ ዓይናቸውን የሚያፈጡበት ዘመን መሆኑ ሃይማኖት፣ ባሕልና ወግ፣ ግላዊና ቤተሰባዊ ክብር ይህ እንዳይፈጸም ከማድረግ አኳያ የነበራቸው ተሰሚነትና የመፈራት ሞገሥ ዋጋ እያጡ እየተዘነጉ እየተናቁ ጨርሶም ያላቸውን አስተዋጽኦም ሆነ በጎ ተጽዕኖን ማሰብ ያለመፈለግ ሁኔታ በጣም ጎልቶ እየታየ መሆኑ፡፡ ይሄ ስንተኛው ነው? አዎ አራተኛ
የመጨረሻው ደግሞ ያላገቡ ሴቶችን ያየን እንደሆነ ከፊሎቹ ወሲብ ማለት ከክብር፣ ከሰብእና፣ ከማንነት፣ ከብስለት፣ ከግብረገብ፣ ከሥነ ምግባር፣ ከንጽሕናና ከብዙ ዋጋ ከሚሰጣቸው ካላቸውም እሴቶች ጋር የተሳሰረ ወይም የሚገናኝ ሆኖ ሳለ እነዚህን እሴቶች ከእቁብ ባለመጣፍ ባለመቁጠር ወይም ዋጋ ቢስ ከንቱ በማድረግ ልክ ለሰላምታ ሰው የመጨበጥን ያህል እጅግ አቅሎ በማየት ብቻ ይመራቸው እንጅ ስሙን እንኳን ከማያውቁት ሰው ጋር የሚተኙ ወይም ወሲብ የሚፈጽሙ እየሆኑ መምጣታቸው የሚሉት ናቸው፡፡
እናም እነዚህ 5 ነጥቦች ለማኅበረሰባችን አዳዲስ የሆኑ ችግሮች ቀድሞ ያልነበሩ ከሆኑ አሁን ምን አምጥቶ ዘረገፋቸው? የሚል ጥያቄ ለራሴ በማንሣት ነገሩን በጥንቃቄና በአጽንኦት ጊዜዬን ወስጀ መመርመር ተያያዝኩት ፡፡ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ አራት ዋና ዋና ነጥቦችን ማስታዎሻዬ ላይ አሠፈርኩ፡፡ እያንዳንዳቸውን በጥልቀት በምመረምርበት ጊዜ አንዱ መንስኤ ብቻውን ከላይ ለዘርዘርኳቸው ችግሮች ከፍተኛውንና ቁልፉን ድርሻ ይዞ አገኘሁት፡፡ ይሄ መሆኑም አስደነገጠኝ ልደነግጥ የቻልኩበት ዋነኛው ምክንያት እስከዛሬ ድረስ በማኅበረሰባችን እነኝህ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ማኅበረሰቡን ይዞ ለሚጓዘው ባቡር (ሰደዴ) ፍሬን ሆኖ ያገለግል የነበረውን መሣሪያ ጎጅ ነው ብሎ መላው ዓለም ሕግና ሥርዓት ቀርፆ እያወገዘውና እየተከላከለው መሆኑ ነበር፡፡ ጎጅ ነው ተብሎ እንዲቀር ከተደረገ በኋላ ግን እየተፈጠረ ያለውን ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ ስንመለከተውና በዚህ ከቀጠለም ከሁለትና ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት በኋላ ሊፈጠር የሚችለው ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ ሀገርን እንደ ሀገር ማስቀጠል እንዳይቻል ሊያደርግ እንደሚችል በግልጽ የሚታይ ሆኖ መገኘቱ እንደ ዜጋ በድንጋጤዬ ላይ ጭራሽ ጭንቀትም ጨምሮ አመጣብኝና ዕረፍት እንዳጣ መተንፈሻ እንድፈልግ የዜግነት ግዴታየ እንደሆነ እንዳምን አስገደደኝ፡፡
ልብ ብሎ ላላየና አርቆ ላላሰብ ሰው ይህንን ሥጋቴን አካብጀ እንዳቀረብኩት ያስብ ይሆናል፡፡ እኔ ይህ ሰው እንዲህ በማሰቡ ለመረዳት እራሱን እስካዘጋጀ ጊዜ ድረስ ችግር ነው ብየ አልወስደውም፡፡ ቀስ በቀስ እየሞቀ በሚሔድ ውኃ ውስጥ ያለች እንቁራሪት ውኃው እንደ እሳተ ጎመራ እየተገለባበጠ እስኪፈላ ድረስ መፍላቱ ወይም ማቃጠሉ ሳይታወቃት ፍላቱ አፈንድቶ ለሞት እንደሚያበቃት ሁሉ አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው ለውጥም በአንድ ጀንበር ጨልሞ ሲነጋ ዓይተን የምንረዳው ሳይሆን እንደ ውኃው ፍላት ቀስ በቀስ እያላመደን የሚሞቅ በመሆኑ ይህ ጠባዩም እየጨመረ የመጣውን ግለቱን እንዳንረዳው የማድረግ ባሕርይ ስላለው እስኪያጠፋን ድረስ ያለንበትን አደገኛ ሁኔታ ከነበርበት ጋር የማመዛዘንና የማጋናዘብ አደገኛውንም ለውጥ ተረድተን የመንቃት ዕድል ሳይሰጠን ድንገት ያጠፋናል ወይም ከፍጻሜያችን ጋር ያፋጥጠናል፡፡ ይሄንን ሀቅ ለመረዳት አሁን ያለንበትን ሁኔታ ቀድሞ ከነበርንበት ጋር በማነጻጸር የግለቱ መጠንም ምንም ያህል እንዳልተሰማን ማየቱ በቂ መረጃ ነው፡፡
የችግሩን ክብደት በጨረፍታ ለማሳየት ያህል በዚህ ችግር መንስኤነት ምክንያት በኤድስ የሚያልቀውንና ሊያልቅ የሚችለውን ወገን ትተን የዛሬ ዘመን ትዳሮች በውስጣቸው የቱንም ያህል ችግርና በደል ቢኖርም እንኳ እንደቀድሞ ዘመን ትዳሮች ከራስ በላይ ለማኅበራዊው መዋቅራችን አልፎም ለሀገር በማሰብ ሁሉንም ችሎ በማሳለፍ በትዳራቸው እንደ ጸኑ ፍጹም የተረጋጉ መስለው ልጆቻቸውን አሳድገው ለቁም ነገር ከማብቃት አልፎ አስከ ሕልፈታቸው የመቆየት ጽናት ትዕግስት ማስተዋልና ኃላፊነት ጨርሶ የሌላቸው በትዳር ውስጥ አግባብ ያልሆነና የማይመከር የየግል ጥቅም ብቻ የሰፈነባቸው ሆነዋል፡፡ እንደኔ እንደኔ የቀደምቶቹ ትዳሮች ውሳኔ ትክክለኛና ምንም አማራጭ የሌለው ውሳኔ ነው፡፡ ምክንያቱም ተወደደም ተጠላ በትዳር ውስጥ ቀላልም ይሁን ከባድ ግጭትና አለመግባባት መፈጠሩ አይቀርምና፤ ተፈጥሯዊም ነውና፡፡ ሰው እንኳን ከሌላ ጋር ከራሱም ጋር እንኳን ቢሆን በቀን ውስጥ ስንት ጊዜ ይጋጫል ይጣላል፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ከራሱ ጋር መግባባት አቅቶት ብዙ ጊዜ በብዙ ጉዳዮች ላይ ለውሳኔ ሳይበቃ የሚቀርበት በርካታ አጋጣሚዎች አሉና፤ ባስ ሲልም ይሄንን መፍታት ሲያቅተው ራሱን እስከማጥፋት የሚደርሰው ስንት አለና፡፡ በመሆኑም በውኃ ከጠነ በሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ግጭቶች ከባድም ቢሆኑ ትዳርን ለማፍረስ መብቃት የለባቸውም እንዳመጣጡ ተቀብለን እንኖራለን ብለው የቀድሞ ትዳሮች ከችግራቸው ጋራ ባለማፍረስ መጽናታቸው እጅግ የበሰለና ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንፃርም እጅግ ኃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ ነው ብየ አምናለሁ፡፡
የአሁን ዘመን ትዳር ግን በዚህ ከላይ ዋነኛውን ድርሻ ይዟል ባልኩት ችግር መንስኤነት እንደ ቀድሞዎቹ ትዳሮች ምንም ዓይነት ችግር በመሀከላቸው ቢፈጠር በበሰለ የመቻቻል ባሕል ዋጥ እያደረጉና ከባዶ፣ ከምንም ወይም ከከፋው የሚሻለውን በመምረጥ በቀሪ ጉዳይ ላይ መግባባትን ፈጥረው ልጆችን የወላጅ ፍቅር ሳያጡ በጋራ አሳድጎ ለቁም ነገር ማብቃት ለሀገር ካለው ጥቅም አንፃር ያለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ባለመገንዘብ ወይም ለመገንዘብ ባለመፈለግ በውኃ ቀጠነ ልጆችን በትነው ትዳር ለማፍረስ የተገደዱ እንዲሆኑ ካደረጋቸው፤ በዚህም ምክንያት ሀገር ተረካቢ የሆነ ብቁ ትውልድን ማግኘት የማይችል ከሆነ፤ ምክንያቱም የሥነ-ልቡና ባለሙያዎች የወላጅ ፍቅር ሳያገኙ ወይም ከሚበጠበጥና ከሚታወክ ወይም ከፈረሰ ትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ልጆች ሰብእናቸው የተሟላና የተረጋጉ ሆነው የመገኘት ዕድል በጣም የመነመነ ነው ይላሉና፡፡ እናም በዚህ ችግር መንስኤነት ምክንያት እንዲህ ዓይነት ተረካቢ ትውልድ የሌላት ሀገር ከሆነች ወይም ደግሞ ችግሩ በሚፈጥረው የአመንዝራነት  ጠባይ በአመንዝራ ትውልድ የተሞላች ሀገር ከሆነች ልብ በሉ አመንዝራነት ብቻውን የሚመጣና የሚኖር ማኅበራዊ ቀውስ ወይም ችግር አይደለም አዳብሎ የሚይዛቸው በርካታ አደገኛ ችግሮችንም ጨምሮ ይይዛል እናም በዚህ ዓይነት ትውልድ የተሞላች ሀገር ከሆነች እንዴትም ሆና በሀገርነት ልትቀጥል የምትችልበትን ዕድል አታገኝም ማለት መሆኑ አይደለምን?
በተደጋጋሚ የምንሰማው ተአማኒነትም ያለው አንድ ጥሩ አባባል አለ ‹‹ቤተሰብ የሀገርና የማኅበረሰብ መሠረት ነው›› የሚል፡፡ ይሄንን ነው እያልኩ ያላሁት፡፡ የበሰለ የግጭት አፈታት ዘዴን ያወቁ፣ ፍቅር መተማመንና መተሳሰብ ያለበት ሰላማዊና ደስተኛ ትዳር ወይም ቤተሰብ በትክክልም ይህ ቤተሰብ ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚሆኑ ልጆችን ስለሚያፈራ የሀገር መሠረት ነው፡፡ ሁላችንም በግልጽ እንደምንረዳው ዋነኛውን ድርሻ ያዘ ያልኩት መንስኤ ግን አንዲህ ዓይነት ትዳር ወይም ቤተሰብ እንዳይኖር ካደረገ ውጤቱ የዛኑ ያህል ሊሆን እንደሚችል በጣም ግልጽ ነገር ነው፡፡ ይሄንን መረዳት የማይችል ጭንቅላት ያለው ሰው ይኖራል ብየም አላስብም፡፡
አራቱ  መንስኤዎች ምን ምን ናቸው?
  1. የቀደመውንና ምስጉኑን ትውልድ ለመቅረጽ አብቅቶ የነበረው የግብረ ገብ ትምህርት በቀድሞው ይዘት ዓይነት ነገር ግን ይህ ዘመን በሚጠይቀው መግባባት መልኩ ባሕልን፣ የሃይማኖቶች የጋራ የሆኑ መልካም የሥነ-ምግባር አስተሳሰቦችን፣ የሞራል(የግብረ-ገብ) ድንጋጌዎችን ባቀናጀ መልኩ የግብረ ገብ ትምህርት አለመሰጠቱ፡፡
  2. ትውልዱ በሉላዊነት(Globalization) ምክንያት ‹‹ለዘመናዊነት›› እና ለምዕራባዊያን ባሕል ተጋላጭ መሆኑና የራሱን ባሕል አስተሳሰብ የኑሮ ዘይቤ ትቶ ያንን የምዕራባዊያኑን ባሕል አስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ በተሳሳተ አረዳድ በመያዙ፡፡
  3. ከዚህ ትውልድ በፊት የነበሩትን ትውልዶቻችንን ሥርዓት ባለው መንገድ ለመምራት ቁልፍ ሚናና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው እናት አባቶቻችን የሚያወሩለትና ባሕል አድርገው ይዘውት የነበሩት የሴት “ልጅ ግርዛት” ጎጅ ልማድ ተብሎ እንዲቀር መደረጉ፡፡
  4. በሥነ-ልቡና ሳይንስ (መጣቅ) ትምህርት ውስጥ እንዳለ የሚነገረው ፀረ-ማኅበረሰባዊ የሰብእና ዓይነት ያላቸው ግለሰቦች መበራከታቸውና ይሄንኑ ክፉ የውስጥ ስሜታቸውን ለማርካት ባሉበት ወይም ባገኙት ሥልጣን ኃላፊነት የሥራ ድርሻ ቦታ ሁሉ ማኅበረሰቡን ለመጉዳት ለማጥፋት በሠሩትና በሚሠሩት የጥፋት ሥራ ምክንያት፡፡
የሚሉት ሲሆኑ  ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ ያገኘሁት ግን በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ማለትም ‹‹ግርዛት›› የሴት ልጅ ግርዛት ልብ በሉ እያልኩ ያለሁት “የሴት ልጅ ግርዛት” (woman’s circumcision) እንጅ የሴት ልጅ ብልት ትልተላ (genital mutilation) አይደለም፡፡ ሦስት የግርዛት ዓይነቶች አሉ፡፡ ሁለቱ የግርዛት ዓይነቶች ማለትም በሴት ልጅ ብልት ላይ ከፍ ብሎ ከወደ አናቱ ያለውን አፍንጫ መሰል የሴት ልጅ የብልት አካል (በእርግጥ እንደየ ሴቱ የተለያየ ቅርጽና መጠጥ አለው) ብቻ ለማለት  የፈለኩት የብልት አካል የቱ እንደሆነ ይገባቹሀል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ይሄንን የብልት አካል መቁረጥ አንዱ ዓይነት ሲሆን ሁለተኛው የግርዛት ዓይነት ደግሞ በሴት ልጅ ብልት የውጭና የውስጥ ከንፈር መሰል ነገር አለ የውስጠኛው ‹‹ቂንጥር›› በመባል ይታወቃል ይህ የብልት አካል ከላይ ከአፍንጫው ወይም ሙሽራም ይባላል ከሱ ጀምሮ እስከ ታች ወርዶ በሁሉም ሴቶች ላይም ባይሆን በከፊሎቹ የማኅፀን አፍንም ይዞራል፡፡ ይህንን የብልት ክፍል የማኅፀን አፍ አካባቢ ያለውን ትቶ ከፍ ይልና አሁንም አፍንጫው (ሙሽራው) አካባቢ ያለውን ትቶ መሀል ላይ ያለውን የሚያነሡበት የግርዛት ዓይነት ነው፡፡ እነኝህ ሁለቱ የግርዛት ዓይነቶች በደጋው የሀገራችን ክፍልና በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ የሚፈጸሙ ሲሆኑ ሦስተኛው የግርዛት ዓይነት ግን ባለሙያዎች ይህንን ግርዛት ሳይሆን የብልት ትልተላ (Genital mutilation) የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል  አፈጻጸሙም የሴትን ልጅ  የብልት አካል እንዳለ ጠርጎ በማንሣት ለሽንት መውጫ ትንሽ ቀዳዳ ትቶ ገጥሞ እንደ ጨርቅ የሚሰፋበት  የግርዛት ዓይነት  ደግሞ በቆላማው የሀገራችን ክፍልና በሙስሊም ማኅበረሰብ የሚፈጸም በማለት ይለዩታል፡፡ ትንሽ አሰቃቂና ዘግናኝም ነው፡፡
እንግዲህ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ በዝርዝርና በጥልቀት እንወያያለን በጉዳዩ ላይ የሚነሡትን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ጥቅምና ጉዳቶችን አንድም ሳናስቀር እንፈትሻለን በጥሞና እንድትከታተሉኝ አደራ እላለሁ፡፡ ነገር ግን ላስጠነቅቃቹህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ጉዳዩ የመራቢያ ወይም የወሲብ አካልን የሚመለከት እንደመሆኑ መጠን ከላይ እየሞካከረኝ እንደመጣሁ ሁሉ ከተለመደው ንግግራችን ወጣ ያሉና ከበድ የሚሉ አገላለፆች ስለምጠቀም እንዲሁም ርእሰ ጉዳዩ ነገሮችን ግልጽ አድርጎ ከማስረዳት አንጻር አንዳንድ ነገሮችን በግልጽ ለመናገር ግድ ስለሚል በግልጽ ለምናገራቸው አነጋገሮችም ሆነ ለመናገር ለሚከብዱት ቃላት አስቀድሜ ይቅርታቹህን እለምናለሁ፡፡
ጉዳዩ እንዲህ እንደወረደ መጻፍ የሚያስከፋቸው ወገኖች መኖራቸው አይቀርምና እባካቹህ ጉዳዩ እንዲህ ባለ ሁኔታ ተፍረጥርጦ እውነቱ መጻፍ ስላለበትና ካለው አደጋ አንጻር ግንዛቤን ለማስጨበጥ ሲባል ግድ ስለሚል ነውና ለድፍረቴና ምናልባትም ለብልግናየ ይቅርታቹህን እንዳትነፍጉኝ አደራ፡፡
የሴት ልጅ ግርዛትን ጎጅ ባሕል (ልማድ) የሚሉት እነማን ናቸው?
ሲጀመር ግርዛትን ሕገወጥ የማድረግ ሐሳቡ ሀገር በቀል አይደለም ምዕራባዊያኑ ናቸው በእኛ እናውቅልሀለን አምተው የጫኑብን ችግሩ ከዚህ ይጀምራል፡፡ አንድ ማኅበረሰብ በረጅም የጊዜ ሂደት ለአኗኗሩ የሚስማማ ሥርዓትን ነገሮችን ደጋግሞ በመሞከር ይጠቅመኛል የሚለውን በመውሰድ የማይጠቅመውን በመተው ከባድና ውስብስብ ሒደት (by trial and error) መንገድ የራሱን ባሕል ለራሱ በሚስማማው ችግሬን ይቀርፍልኛል ባለው መንገድ ይቀርፃል፡፡ ምናልባትም የዚህ ማኅበረሰብ ባሕል በሌሎቹ ዓይን ሲታይ ከባሕሎቹ አንዳንዶቹ በጣም ስሕተት ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ የሚገርማቹህ ግን ያ ከሩቁ የሚያሽሟጥጠውን ማኅበረሰብና ተሸሟጣጩን ማኅበረሰብ የመኖሪያ ቦታቸውን ብታቀያይሯቸው አሽሟጣጩ የተሸሟጣጩን መንገድ በመከተል ወይም ያንኑ በመድገም  አሽሟጣጮቹ ተሸሟጣጭ ተሸሟጣጮቹ ደግሞ አሽሟጣጭ ሆነው ታገኟቸዋላቹህ፡፡ እንዴት አረጋገጥክ? እንደምትሉ እገምታለሁ ወደ ኋላ ግልጽ ይሆንላቹሀልና እናንተ ብቻ በጥሞና ተከታተሉኝ፡፡
ባሕል ማለት ምን ማለት ነው? ልማድስ?
ባሕል ማለት የአባባል የአስተሳሰብ የኑሮ ስልት ዘይቤ ማለት ነው፡፡ ግሱ ብህለ ሲሆን ትርጉሙም አለ ተናገረ ማለት ነው፡፡ የዓለማችን ሊቃውንት ባሕል ለሚለው ቃል ፍች ሲሰጡ ምን ይላሉ ‹‹ባሕል ማለት የአስተሳሰብ መንገድ (the way of thinking)›› ነው ይላሉ በእርግጥም በአጭሩ እናስቀምጠው ከተባለ ከዚህ የተለየ ትርጉም መስጠት ይከብዳል፡፡ የሆነ ሆኖ እኔ የሚመስለኝና የማምንበት ግን ባሕል ማለት ‹‹አንድ ማኅበረሰብ በሚኖርበት የአየር ንብረትና የመልክአ ምድር ሁኔታ በመገደድ በሰብአዊና ሞራላዊ (ግብረገባዊ) አመለካከቱ ምክንያት ከሂደቶችና ከተሞክሮዎች በኋላ በስምምነት ቀርፆ ይሁን ይደረግ ብሎ የሚቀበለው ጠቃሚ የጋራ አስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ ማለት ነው›› አንዳንዴም ሃይማኖት ባሕልን የመቅረጽ ትልቅ ድርሻ ሲይዝ ይስተዋላል፡፡ እንደዚያውም ሁሉ ባሕልም በሃይማኖት ላይ ጠንካራ ተጽዕኖውን አሳልፎማየት የሚችልበት አጋጣሚ ተስተውሏል እርስ በርሳቸው ተጽዕኖ  ይደራረጋሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ፍቺ ወይም ትርጉም በባሕል ስም ያሉ ልማዶችን አያካትትም ብዙ ጊዜም እነኝህ ልማዶች የባሕል አካል ተደርገው እንዲቆተሩ የሚደረጉትም በተጽዕኖ ወይም በአስገዳጅ ሁኔታ ነው፡፡ ተጽእኖ አድራጊው ገዥ ወይም የጎሳ መሪ በተለይም ደግሞ የሃይማኖትን ወይም ሌላ የተደማጭነትን ቦታ የያዘ አካል ሊሆን ይችላል፡፡ ያለውን ሥልጣን በሉት የፈለገውን የሚያደርግበትን መብት ተጠቅሞ የግሉን አስተሳሰብና ፍላጎት ነገር ግን ለማኅበረሰቡ ጠቃሚነቱንና እውነትነቱን እንዲፈትሸውና እንዲያረጋግጠው ዕድል ሳይሰጥ በተጽዕኖ ተቀብሎት እንዲኖረው የሚገደድበት በርካታ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ኅብረተሰቡም አማራጭ ከማጣት የተነሣ ተቀብሎት ይኖርበታል፡፡ ወዲያውም የባሕሉ አካል አድርጎት ቁጭ ይላል፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን ዐሥር ሊቃውንት አይነቅሉትም እንደሚባለውም ከዚያ በኋላ ያንን ማኅበረሰብ እንደ ባሕል አድርጎ የወሰደውን ልማድ ማስተው ከባድ ይሆናል፡፡ የእነዚህ ተጽዕኖ አድራጊ ግለሰቦች አስተሳሰቦች ብዙ ጊዜ ለዚያ ማኅበረሰብ ጠቃሚነት የላቸውም እጅግ ጎጂ የሚሆንበት አጋጣሚም ብዙ ነው፡፡ ሲጀመርም እነዚህ ግለሰቦች ያንን የሚያደርጉበት ምክንያት የሥልጣናቸውን ኃይል ለመፈተሽና ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡም ምን ያህል ቃሌን ይቀበላል፣ ይታዘዝልኛል የሚለውን ለመገመት ለመገምገም ሲሉ ያደርጉታል እንጅ ብዙውን ጊዜ እራሳቸውም ቢሆኑ በሕዝባቸው ላይ የጫኑትን አስተሳሰብ ወይም ልማድ አይቀበሉትም  ወይም አይኖሩበትም፡፡ ከዘመናት በኋላ ግን በዚያ ልማድ የሚነቀፈውና የሚዘለፈው ያለ በደሉ ማኅበረሰቡ ወይም ሕዝቡ ይሆናል፡፡
ባሕልን ከልማድ እንዴት መለየት ይቻላል?
ልማድን ከባሕል ለመለየት የሚያስችላቹህን ቀላል የሆነ መንገድ ልንገራቹህ ፡፡ ባሕል ነፃና አመዛዛኝ ሕሊና ባለው ማንኛውም ሰው ሲመዘን ሁል ጊዜም ትክክልና አመክንዮአዊም ሆኖ ይገኛል፡፡ ልማድ ግን በተቃራኒው ነው ሁል ጊዜም አመክንዮአዊ አይሆንም  ለመጠየቅ ለመፈተሸ ለመመርመርም አይፈቅድም በሩ ዝግ ነው፡፡ ሁልጊዜ ከአጠቃላይ እውነታ (general truth) ጋር ይጋጫል ጎጅ እንጅ ጠቃሚም አይሆንም፡፡ በመሆኑም በቀላሉ በማንኛውም ሰው ሲመዘን የሚተች የሚነቀፍ የሚወገዝ ሆኖ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በዓለማችን አንዳንድ ጎሳዎች በርከት ያሉ ለመፈጸም አይደለም ለማሰብ የሚከብዱ በባሕል ስም ያሉ ልማዶች አሏቸው፡፡ አንድ ሁለቱን ብንጠቅስ ሴቶቻቸውን የመራቢያ አካላቸውን ወይም ብልታቸውን ጨርሶ እንዳይታጠቡ የሚያደርጉ ወይም የሚከለክሉ አሉ ከታጠቡ መሐን ይሆናሉ የሚል እጅግ የተሳሳተና ጨርሶ ተአማኒነት የሌለው እምነት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሴቶቻቸው ሲወልዱ ከማኅበረሰቡ ተነጥላ ወደ ጫካ ሔዳ ያለምንም እረዳት ምጥን ያህል ከባድ ነገር ልጅን ያህል ታላቅ ክብር አደገኛ በሆነ ሁኔታና ቦታ ከአውሬ ጋር ተፋጣና ታግላ ብቻዋን እጣ ነፍሷን ወልዳ ያለ አራሽ እዚያው ጥቂት ከሰነበተች በኋላ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቀላቀል የሚፈቀድላት ቀን ሲደርስ ትመለሳለች ፡፡ እንግዲህ በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ ሴት ሆኖ መፈጠር ምን ያህል እርግማን እንደሆነ መገንዘብ አያቅትም፡፡ እነኝህ ምሳሌዎች መጀመሪያ የጠቀስኩት ተአማኒነት እንደሌለው ማንኛውም ሰው ሊገነዘበው የሚችለው ነው ሁለተኛው ደግሞ ፈጽሞ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት መሆኑን ሁሉም ሰው ይገነዘበዋል እነኝህን መጥፎና አደገኛ ልማዶች የባሕላቸው አካል እንዲሆን የሚያደርጉት ብዙውን ጊዜ የገዛ ማኅበረሰባቸው አባል የሆኑ ጉልበተኛ የጎሳ መሪዎች በተለይም መብታቸው የማይገሰስ የልማዳዊ አምልኮ መሪዎች ነው፡፡ እጅግ ሊቀበሉት የሚከብድን ነገር በገዛ ማኅበረሰባቸው ላይ ጭነው ማኅበረሰቡም ሳያቅማማ ጥቅምና ጉዳቱንም ጨርሶ ለማመዛዘን ሳይሞክር ተቀብሎ ሲፈጽመውም ሲያዩ ያኔ እነሱ በማኅበረሰባቸው ምን ያህል እንደተወደዱ፣እንደተፈሩ፣እንደተከበሩ ዕያዩ ይረካሉ ይደሰታሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቅኝ ገዥዎች ለጥቅማቸው ሲሉ በግዳጅ ያስፈጽሙት የነበረ ጥቃት ጥቃቱ ይፈጸምበት የነበረው ማኅበረሰብ ያንን ጥቃት ባሕሉ አድርጎ የያዘበት አጋጣሚ ያጋጥማል፡፡ ለምሳሌ እንግሊዞች ኬኒያን በቅኝ ግዛት ይዘው በነበረበት ወቅት ከሀገራችን ድንበርማዶና ወዲህ ያሉ ማኅበረሰቦች መመሳሰል ለአገዛዛቸው አላመች ሲላቸው ከድንበሩ ወዲህ ያሉ ማኅበረሰቦችን ከድንበሩ ወዲያ ካሉቱ ለመለየትና ጎሳን ከጎሳ ለመለየት ፊታቸውን በተለያዬ መልክ ይተለትሏቸው ነበር በሚገርም ሁኔታም አነዚህ ጎሳዎች እስከ አሁንም ድረስ ያንን ጥቃት ባሕላቸው አድርገው የያዙበትና የሚፈጽሙበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ እንግዲህ እስከዚህ ባለው ገለጻየ ስለ ባሕልና ልማድ ምንነትና ልዩነት ለማስረዳት ሞክሬያለሁ፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ ግልጽ እንደሆነላቹህ፡፡
የሴት ልጅ ግርዛት ባሕል ነው ወይስ ልማድ?
የወንድ ልጅ ግርዛት የአይሁድ ሃይማኖት ሃይማኖታዊ ግዴታ ከመሆኑ በፊት የእኛ የኢትዮጵያዊያን ባሕል እንደነበረ ከመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ  የሙሴ ሚስት ሲፓራ ሙሴ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር የባርነት አገዛዝ እግዚአብሔር ባዘዘው መንገድ ነፃ ካወጣቸውና የሕዝቡ መሪ ሆኖ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ግርዛትን የአይሁድ ሃይማኖት ሥርዓት አድርጎ ከመደንገጉ በፊት ግርዛትን በልጇ ላይ እንደፈጸመች ማየት እንችላለን፡፡ ዘጸ. 4÷25 ከዚህ በኋላ ግን በአሁኑ ወቅት የወንድ ልጅ ግርዛት ጠቃሚነቱ ታምኖበት አይሁድ ያልሆነ ሁሉ ለነገሩ የኦሪትን ሥርዓት ወይም ብሉይ ኪዳንን የሚከተል ሁሉ አይሁድ አይደለም ወይም የግድ አይሁድ መሆን አይጠበቅበትም፡፡ እንዲያው በዘልማድ ይባላል እንጅ፤ ምክንያቱም አሁን እኛን ኢትዮጵያዊያንን የወሰድን እንደሆን አይሁድ አይደለንም ነገር ግን ኦሪትን ወይም ብሉይ ኪዳንን እንቀበል ወይም በዚያ ሥርዓተ አምልኮ እግዚአብሔርን እናመልክ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ተጽፎ ይገኛል፡፡ እናም ዛሬ ለመገረዝ አይሁድ ወይም ኦሪታዊ መሆኑ ግድ ሳይሆን ሁሉም ወንዶች እየፈጸሙትና የዓለም ሕዝብ የጋራ ባሕል ሆኗል ማለት የሚቻል ሆኗል፡፡ ጠቀሜታ ያለው ነገር ሆኖ ስለተገኘ፡፡
የሴት ልጅን ግርዛት የሚቃወሙ ሰዎች ከዚህ ተሞክሮ ሊማሩት የሚገባ አንዳች ቁምነገር አለ፡፡ የሴት ልጅ ብልት ተፈጥሮ ያደላት ነውና መነካት የለበትም የሚለው ሐሳባቸው ከመከራከሪያ ነጥቦቻቸው አንዱ ነውና፡፡ ጥሩ ምነዋ ታዲያ የወንዱንም ሸለፈት በዚሁ መልኩ ያላዩት? የሴት ልጅ ግርዛት ከሃይማኖት መሪዎች እስከ ፖለቲከኞች (እምነተ-አስተዳደሮች) ድረስ አወዛጋቢና አከራካሪ ሆኗል፡፡ እንደኔ እንደኔ የወንድ ልጅ ግርዛት የሁሉም ባሕል እንደሆነና ተቀባይነት እንዳገኘ ሁሉ ቢያንስ በረጅም የጊዜ ሂደትና ጥናታዊ ሙከራዎች እንደሚጠቅማቸው ዐውቀውና በሁኔታዎች ተገደው ባሕላቸው አድርገውት ለኖሩት ማኅበረሰቦች ባሕላቸው እንደሆነ እንዲቀጥል ዓለም ሊቀበልላቸውና ሊፈቅድላቸው ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ከተረዳም እንደወንዱ ግርዛት ሁሉ የሴት ልጅ ግርዛትም ዓለማቀፍዊ ባሕል አድርጎ ቢወስደው ከዚሁ ጋር ተያይዘው ካሉ ችግሮችና ውጤታቸው ማኅበራዊ ቀውስ አንፃር ማምለጫ የተሻለውና ብቸኛው አማራጭ ይሄው  በመሆኑ መልካም እንደሆነ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህች ዓለም ወይም የዓለማችን ሕዝብ ከዚህ በኋላ የመንፈስ ንጽሕና ተሐድሶ (the renaissance of spiritual purity) ለማድረግ ሥራዬ ብሎ የሚያስብ ከሆነና የማድረግም ዕድል የሚኖረው ከሆነ ፣ የተሠባበረውና እየተሰባበረ ያለው የሞራል(የግብረ-ገብ) እሴቶቹን ለመጠገን የሚሻ ከሆነና ይሄንን ለማድረግም ዕድል የሚያገኝ ከሆነ ብቸኛው የመታደሻ መንገዱና መሠረቱ የማንሠራሪያ አቅሙ የሴት ልጅን ግርዛት በባሕል ደረጃ መቀበል እንደሆነ ይደርስበታል ብየ እጠብቃለሁ፡፡ ያኔ የወንድ ልጅ ግርዛት ከሀገራችን ወጥቶ ጠቀሜታው ታምኖበት የመላው ዓለም ሕዝብ ባሕል ለመሆን እንደበቃ ሁሉ የሴት ልጅ ግርዛትም እንዲሁ ይሆናል የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡
women gmአንዲት ሀገር ጥንታዊት ሀገር መሆኗን ማኅበረሰቧም ጥንታዊ ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ህላዌና ቁርኝት ያለው መሆኑን ከሚያስረዱ ነገሮች አንዱ በሙከራዎች (by trial and error) ሲሞክር የሚወድቀውን ሲጥል የሚያነሣውን ሲያነሣ ያመጣው ሲቀባበለው ወይም ሲወርድ ሲዋረድ እዚህ ያደረሰው ባሕል ልብ በሉ እያልኳቹህ ያለሁት ባሕል ነው የባሕል ስም ያገኘ ልማድ አይደለም፡፡ እናም እንዲህ ዓይነት ባሕል ወይም አስተሳሰብ ነው፡፡ የአንድን ማኅበረሰብ ጥንታዊነትና ትሥሥር የሚመሰክረው ወይም የሚያስረዳው፡፡
እናት አባቶቻችን እንደ አንድ ማኅበረሰብ በአንድነት መኖር ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የሕይዎትን መንገድ ለማመቻቸት ሥርዓት ሲሠሩ በተመሳሳይ ሰዓት ባሕል የሚለው እሴት ተወልዶ ቁጭ አለ፡፡ ባሕል ከመፈጠሩ በፊት ግን ከላይ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ሲሞክሩትና ውጤቱን ሲያዩ ሲጥሉና ሲያነሱ ብዙ ጊዜ የፈጀ ሒደት አሳልፈዋል፡፡ በመጨረሻ ነው ጥሩ ነው ይጠቅማል ያሉትን ያጣሩትን ባሕላችን አድርገው  ለትውልድ የሚያስተላልፉት ፡፡ አሁን ስለ ሴት ልጅ ግርዛት ስናወራ በዚህ ሒደት ያለፈ ነው ወይ? ከተባለ መልሴ በሚገባ ነዋ! የሚል ይሆናል፡፡ እናት አባቶቻችንን ለምን ይሄንን እንደሚያደርጉ ወይም ያደርጉ እንደነበረ ስትጠይቁ መጀመሪያ የሚመልሱት መልስ በጣም አጭር እና ግልጽ ያልሆነ ከገባም ለጥቂቶች ብቻ የሚገባ መልስ ነው፡፡ እሱም ‹‹ካልተገረዘች እቃ ትሠብራለች›› በማለት፡፡ በዚህች አጭር ቃል ውስጥ ግን ብዙ ከባባድ ሀቆችና ምሥጢሮች አደጋዎች ታጭቀው ይገኛሉ፡፡
‹‹እቃ ትሠብራለች›› በጣም ጨዋ በሆነ አገላለጽ ለመግለጽ ሲሉ የሚፈሩትን አደጋ ግን በግልጽ ሳያስቀምጡት ቀሩ፡፡ ለነገሩ ይሄ የማይገባው ሰው ይኖር አይመስለኝም በተለይ ምን ሆና? ለምንድን ነው ዕቃ  የምትሠብረው? ብሎ ለመጠየቅ ሰው፤ ቁም ነገሩ ያለውም በእነዚህ መልሶች ላይ ነው፡፡ እኔም ተጋፍቸ ምን ሆና? ብየ ጠይቄ ነበርና በጥናቴ ወቅት ከጠየኳቸው እናቶችና አባቶች እንደተረዳሁት ያልተገረዘች ሴት ዕቃ የምትሠብርበት ምክንያት ግልጽና አጭር በሆነ አገላለጽ ስገልጸው አቅል ከማጣቷ ቀልቧ ከመሰረቁ የተነሣ ነው፡፡ አቅል የምታጣው ቀልቧስ የሚሰረቀው ለምንድን ነው ብትሉ ደሞ ተገርዞ  መጣል ያለበት የብልቷ አካል ስላልተገረዘ ይሏቹሀል፡፡ እና እሱ ነው ማለት ነው አቅል የሚያሳጣት ቀልቧንም የሚያሰርቅባት? ስትሉ አዎን ይሏቹሀል፡፡ እንዴት አድርጎ ካላቹህ ደግሞ የመጨረሻቸውን መልሳቸውን ይሰጧቹሀል፡፡ ይሄ ተገርዞ የሚወድቀው ነገር የሴትን ልጅ የወሲብ ፍላጎት እየቀሰቀሰና እያናረ እያባባሰ ስለሚያስቸግራት ያለችበትን ጊዜ ቦታና ሁኔታ ክብርና ደረጃ ወ.ዘ.ተ እንዳታገናዝብ እንዳታስተውል እንድትረሳ አድርጎ የቀሰቀሰባትን ስሜቷን ላመርካት ብቻ እንድታስብ እንድፈጽመውም በመገፋፋት የትም ከማንም ጋር እንድትወድቅ በማድረግ ክብሯን ያረክሳል፣ ለችግር ይዳርጋታል፣ ጋለሞታ  ወይም ትዳር አልባ ያደርጋታል፣ ትዳር ብትመሠርትም እንኳ ለትዳሯ ታማኝ እንዳትሆንና ባሏ ብቻ ለወሲብ ፍላጎቷ በቂ ሆኖ እንዳታገኘው ወይም እንዳይበቃት ያደርጋታል፡፡ በማለት እየፈሩም እየተሽኮረመሙም እየተጨነቁም  ሲመልሱላቹህ የነበረውን የጥያቄዎቻቹህን መልሶች ይደመድሟሉ፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ በእኛ ዘመን ደግሞ ካለመገረዝ በሚፈጠር የናረ የወሲብ ስሜት ጥማት ሳቢያ ጉዳዩ ከዚህም አልፎ ሌላ መልክ እንዲይዝ እያደረገ ነው፡፡ ይህ ችግር ቀደም ሲል በምዕራቡና በሌሎች ሀገሮች ስንሰማው የነበረ አሁን አሁን ግን ግርዛት ከቀረ ወዲህ በሀገራችንም እየተስፋፋ የመጣ ነው እሱም ግብረሰዶማዊነት ነው፡፡ የሴት ልጅ ግርዛት መቅረት ሴቶችን ለስሜታቸው የተሸነፉና እሱን ብቻ ለማዳመጥ እንዲገደዱ ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም በከፊል ተገርዞ እንዲወድቅ የሚደረገው የብልት አካል ሥራው የወሲብ ፍላጎትን ማናር ማባባስ እንደመሆኑ መጠን ሴቶች ከወንድ ጋር በሚያደርጉት ወሲብ ያለው የጊዜ ቆይታ በቂ ሆኖ ስለማያገኙት ሴቶችን ከወንዶች እያራቀ እርስ በርሳቸው በራሳቸው መንገድና በፈለጉት የጊዜ ቆይታና የድግግሞሽ መጠን የወሲብ ድርጊትን በመፈጸም የወሲብ ፍላጎታቸውን ወደ ማርካት እንዲሔዱ እያደረጋቸው ነው፡፡ በሌላም በኩል ይህ የሴቶች የወሲብ አጋርን በተመሳሳይ ፆታ እንዲሆን የመምረጣቸው ጉዳይ ወንዶችንም በሁለት ምክንያቶች ተመሳሳያቸውን ፆታ እንዲመርጡ በማድረግ ግብረሰዶማዊነት እንዲስፋፋ ቀጥተኛ የሆነ አሉታዊ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ አንደኛው ምክንያት ወንዶቹ እነዚህ ዓይነት ሴቶች የሚፈልጉባቸውን ወሲብ የመከወን ችሎታና የጊዜ ቆይታ ሊያሟሉ ባለመቻላቸው ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ሴቶቹ ወደ እርስበርስ ወሲብ (ግብረሰዶማዊነት) ወይም ሌዝቢነት ማተኮራቸው ወንዶቹ እነሱን በፈለጉ ጊዜ ሊያገኟቸው አለመቻላቸው በሚፈጥረው እጥረትና እጦት ሳቢያ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ተሞክሮ  በዚህ ደረጃ እንደምዕራባዊያኑ በሀገራችን ውስጥ ገና አልደረሰም፡፡ አንዳች ነገር እስካልተደረገ ድረስ ግን የሰይጣን ጆሮው ይደፈንና ወደ ፊት ምዕራባዊያኑ እየተቸገሩበት ባለው ከላይ ከገለጽኩት ደረጃ መደረሱ አይቀርም፡፡
እዚህ ላይ ግልጽ እንዲሆን የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ያልተገረዙ ሴቶች በአመዛኙ ለችግሩ ስለሚዳረጉ እንጂ ሁሉም ያልተገረዙ ሴቶች እንዲህ ይሆናሉ ወይም ዕድል ፈንታቸው እጣ ተርታቸው እንዲህ መሆን ነው ማለት አይደለም፡፡ ጥናቱን በማደርግበት ጊዜ ያልተገረዙ ሆነው ወጣቶችና ከወጣትነትም ያለፉ ልጃገረዶች የሆኑ ወይም ከነ ክብረንጽሕናቸው ያሉ ከገዳም እስከ ዓለም አጋጥመውኛል፡፡ እነዚህ ሴቶች ግን ሃይማኖታዊ አስተምህሮ የተጫናቸውና እነሱም እሱን ወደውና ፈቅደው የተሸከሙ ናቸው፡፡ ይህ መሆኑም የውስጣቸውን በውስጥ አድርገውና ስሜታቸውን አፍነው አርቀው ውጠው የመኖርን ልምድ እንዲያካብቱ እንዲያዳብሩ አስችሏቸዋል፡፡ ጫናውን ተቋቁመው ለመወጣት እንዲያስችላቸውም እራሳቸውን በጾም በጣም ይጎዳሉ በስግደት ያደክማሉ፡፡ ይሁን እንጅ በባሕርያቸው ላይ ያሳደረው የሚታይባቸው  ተመሳሳይ የሆነ ተጽዕኖ አስተውየባቸዋለሁ ‹‹ቁጡነት›› ሁሉም ቁቱዎች ናቸው፡፡     ከባለትዳሮችም እንዲህ ያልተገረዙ ሆነው ነገር ግን ለትዳሮቻቸው ታማኝ የሆኑ ሴቶች እንዳሉ ጥናቴ አረጋግጦልኛል፡፡ ከላይ እንዳልኩት ካልተገረዙት ሴቶች አብዛኛውን ቁጥር የያዙት ግን ከላይ እናት አባቶቻችን የገለጹት ሥጋት የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥናት ባደረኩበት ጊዜ ካጋጠመችኝ አንዲት የ19 ዓመት ወጣት ለአሁኑ ስሟን ቀይረን ሊሊ እንበላት እናም ከዚህች እኅት የተረዳሁት ነገር ቢኖር በጣም ነፃና የባሕልና የሃይማኖት ገደቦች ምንም የማይመስሏት  በእነርሱም መገዛት የማትፈልግ ከአለባበሷ ጀምሮ ወጣ ያለ ነገር የምትመርጥ ልጅ ነች፡፡ ሊሊ ያልተገረዘች ነች ለምን እንዲህ ዓይነቱን የኑሮ ዘይቤ እንደመረጠችና እንደምትከተል በጠየኳት ጊዜ ስትመልስልኝ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከሰው የተለየ ዘይቤ እንዳላት እንኳን ጨርሶ አለማወቋን ነው፡፡ ነገር ግን በመጥፎም በበጎም ከሰው ከሚያጋጥሟት ምላሾች የሆነ የተለየ ነገር ዓይተውባት ሊሆን እንደሚችል ትጠረጥራለች፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን የሆነችውንና የያዘችውን ዘይቤ ልሁነው ብላ መርጣው የሆነችው እንዳልሆነና ስሜቷ የሚያዛትን የሚያሰኛትን ስትከተል ግን በአጋጣሚ አሁን የሆነችውን ሆና እንዳገኘችው ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ሊሊ አለባበሷ ብቻ ሳይሆን አረማመዷና አነጋገሯም ሌሎች በብዙዎቹ  የማይወደዱላት ነገሮች ሁሉም በዚሁ ምክንያት የተከሰቱባት እንጅ ይሁነኝ ብላ የፈጠረችው ዘይቤ ወይም ከሌሎች ዓይታ የወሰደችው እንዳልሆነ ተገንዝቤላታለሁ፡፡ ሊሊ ካልተወደዱልሽ ለምን እንዲህ ታደሪጊያለሽ ለምን አትተይውም? ብየ ለጠየኳት ጥያቄም መብቴ ነው እኔን ደስ ካሰኘኝ ስለሌላው ግድ የለኝም ነበር ያለችኝ፡፡ አንዴም እንዲሁ ስንወያይ “እውነቱን ልንገርህ? እኔ እነኝህን ነገሮች ሳደርግ ወሲብ ስፈጽም ከማገኘው ደስታና እርካታ ያልተናነሰ ደስታ ይሰጡኛል፡፡ ሰው የፈለገውን ቢለኝ ምንም አይመስለኝም” ስትል መልሳልኛለች፡፡
የብዙዎቹ ያልተገረዙ ሴቶች ግን ያለመገረዛቸው ችግር ከባሕላችንም ከሃይማኖታችንም ተጽዕኖ ይመስለኛል የዚችን ልጅ ያህል ገኖ በግልጽ የሚነበብባቸው አይደሉም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ሁሉም መቶ በመቶ ማለት ባንችልም ከሞላ ጎደል ከላይ እናት አባቶቻችን ካልተገረዘች እንዲህ እንዲህ ያደርጋታል እያሉ ከተነተኑት ችግር ግን የመትረፍ የመዳን ዕድል የሚያገኙ አልሆኑም፡፡ እዚህ ላይ አንድ በአጽንኦት ልገልጸው የምፈልገው ነገር ቢኖር ሊሊ ደጋግማ ትለው በነበረው ነገር ላይ ለምን እያልኩ ላነሣሁላት  ጥያቄዎች ምላl ‹‹መብቴ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ይህች ልጅ እነኝህን ነገሮች ማድረግ ስለመቻሏና ስላለመቻሏ በሕግ ምን እንደተደነገገ የምታውቀው ነገር የለም፡፡ ያን ያህል መብትና ግዴታዋን ዳስሳ የተረዳች ብትሆን ኖሮ ድርጊቶቿ ሁሉ ሕገወጦችና አስከስሶ ለእሥር የሚዳርግ እንደሆነ ትገነዘብ ነበር፡፡ የሷ ግንዛቤ የመነጨው ውስጧ ወይም ስሜቷ ስለጠየቃት ብቻ ያን የውስጧን ስሜትና ግፊት ማስተናገድ መብቷ እንደሆነ አምና ባይመቻቸውም ሌሎቹም እንዲቀበሉላት እንዲያከብሩላት ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን እኛን ስላማረን ስሜታችን ስለፈለገ ብቻ ማድረግ የፈለግነውን ነገር ማድረግ አለብን ወይ? እንችላለን ወይ? ማለትም በትክክል መብት አለን ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን መልሰን ማለፍ ያለብን ይመስለኛል፡፡ የሰው ልጅ ማኅበራዊ “እንስሳ” ነው ይባላል እንስሳ የሚለውን ቃል ፍጡር ወደሚል እንቀይረው፡፡ በማኅበር ወይም በጋርዮሽ ሲኖርም ሊያግባቡት የሚችሉትን ህልውናውን የሚያረጋግጡለትን “የጋራ ጥቅሞች” እንዲኖሩና እንዲከበሩ የሚያደርጉ ሕግና ሥርዓቶችን በመቅረጽ ነው፡፡ እነሱም ባሕል ወግና ሃይማኖት ናቸው፡፡ በዘመናዊው የኑሮ ዘይቤው ደግሞ በመንግሥት የሚደነገጉ የተለያዩ ሕግና ደንቦችን በመቅረጽ የማይጣስ ማይገሠስ የጋራ የኑሮ ዘይቤ ሥርዓቱን በመቅረጽ ኑሮውን ሲገፋ ቆይቷል፡፡
እነኝህን የጋራ ጥቅሞች ሥርዓቶችን የሚጥስ ሲያጋጥምም ዘመናዊው ሕግ ከመቀረጹ በፊት የጣሰውን ሰው ከአካላዊ ቅጣት አንሥቶ እስከ ሥነ-ልቡናዊ ቅጣቶች ያጠፋውን ሰው ይቀጣ ነበር፡፡ ዘመናዊ ሕግ ከመጣ በኋላም የሕግ አንቀጽ ጠቅሶ በመክሰስና በማስፈረድ ወደ ማረሚያ ቦታዎች በማውረድ ቅጣቱን እንዲያገኝ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሊሊና መሰሎቿም በማኅበረሰቡ የሚደርስባቸው የመገለል ግልምጫና መናቅ ከዚያም አልፎ አካላዊ ጥቃት የሚከሰትባቸውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ማኅበረሰቡ የጋራ ጥቅማችን ድንበር ነው ብሎ ከከለለው አጥር ካሠመረው መሥመር በማለፋቸው የተቀበሉት ቅጣት ነው፡፡ እነኛን የጋራ ጥቅሞችን የማክበር የማስከበርና ለዚሁም መስማማት  እንደ ሰው ከሰው ልጆች የሚጠበቅና ለሁላችንም አማራጭ የሌለው ጠቃሚ ሥርዓትም ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ግን ሰው ከሰውነት ወጥቶ ሕግና ሥርዓት አልባ የጋራ መግባቢያ (code of conduct) የሌለው ተግባብቶና ተስማምቶ የማይሠራና የማይኖር ምሳሌ ለመስጠት የሚያስቸግር ኑሮ ይኖረው ነበር፡፡ እኛን የሚያግባባን ተስማምተን ተባብረን እንድንሠራ እንድንኖር የሚያደርገን የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የመግባቢያ ደንብ መኖሩና ይሄንንም የሚያስከብር እንደ ወግ ባሕልና ሃይማኖት ያሉ የጋራ ሕግ ሥርዓትና የኑሮ ዘይቤ መኖራቸው ነው፡፡ የሰው ልጆችን እንደሰው ልጆች አግባብቶ የሚያኖር ይሄው ነው ምንም እንኳን አንዳንድ ከአስተዳደግና ካለመብሰል የተነሣ እንስሳዊ ባሕርይ በሚያይልባቸው አፈንጋጮች ፈተና ቢያጋጥመውም ቅሉ፤ ይህ ሥርዓት ባይኖረን ግን ከመሰብሰብ ይልቅ እንበተን ነበር ከማኅበራዊነት ይልቅ ተነጣጣይነት ከመተሳሰብ ይልቅ እንጨካከን ነበር ወ.ዘ.ተ እነኝህ ችግሮች ደግሞ የሰብአዊነት ወይም ሰው የመሆን መገለጫዎች አይደሉም የአውሬነት እንጅ፤ በመሆኑም የጋራ ጥቅሞቻችን መቸም ቢሆን መጠበቅ ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡ ‹‹መብቴ ነው›› የምንለው ነገር የጋራ ጥቅማችንን የሚቃረን ወይም የሚጥስ ከሆነ ያኔ መብታችን መሆኑ ያበቃለታል፡፡
ለአንድ ሰው የሚያደርገው ወይም ሊያደርገው የፈለገው ነገር ግላዊ መብቱ ሊሆን የሚችለው ነገሩ ማኅበረሰቡ የጋራ ጥቅማችን ነው ብሎ ካለው ባሕል ሕግ ሥርዓት ወይም የኗኗር ዘይቤና ሃይማኖት ጋር የማይጋጭ ሆኖ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ሥርዓት አክብሮ የሚንቀሳቀሰው ሰው ብዙ ስለሆነና አፈንጋጮቹ ደግሞ ጥቂቶች ስለሆኑ እንጅ የጋራ ጥቅም ማሠሪያችን ጨርሶ ቢበጠስ አፈንጋቾቹም ራሳቸው አደጋ ላይ በወደቁ ወይም ህልውና የማግኘት ዕድል ባልኖራቸውም ነበር፡፡ ማንም ተጠቃሚ የሚሆን አይኖርም እንደኔ እምነት የሰው ልጅ ከእንስሳት የሚለይበት ዋነኛው ነገር በስሜቱ ላይ መሠልጠን መቻሉ ወይም ስሜቱን መቆጣጠር መቻሉ ነው፡፡ እንደ እንስሳትና አራዊት ስሜቱ ያዘዘውን ነገር በተሰማው ቅጽበትና ቦታ የመግለጽ ወይም የመተግበር የስሜት ግዴታ ውስጥ የሚከት ተፈጥሮ የለውም ስሜቱን መምራት ወይም መቆጣጠር በስሜቱ ላይ መሠልጠን የሚያስችለው ተፈጥሮአዊ አቅም ጸጋ አለው፡፡ እናም ይህች እኅታችን አለመገረዟ እዚህ ዓይነት ጣጣ ቢከታትም ሰው የሰው ልጅ በመሆኗ ብቻ በስሜቷ ላይ የመሠልጠንን ስሜትን የመቆጣጠርን ጸጋዋን አቅሟን አነቃቅታ ለስሜቷ ወይም ለውሳጣዊ አጉራ ዘለል ፍላጎቷ አለቅጥ ሳታደላ ለፍላጎቷ ገደብ ማበጀትና ማረቅ መግታት በተገባት ነበር፡፡ እሷ ግን ከዚህ ይልቅ ጭራሽም ሰው ሁሉ ወዶ እንዲቀበልላትና የእሷነት መብቷ እንደሆነም አስባ እንዲታሰብላት ፈለገች፡፡
ሰብአዊ መብት በዘመንኛ ምዕራባዊያን ዕይታ ከባሕልና ግብረገብነት አንፃር፡-
ፍላጎትን መብት አድርጎ የማስቆጠር ፍላጎት በሊሊና በመሰሎቿ ያለ ችግር ብቻ አይደለም፡፡ በተለይም በዚህ ወቅት ወደ ምዕራቡ ዓለም ስትሔዱ ይህንን ጉዳይ የሰብአዊ መብት አድርገው ከሰብአዊ መብት ትርጓሜና ምንነት ጋር ጨርሶ የማይስማማና የማይጣጣምን ነገር ለማገናኘት ሲሞክሩ ታገኟቸዋላቹህ፡፡ ሊገናኝ እንደማይችል እነሱም የሚያጡት አይመስለኝም ነገር ግን ሥጋዊና ኢግብረ-ገባዊ ተግባራቸው ስለበለጠባቸው ያልተገራና ሊገሩትም የማይፈልጉትን ስሜታቸውንና ድርጊቱን ፍጹም ኢግብረ-ገባዊ በሆነ መንገድ በነፃነት የትም ቦታ ለማድረግ የግድ ሕጋዊ ሽፋን ማግኘት ስላለባቸውና‹‹ሰብአዊ መብት›› ከምትለዋ መጠለያ የተሻለ አስተማማኝ መጠለያ ስለሌላቸው እንጅ፤ ተስማሚውና የሚገባቸው ሥያሜ ግን ‹‹የጋጠዎጦች ወይም የስዶች ተግባራት መብት›› የሚለው ሥያሜ ነው ያውም የዚህ ዓይነት ግብር መብት የሚሆን ከሆነ ነው፤ ስለማይሆንም ይመስለኛል መልካም ስም ፈልጎ መጠጋት ግድ የሆነባቸው፡፡ በሚገርም ሁኔታ እነኝህ ጸያፍ ድርጊቶችን የሰብአዊ መብት ሽፋን እንዲያገኙ የማድረጉ እንቅስቃሴ እዚህ ሀገራችንም ያውም የሕግ ባለሙያ ነን በሚሉ ግለሰቦች እየተደረገ ነው፡፡
ባለፈው ሰሞን እንዲት ቤቲ የተባለች ልጅ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” በተባለ የእውነታ ትዕይንት ላይ ያልተገባና በባሕላችን በሃይማኖታችን በሕጋችንም የተከለከለ የተወገዘ ጸያፍ ድርጊት ፈጽማ መነጋገሪያ ሆና በነበረበት ጊዜ እንደ ዜጋና እንደ የሕግ ባለሙያ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሁለት የሕግ ባለሙያዎች በሀገርና በሕዝብ ላይ ያልተገባ ሀፍረት ያሸከመችንን ልጅ ለመክሰስና ለማስቀጣት በተመሳሳይም ሰዓት መሰሎቿ እንዳይበረታቱና ነገ ደሞ ከዚህ የከፋ ነገር አድርገው እንዳያዋርዱን መቀጣጫና ማስተማሪያ ለማድረግ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ እንቅስቃሴያቸውን ለማደናቀፍ የተቻላቸውን ጥረት አደረጉ የስም ማጥፋት ዘመቻም ለማድረግ ሞከሩ የሕግ ባለሙያዎችን  አጋጣሚውን ተጠቅመው ዕውቅና ለማግኘት የፈለጉ ምንትስ ምንትስ አሏቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝን ነው እንደኔ እንደኔ ምን ነው እንዲያው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ዕውቅና እየፈለገ መልካም መልካም ሥራ የሚሠራ በሆነ ምንኛ በታደልን ሀገራችንም የት በደረሰች ነበር፡፡ ዕውቅና ለማግኘት ቢሆንስ ምንድን ነው ክፋቱ? ባደጉት ሀገሮች ዕውቅና ለማግኘት በሚል ተነሣሽነት አይደለም እንዴ ስንት ሥራ የሚሠራው? እንኳንና መልካም ሥራ ክፉ ሥራ ተሠርቶም ለመታወቅ የሚፈልጉ ዜጎች የሏቸውም እንዴ? የሰው ልጅ በተፈጥሮው ጥቅም ፈላጊ ከመሆኑ የተነሣ የሁላችንም የጋራ ባሕርይ ነውና የተባሉት ነገር እውነት ቢሆንም እንኳ አንድም ችግር የለበትም፡፡ ብቻ ምን አለፋቹህ በወቅቱ ጥቅማቸው የተነካባቸው ሥውር ዓላማ አንግበው በሕግ ባለሙያዎቹ ላይ ከዘመቱት ይልቅ ተንኮሉ ሳይገባው ተቀብሎ የሚያወራው ሰው ብሶ ነበር፡፡ እነዚያ የሕግ ባለሙያዎች አሁን ላይ ያቋርጡት ይቀጥሉበት ምን እንደሆኑም አላውቅም፡፡
ይሄን ጉዳይ ያነሣሁት በወቅቱ እነዚህን የሕግ ባለሞያዎች በተመለከተ አንድ የሕግ ባለሙያ የተባለ ግለሰብ ያውም በብዙኃን መገናኛ ተደማጭ ሳምንታዊ የመወያያ መድረክ ላይ የተናገረው ነገር በምዕራቡ ዓለም ጸያፍ ድርጊቶችን ከሰብአዊ መብት ጋር በማያያዝ ከለላ እንዲያገኝ የሚያደርጉት ጥረትና ስኬትም እዚህ ሀገራችን ላይም ለመተግበር በመሞከሩ ነው፡፡ ይህ ሰው በዚያ የሬዲዮ(የነጋሪተ-ወግ) የመወያያ መድረክ ላይ የዘወትር እንግዳ ነው፡፡  የሰውየው አነጋገር እጅግ አስደንጋጭና ለሀገራችንም ፍጹም እንግዳ ነበር፡፡ በወቅቱ ከመደንገጤ የተነሣ በአዘጋጇ የግል ስልክ በመደወልና መልእክት በመጻፍ በልጅቱ ድርጊት ዙሪያ ጋዜጣ ላይ የጻፍኩትን እንዲያነቡ ቢቻል ደሞ የሕግ ባለሙያ ከተባለው ሰው ጋር እንድታወያየኝ እንድጠይቅ አድርጎኝ ነበር፡፡ ያ አንጋፋ የሕግ ባለሙያ የተባለው ሰው ምን ነበር ያለው? ‹‹የእነኛን የሕግ ባለሙያዎች ጥያቄ ወይም ክስ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ካስተናገደው በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ያከተመለት ወይም አጠያያቂ ሆነ ማለት ነው ያኔ እኛም ዝም እንልም እንከሳለን ዝም ብለን አንቀመጥም›› ነበር ያሉት አይገርማቹህም? አሁን ይሄ ሰው የሕግ ባለሙያ ነው? እኔ እሱን ቢያደርገኝ እንደገና አንደኛ ክፍል ወርጀ ሀ ብየ ፊደል እቆጥር ነበር፡፡
እውነት ይህ ሰው “ለሰብአዊ መብት” እንዳለው ሁሉ ተቆርቋሪና  ተሟጋች ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ለእኛ አንገብጋቢ አሳሳቢ የሆነው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ጥያቄ ለቤቲ ዓይነት ተግባር ነውን? ነው ወይስ የሕግ ባለሙያ ተብየው ኢትዮጵያ ውስጥ በየሥፍራው የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ግፍ እረገጣና  በደል የሚጋቱ ወገኖች እንዳሉ የሚያይና የሚሰማ ጆሮ የሌላቸው ሆኖ? ‹‹የደላው ሙቅ ያኝካል አለ ያገሬ ሰው›› የሕግ ባለሙያ ሆይ! እባክዎን እንደሚሉት የሰብአዊ መብት ጥሰት ሚያሳስብዎት ከሆነ ሞጃ ሞጃ ደንበኞችዎን በመጠኑም ቢሆን ቀነስ አድርገው የደም እንባ ለሚያነቡ ቤሳቤስቲን ለሌላቸው ዜጎች ይሟገቱ ሞያዊ ግዴታዎንም ይወጡ፡፡ ለአሁኑ ግን  አንድ ላስገነዝብዎት የምፈልገው ጉዳይ እርስዎም እንደ ሊሊ ቤቲና ምዕራባዊያን የሞያ አጋርዎችዎ ሁሉ በሰው ጭንቅላት የታሰበ “ሰው” ሊያደርገው የፈለገው ምንም ዓይነት ቢሆን ስሜትን ፍላጎትን የመግለጽ የመተግበር ፍላጎት ሁሉ በሰው ጭንቅላት ስለታሰበ ብቻ የሰብአዊ መብት ጥያቄ ነው ብለው ያስባሉ ያምናሉና እጅግ መሳሳትዎን ላረጋግጥልዎት እወዳለሁ፡፡ ጥሩ እንግዲያውስ እራስን  ማጥፋት መግደልም ሆነ ሌላን ሰው መግደል ሰብአዊ መብት ነዋ፣ እርቃንን በአደባባይ መሔድም ሰብአዊ መብት ነዋ፣ በእርግጠኝነት በእርስዎ ሐሳብ እንደ ብዙዎች የምዕራቡ ዓለም የሞያ አጋርዎ ሁሉ ግብረሰዶማዊነትም ሰብአዊ መብት ነው፡፡ ባጠቃላይ በጤነኛ ሰው አእምሮ የማይታሰቡ ነገሮች በምዕራቡ ዓለም ንኮችና የሥነ-ምግባር እክል ያለባቸው ጋጠወጦች ሕጋዊ ዕውቅናና ጥበቃ እንዲያገኙ ያስቻሏቸው በእነሱም ሀገር ቢሆን ቀደም ባለው ሕጋቸው የተከለከሉና የተወገዙ የነበሩ ድርጊቶች ሁሉ በእርስዎ እምነት ሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡
የሕግ ባለሙያ ሆይ! በእርስዎ ግምት ንክ ስድ ወይም ጋጠወጥ የሚባል ሰው መገለጫው ድርጊቶቹ ምን ዓይነቶች ድርጊቶች ይመስልዎታል? እንደ የሕግ ባለሙያ እራስንና ሌላውን ማጥፋት መጉዳት መግደል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ነው የሚረዱት? በእርስዎ የኑሮ ዘይቤስ ኢትዮጵያዊ ባሕል ወግ አስተሳሰብ ወ.ዘ.ተ ጨርሶ ቦታ የላቸውም ወይ? ለምን? የሕይዎት መመሪያዎችዎ ሁሉ ‹‹ምሁራዊ›› ስም የለጠፉ የምዕራባዊያን ዋልጌዎች የሕይዎት መመሪያ ብቻ ነውን? እንዴ! እንዲህ ከሆነ ታዲያ እኛን አንዳች ነገር ለማለትና ማኅበረሰቡ ተቀብሎት የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ባሕልን፣ ወግን፣ ሃይማኖትን ዕውቅናና ጥበቃ ሰጥቶ እነርሱንም መጣስ መጋፋት መተላላፍ ወንጀል አድርጎ በሚሠራው የሕግ ሥርዓታችን ላይ አንዳች ነገር ሊሉ የሚችሉበት ምን ዓይነት መሠረት መብትና የሞራል (የግብረ-ገብ) አቋም አለዎት? ወይስ ይሄንን አያውቁም? ይሄንን ካላወቁስ ምኑን የሕግ ባለሙያ ሆኑት? ይሄን የምልዎት ከላይ ላነሣሁልዎት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ እነ እከሌ እነ እከሌ እያሉ ሊጠቅሱልኝ የሚችሏቸው ዋልጌ የምዕራባዊያን ታዋቂ የሕግ ባለሞያዎችንና የሕግ አውጭዎችን እነደሆኑ ስለማውቅ ነው፡፡ የሕግ ባለሞያ ሆይ! እኛ ኢትዮጵያዊያን እንጅ ምዕራባዊያን አይደለንም፡፡ ኢትዮጵያዊያን  የራሳችን ባሕል ወግ አስተሳሰብ ማንነት መገለጫ ጥቅም ፍላጎት ወዘተ አሉን፡፡ ሊያስቡና ልንነጋገር የሚገባን በኢትዮጵያዊኛ እንጅ ጊዜ በበከለው ምዕራባዊኛ አይደለም፡፡ እነዚህ ታዋቂ ምዕራባዊያን የሕግ ባለሙያዎች ታዋቂና ‹‹ምሁር›› ስለተባሉ ብቻ የእነሱ ተቀጽላ መሆን አይኖርብዎትም፡፡ ከታዋቂነትና ከምሁርነት ጋራ ሰብእናቸውስ ምን ይመስላል የሚለውን በአንክሮ መመልከት ያስፈልግዎታል፡፡ የእነሱን ዕውቀት ይዘው በኢትዮጵያዊኛ ይተረጉሙት ችግር ካለበት ከእኛም ሳያደርሱት ድንበር ላይ ይጣሉት፡፡ እነዚያን አግባብነት የሌላቸውን ሕጎች ያጸደቋቸውና ለማጽደቅም የሚሯሯጡት ምሁር ስለሆኑ አይደለም ካለባቸው የሰብእና እክል አኳያ እንጅ፤ በመሆኑም ያንን የረከሰ ሐሳባቸውን ሊጋሩ አልፈውም በእኛ ላይ ሊጭኑ የሚችሉበት አንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ በተመሳሳይ እንደእነሱ ሁሉ የሰብእና እክል ካልኖረብዎት ወይም የእነርሱ ጉዳይ ፈፃሚ መልእከተኛ ካልሆኑ  በስተቀር፡፡
በመሆኑም እያደረጉት ያለው ነገር ምን ያህል አደገኛና ከዜጋ የማይጠበቅ እንደሆነ ካለመረዳት ከሆነ ቁጭ ብለው ያጢኑት ይመለሱም፡፡ ካልሆነ ግን አንዳች ተልእኮ አለዎት ማለት ነውና እንደተነቃብዎት ላስገንዝብዎት እወዳለሁ፡፡ ይሄንን ለማለት የሚያስደፍረኝ ብዙ ነገር አለ፡፡ ካዳመጥኳቸው በዚያ የሬዲዮ (የነጋሪተ-ወግ) የመወያያ መድረክ እርስዎ ካነሷቸው ጉዳዮች ብዙዎቹ አልተመቹኝም፡፡ ሌላ ሌላ ይሸታሉ ኢትዮጵያዊኛን ያፈራርሳሉ በብዙዎቹ ባልጣሙኝ ሐሳቦችዎ ላይ በየጊዜው በአዘጋጇ የግል ስልክ እየደወልኩና መልእክት እየጻፍኩ ቅሬታየን ከማረሚያ ሐሳቦቸ ጋር አቅርቤያለሁ፡፡ የሚቻል ከሆነም ለመወያየት ከመፍቀድ ጋር፤ ለማንኛውም ግን በእንደነዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ የአንድ ወገንን ሐሳብ ብቻ  ሳይሆን በአንፃሩ ያለውንም ወገን ማካተትና ሚዛናዊ ማድረግ እንደሚገባ በተለያዩ ጊዜያት አበክሬ አሳስቤ ነበር፡፡ እርስዎ እኮ ሌላው ቀርቶ የራሳችንን የዘመን አቆጣጠራችንንና የሰዓት አቆጣጠራችንን ትተን በይፋ እንደምዕራባዊያኑ እንድናደርግ አጥብቀው የወተወቱ ሰው ነዎት፡፡ እንደዜጋ ይሄ ምን ማለት እንደሆነ እንኳን ለቅጽበት ማሰብ  የቻሉ አልነበሩም፡፡ ያለን የዘመንና የሰዓት አቆጣጠር ከማንነታችን ጋር ያላቸውን ትሥሥርና ቁርኝት ያውቃሉ? እነዚህ የማንነታችን የሥልጣኔያችን መገለጫዎችና አሻራዎች ማስረጃዎች ቅርሶቻችንም እንደሆኑስ ጨርሶ አያውቁም? ይሄንን እንኳን ማወቅ መረዳት የተሳነዎትና እንዲወገዱ የፈለጉ ሰው ነዎት፡፡ አሁን እርስዎም ኢትዮጵያዊ ነዎት? ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ሀብቶችን ማንነትን ቅርሶቻችንን በመንከባከብ በመጠበቅና ለትውልድ በማስተላለፍ ለዚህም ባለን ቁርጠኝነትና ጽናት ካልተለካ በምን ሊለካ የሚችልና የሚገባስ ይመስልዎታል? እነኝህ እሴቶቻችን ከባሕላችን ከወጋችን፣ ከማንነታችን፣ ከአስተሳሰባችን፣ ከሃይማኖታችን ወዘተ ጋራ ያላቸውን ትሥሥርና ቁርኝት ያውቃሉ?
አውቃለሁ እርስዎ እነዚህ እሴቶቻችን ከምዕራባዊያኑ ጋር ሲነጻጸሩ ስላላቸው የላቀ ትክክለኝነትና ተአማኒነት ለመመርመርና ለመረዳት በጣም ሩቅ መሆንዎን ፡፡ የገረመኝ ነገርም ይሄው ነው ይሄንን ያህል ሩቅ ሆነው ሳለ ‹‹ላለመደናገርና ላለመነጠል›› የምትል ቁንጽል የመከራከሪያ ነጥብ በመያዝ ብቻ ያንን ያህል የድፍረት ሐሳብ ያለመሳቀቅ ለመናገር መድፈርዎት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥሩ አድርጌ ጽፌልዎታለሁ ያነቡታል በዚያ መድረክ ላገኝዎት ባለመቻሌና ዋልጌነትን በሰብአዊ መብት ድንኳን ለመሸሸግ ትውልድንም ለማጥፋት የሸፈጡትን ሸፍጥ ግን መታገስ ስላልቻልኩ በዚሁ መልኩ ለማስተናገድ ተገድጃለሁ፡፡ የእርስዎ ዕውቀት ከዘመን በኋላ የተበከው ምዕራባዊኛ ስለሆነና ኢትዮጵያዊኛ ስለሌለበት ሰብአዊ መብት ማለት በኢትዮጵያዊኛ ምን ማለት እንደሆነ ላስተምርዎት ተገድጃለሁ እርስዎ ደግሞ የሰብአዊ መብት “የሰውነት” “ሰው የመሆን መብት” ያለ ሞራል (ግብረ-ገብ) እሴቶች እንዴት ሆኖ ሰብአዊ መብት ሊሆን እንደሚችልና እንደሚገባም ያስተምሩኛል፡፡
ሰብአዊ መብት ማለት ምን ማለት ነው?
“ሰብአዊ መብት” ማለት “ሰው የመሆን መብት ማለት ነው” ይሄም ማለት የሰውን ልጅ  እንደሰውነቱ ማለትም እንደ ክቡርነቱና እንደ ማኅበራዊ ፍጡርነቱ ከሌሎቹ ፍጡራን የሚለየውንና የሚያልቀውን ኅሊናውን ለጸጸትና ለጉዳት የማይዳርጉ ተስማሚ አስተሳሰቡንና የጋራ ጥቅሙን ማለትም ማኅበራዊነቱን ከሰላሙና ደኅንነቱ ጋራ ጠብቆ ለማኖር ያስችለኛል ብሎ በጋራ ስምምነት የቀረጻቸውን ባሕል፣ ወግ፣ የግብረ-ገብ (የሞራል) ድንጋጌዎችን፣ ሃይማኖት ወዘተ. የመጠበቅ የመንከባከብ የማክበር ግዴታና እነሱንም የማጣጣም በእነሱም የመድመቅ የመክበር መብት ማለት እንጅ የአዕምሮ ጤና ዕክልና ዋልጌነት የተጠናወታቸው ወይም ያለባቸው ግለሰቦች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጤናማ ኅሊና የሚጸየፈውን የሚቀፈውን ሥነ-ልቡናውን የሚጎዳውን የሚያውከውን ከሰውነት አንጻር ተቃርኖ ያለውን ግላዊና ማኅበራዊ ጤናውን የሚያውከውን የተለየ ሐሳብና ድርጊት ያለ ሀፍረት በድፍረት የትም ቦታ በነጻነት መፈጸምና የአፈንጋጭ ድርጊቶችን ማስተናገድ ማለት አይደለም በፍጹም፡፡ ለእኛ ማኅበረሰብ እነዚህ የጋራ መተዳደሪያ ደገኛ የሥርዓቶቻችን ማዕዘናቱን ለድርድር የማቅረብንና ያለማቅረብን፣ የመጠበቅንና ያለመጠበቅን፣ የማክበርንና ያለማክበርን፣ የመፈለግንና ያለመፈለግን ጉዳይ የሰዎችን የአዕምሮ ጤና ደረጃና ደኅንነት፣ የጨዋነትና የብስለት ደረጃ መለኪያ መመዘኛዎቹ ናቸው፡፡
ክቡር የሕግ ባለሞያ ሆይ! ይሄው ማለት ነው እንግዲህ ሰብአዊ መብት ማለት በኢትዮጵያዊኛ ሲተነተን ፡፡ የሚገርም ነው! የዘመኑ የሕግ ባለሞያ እንዴት ነው የሚያስበው ጃል? እንዲህም እንዳልል እነዚያን 2 የሕግ ባለሞያዎች የመሰሉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ደሞ አሉ፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ እርስዎ ያሉንን ነገር ሁሉ አንዲት የዝሙት ተዳዳሪ ስትለው ብሰማ ኖሮ ምንም ባልደነቀኝ ነበር፡፡ የሕግ ባለሞያ ነኝ ከሚል ሰው ግን ስሰማ እንዴት አድርጌ? ሕግ ማለት ምን ማለት ይመስልዎታል? የቆመለት ጥቅምና ዓላማውስ ምን ይመስልዎታል? ይሄንን ጥያቄ በቅጡ መርምረውት የሚያውቁ አይመስሉም፡፡ ለዚህ ለዚህማ እኮ ሕግ የሚባል ነገርም ከነአካቴው ባላስፈለገም ነበር፡፡ ሕግ መቀረጹ ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያቱና ዓላማው የጋጠዎጦችን የዋልጌዎችን የሥርዓት አልበኞችን የጉልበተኞችን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ለመቆጣጠር ለመከላከል መተላለፎችን ፈጽመው ሲገኙም ፈጻሚዎቹን ተላላፊዎቹን በመቅጣት ለማረም አይደለም እንዴ ክቡር የሕግ ባለሙያ?
ባሕል፣ ወግ፣ ግብረ-ገብ፣ ሥርዓትና ሃይማኖት “ፍልስፍና” ባልገባቸው ግለሰቦች እንዴት ይታያሉ?
በተመሳሳይም በዘመናችን ከዐሥርት ዓመታት ቀደም ብሎ ጀምሮ ፈላስፎች ነን ብለው ፍልስፍናን እጅግ በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ኅብረተሰቡን ሰብስቦ፣ አሰላስሎ፣ አስማምቶ፣ አግባብቶ፣ አቀናጅቶ፣ አቻችሎ፣ እያደኛኘ እያሸማገለ እንደኅብረተሰብ እንዲኖር የሚያደርገውን ባሕል፣ወግ፣ሥርዓት፣ግብረ-ገብ የመሳሰሉትን የኅብረተሰብን የጋራ ጥቅሞችና አንድነት የመጠበቂያ መንገዶችን የሚቃወሙ የሚቃረኑ የሚቀናቀኑ የሚጥሱ የሚያፈርሱ ግለሰቦች ልብ ሊሉትና ሊያስተውሉት ከባሕል ከወግ ከሥርዓት ከግብረ-ገብ ወዘተ. ቀንበሮች የተላቀቀ የተገላገለ በእነሱ አገላለጽ ‹‹ነፃ የወጣ›› የሚሉትን ሕይዎት እንዲኖረው ከመስበካቸው በፊት እራሳቸውን ሊጠይቁና ሊመልሱት የሚገባ ወሳኝ ጥያቄ ነበር፡፡ ኅብረተሰብ ለምንድን ነው ባሕል ወግ ሥርዓት ግብረ-ገብ ወዘተ. የሚባሉትን የመግባቢያ ደንቦችን (code of conduct) የቀረጸው? በራሱ ላይ ቀንበር መጫን ፈልጎ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው? እንደ የሰው ልጅ እንደ ማኅበረሰብ ሥርዓት ያለው የተረጋጋ ሰላማዊ ኑሮን ለመኖር እነዚህን ደንቦች ቀርጾ ከመኖር ውጭሌላ አማራጭ ነበረው ወይ? ከሌለውስ እነዚህን ሥርዓቶች ቀርጾና ተስማምቶባቸውም መኖር ግዴታው አይደለም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ይኖርባቸው ነበር፡፡ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ፈላስፋ ወይም አቢዮተኛ ነን ብለው ከእነኝህ ማኅበራዊ እሴቶች አፈንግጠው ለመኖር የሞከሩ ሰዎች ሁሉ ይሄንን ጥያቄ ለራሳቸው አንሥተው እና ለመመለስ  ሞክረው አለማወቃቸው ነው ፡፡
እንዴት ቢባል ለመመለስ ቢሚክሩማ ኖሮ በእርግጠኝነት እውነቱን ተረድተው ሌላ አማራጭ እንደሌለ አውቀው ከአፈንጋጭነታቸው የመመለስ ዕድል ባገኙ ነበር፡፡ እውነቱ ግን ያለባቸውን የሰብእናና የሥነ-ምግባር ግድፈት በፍልስፍና ጭንብል ለመሸፈን መሞከራቸው ነው፡፡ አልሆነም እንጅ እነኝህ አፈንጋጮች እንደተመኙት ማኅበረሰቡ እነሱን አርዓያ አድርጎ የቆመባቸውን ማኅበራዊ መሠረቶቹን የባሕል፣ የወግ፣ የሥርዓት፣የግብረ-ገብ ድርጋጌዎቹን ደረማምሶ አፈራርሶ አነሱ የሚኖሩትን የሕይዎት ዘይቤ ቢኖር ኖሮ ይሄኔ የሰው ልጅ የሚባል ፍጥረት ከምድረ-ገጽ ባልተገኘ ነበር፡፡ በሚፈጠረው ሥርዓት አልበኝነትና ማኅበራዊ ቀውስ እርስ በእርሱ ከአውሬ በከፋ ሁኔታ ተባልቶ ተፋጅቶ ተላልቆ ይጠፋልና፡፡ ባሕል ወግ ግብረ-ገብ ሥርዓት ወ.ዘ.ተ የሚጠብቁት የኅብረተሰባዊ ሕይዎትን ቀጣይነትና ሰብአዊነትን ነው፡፡ ያለ እነዚህ እሴቶቹ የሰው ልጅ በሕይወትና በጋርዮሽ  የመኖር ዕድል አይኖረውም፡፡ ፍልስፋና ማለት ያልታየ፣ ልብ ያልተባለ፣ ያልተስተዋለን እውነት ዕውቀት ጥበብ መግለጥ ማሳየት ማስገንዘብ ማለት እንጅ የሥነ-ምግባር ጉድለትን፣ ግድፈትን፣ ኢግብረ-ገባዊነትን፣ ከእውነታ ተቃርኖ ያላቸውን ሐሳቦችና ድርጊቶችን መስበክ ማለት አይደለም፡፡ የሚገርመው ይሄንን ያህል የገዘፈ እውነታና ሀቅ መገንዘብ የተሳናቸው ደናቁርት ሆነው ሳለ ፈላስፋ ነን አቢዮተኛ ነን የሚሉ ሰዎች እራሳቸውን እንደ ምሁር ኅብረተሰቡን ደግሞ እንደ አላዋቂ የሚቆጥሩ መሆናቸው ነው፡፡
እናት አባቶቻችን የሴት ልጅ ግርዛትን ባሕል ማድረጋቸው ትክክል ነው ወይስ አይደለም?
እናት አባቶቻችን ያልተገረዘች ሴት ሰብእናዋ ላይ ያስከትልባታል ካሉት ችግሮችና ውጤቱም ሀገርን እንደ ሀገር እንዳትቀጥልና ኅብረተሰቡንም ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚከት ከተሞክሮና ሲወራረስ ከመጣ የተፈተነ ዕውቀት አረጋግጠው ነውና ባሕል እንዲሆን ያደረጉት ትክክለኛና ከምናየውም አንጻር አሳማኝ  ነው፡፡ ምክንያቱም የሚበዙቱ ያልተገረዙት ሴቶች በሃይማኖት፣ በባሕል፣ በሥነ-ምግባር ሥርዓትና ደንብ ገመድ ራሳቸውን ማሠር የማይፈልጉ በመሆናቸው መፍትሔ ሆኖ ያገኙት ይሄንን ከልክ ያለፈ የወሲብ  ፍላጎት ልከኛ ተመጣጣኝና በቂ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ መፈለግ ትልቁ የቤት ሥራቸው አደረጉት፡፡ እናም ይሄን ሴቷን እንዲህ እያደረገ የሚያስቸግራትን የብልት ክፍል መቀነስ ልብ በሉ ድጋፍ ሰጥቸ እያወራሁለት ያለሁት በደጋማው የሀገራችን ክፍል ሲፈጸም ከኖረው በሁለተኛ ደረጃ የጠቀስኩትን ማለትም ቂንጥር የተባለውን የብልት ክፍል ብቻ የተመለከተውን የግርዛት ዓይነት ነውና‹‹መቀነስ›› የሚለውን ቃል ነው የምጠቀመው፡፡ በቆላማው የሀገራችን ክፍል ስለሚፈጸመው የግርዛት ዓይነት የማወራ ቢሆን ኖሮ እንደ ባለሞያዎቹ ሁሉ “የብልት ትልተላ” ወይም የብልት አካሏን እንዳለ ጠርጎ አንሥቶ ለሽንት መሽኛ ትንሽ ቀዳዳ አስቀርቶ ገጥሞ መስፋት የሚለውን ቃል እጠቀም ነበር፡፡ በዚያ አካባቢ ማለትም በቆላማው የሀገራችን ክፍል የሚኖሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ ይህንን ከመሰለ አሰቃቂ የግርዛት ዓይነት ላይ የደረሱ መስሏቹህ ከሆነ መሳሳታቹህን ልነግራቹህ እወዳለሁ፡፡
ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚያደርጉት የግርዛት ሒደት የሚፈልጉትን ውጤት ያህል ማግኘት ስላልቻሉ እና እሱ ላይ ብቻ ስላተኮሩ እያከበዱት እያከበዱት ሲሔዱ እየከበደ መሔዱን እንኳ ልብ ሳይሉት የሴቷን ተፈጥሮአዊ መብትና ስቃይዋን ጨረሶ ረስተውት የመጨረሻውን አሁን እያደረጉት ያለውን የግርዛት ዓይነት ሊይዙና ባሕላቸውም አርገውት ለመቅረት በቁ፡፡ ለማንኛውም እኔ ድጋፍ የምሰጠውና ቢፈጸም መልካም ጠቃሚ ነው የምለው ይሄ ሴቷን በስሜት የሚያሰክረውን የውስጠኛውን ከንፈር (ቂንጥር) በመባል የሚታወቀውን የብልት አካል ከላዩ ላይ የሚቀነስለትን የግርዛት ዓይነት ነው፡፡ በነገራችን ለይ ከሴቶቻችን ውስጥ የሚገረዘው የብልት አካል ክፍል “ቂንጥር” ሲፈጠሩ ጀምሮ የሌላቸው በርካታ ሴቶች እንዳሉ ታውቃላቹህ? ‹‹ማርያም ግርዝ›› በመባል ይጠራሉ፡፡ እንዴት ተገላገሉ? አልፎ አልፎም ምናልባትም ከሽዎች አንድ ከወንዶችም ያጋጥማል፡፡
በጥናቴ ካገኘኋቸው ውጤቶች የገረመኝ ቢኖር በዚህ ጉዳይ ላይ ቁርጠኛ አቋም ያላቸው ማለትም ግርዛት መኖር አለበት የሚሉቱ ሴቶች ከሴቶችም እናቶች ሆነው ማግኘቴ ነው፡፡ ወንዶች ግን ከወጣቶቹ በአብዛኛው አለመገረዟን የሚፈልጉ ሲሆኑ ሸምገል ያሉት ደሞ ከሞላ ጎደል መገረዟን የሚፈልጉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ይሄንን ውጤት እንዳገኘሁ አንድ አባባላችንን  ነበር ያስታወሰኝ ‹‹ከባለቤቱ የሚያውቅ ምንን ነው›› የሚሉትን፡፡ ሴቶች ከሴቶችም እናቶች እንዴት? ለምን? በግርዛት ችግር እንደሚገጥማቸው የሚወራባቸው እናቶች አቋማቸው እንዲህ ሊሆን ቻለ? አቋማቸው ብቻም አይደለ አገላለፃቸውንና ስሜታቸውን እንደኔ ከፊታቸው የማንበብ ዕድል ብታገኙ እጅግ ነው የሚገርማቹህ አቋማቸው በጣም ጽኑ ነው፡፡ እንግዲህ የጉዳዩ ባለቤቶች እነሱው ስለሆኑ እንደኛ ተወርቶላቸው ሳይሆን ይዘውት ዓይተውት ስለሚያውቁት ባለመገረዛቸው የሚያደርጋቸውንና የሚያጋጥማቸውንም ችግር ከመረዳት አንፃር ይሆናል ብየ አሰብኩ፡፡
ቀድሞ የነበረኝ ግምት ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተማረሩትና እንዲቀር የሚፈልጉት ሴቶች ይመስሉኝ ነበር፡፡ ሌላው ያረጋገጥኩት ነገር ይሄንን ጉዳይ ወላጅ ሆነው ሲያዩትና ወላጅ ሳይሆኑ ሲያዩት ፍጹም የተቃረኑ አቋሞችን ለመያዝ ግድ መሆኑ ነው ፡፡ ይህ ሀቅ ሁልጊዜ በብዙው ሰው ላይ ይንፀባረቃል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ የግርዛት ቀጠና ዜጎችን ሳይቀር የቱንም ያህል ቢማሩና ቢለወጡ በዚህ ጉዳይ ግን ሁል ጊዜ እጅግ ሲቸገሩና ሲፈተኑ ይስተዋላሉ፡፡ እስከ ሦስት ሽህ ዶላር በአማካኝ ለሚደርስ ፍጹም ተገቢ ላልሆነ እጅግ ውድ ክፍያ እንዲከፍሉ ተገደው እዚያው ከሚኖሩባቸው ሀገሮች የድብቅ ማስገረዣ ቦታዎች በድብቅ ከማስገረዝ ጀምሮ ወደየሀገሮቻቸው በሽርሽር ወይም በዘመድ ጥየቃ ስም እየወሰዱ ለማስገረዝ እስከመገደድ ይደርሳሉ፡፡ ይሄንን የሚያደርጉበት ምክንያት እንዲሁ ባሕላቸው ስለሆነ ሳይሆን የማይገረዙት የሚኖሩባቸው ሀገሮች ዜጎች ልጆች ባለመገረዛቸው ምክንያት በወሲብ ፍላጎት ስሜት ተገደው ለአቅመ ሔዋን ከመድረሳቸው በፊት በ12ና በ13 ዓመታቸው ወሲብ ጀምረው በ14 ዓመታቸው የልጅ እናት እየሆኑ እየተሰናከሉ ስለሚቀሩና ይሄንንም ስለሚያዩ ልጆቻቸውን ከዚህ አደጋ ለመታደግ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ይሄው ሆኖ ስለሚያገኙት ነው፡፡
ይሄም ሆኖ እንዴ! ምነው ባክህ የእኛ ሴቶች ከማን የባሱ ሆነው ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የሚታይባቸው? ምነው የምዕራቡ ዓለም ሴቶች አይገረዙም ነገር ግን እኛን ያሠጋን ጉዳይ ምንነውሳ እነሱንም አላሠጋ? የሚል አግባብነት ያለው ጥያቄ ሊነሣ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በዓለማችን ግርዛትን ባሕላቸው ያደረጉ ሀገሮች በመባል የሚታወቁት በእስያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና ከሁለት ሦስቱ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በስተቀር ከወገብ በላይ የአፍሪካ ሀገሮች በሙሉ ናቸው፡፡ ይህ ቀጠና የግርዛት ቀጠና ይባላል፡፡ ሀገራችንም በዚሁ ክልል ውስጥ እንደመገኘቷ የቀጠናው አካል ነች፡፡ በተቀረው የዓለማችን ክፍል ግን ወይ ከእኛው ቀጠና ተሰደው  የሔዱ ሰዎች ካልሆኑ በቀር ግርዛትን በባሕል ደረጃ የያዙ ኅብረተሰቦችና ሀገሮች የሉም፡፡
የግርዛት ቀጠና የሚባለው አካባቢ የግርዛት ባሕል ሊኖረው የቻለው የተቀረው ግን ያልኖረው ለምንድን ነው?
አግባብነት ያለው ጥያቄ ነው ከዚህም ጋር እኛን ያሳሰበን ጉዳይ ሌላውን ያላሳሰበው ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይገባል፡፡ ለእኛ ችግር የሆነብን ለሌሎቹ ግን ያልሆነባቸው ለሚሉት ጥያቄዎች የግሌን መላምቶችና አመለካከቶች እሰነዝራለሁ፡፡ አመለካከቴን አስቀድማለሁ መላምቶቸን በተመለከተ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ግን ለመጣቅ (ለሳይንስ) ወይም ለመጣቅያን (ለሳይንቲስቶች) እንዲሁም ቴክኖሎጂው (ኪነ-ብጀታው) ለሚፈቅድላቸው እተወዋለሁ፡፡ ለእኔ ግን አይደለም ለእኔ ለሀገራችን ለተቋማትም የሚቻል አይደለም፡፡
ከአመለካከቴ ስነሣ ይህ የግርዛት ቀጠና የተባለው አካባቢ ጥንታዊ ሥልጣኔ የፈለቀበትና ጥንታዊ ማኅበረሰብ የሚገኝበት ቀጠና ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ከሌሎቹ የዓለም ክፍሎች ካሉ ማኅበረሰቦች በተለየ ሁኔታ ለክብርና ለማንነት የሚሰጠው ትርጉምና ዋጋ ከበድ ያለ መሆኑ ማኅበራዊም ሆነ ግላዊ ክብሩና ማንነቱ እንዳይነካ ወይም እንዳይደፈር ለማድረግ ዋስትና አድርጎ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱና ዋነኛው ቁልፉ ነገር የሴት ልጅ ግርዛት መሆኑ ሲሆን፡፡ ከዚያም ባሻገር ሴቶች በወሲብና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ የሚሰማቸውንና የሚያስቡትን የሚመስላቸውንም ከተቃራኒ ፆታ ጋር በመግለጥ በማውራት ለመጠቃት መንገድ እንዳይከፍት፣ ምክንያት እንዳይሆን  የሚያደርግ ‹‹ነውር›› የሚባል የማይጣስ የአስተሳሰብ አጥር መከለልም ግዴታው አድርጎ በማሰብ አጥር ቀጥሯል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ግን የዳበረ ትሥሥር ያለው ጥንታዊ ማኅበረሰብ ስላልሆነ ይህን በመሳሰለ ነገር ላይ ጊዜ ወስዶ በጥልቀት ያጠናውና ሲወርድ ሲዋረድ የተቀባበለው ነገር ስለሌለው አንደኛው ምክንያት ሲሆን፡፡ ሌላው ደግሞ ለክብርና ለሞራል (ለግብረ-ገብ) እሴቶች የሚሰጡት ዋጋ ትርጉምና ክብር እንደ የግርዛት ቀጠና ሀገሮች ጠንካራና የጠለቀ ባለመሆኑ ለእነዚህ እሴቶች ለመጠበቃቸውና ላለመጠበቃቸው ቁልፍ ሚና የሚጫወተውን የሴት ልጅ ግርዛትን ባሕል የማድረግ ጉዳይ ሳያሳስባቸው ቀርቷል፡፡circum
ለምሳሌ የሀገራችንን ሴቶች የወሰድን እንደሆነ እንደዛሬው በምዕራቡ ዓለም ዘመንኛ ባሕል ሳይበከሉና ባለመገረዝ ምክንያት በሚፈጠር ተጽእኖ ሳይወድቁ ከባሏ ጋር ተራክቦ ወይም ግንኙነት ቢያምራት በተለያዩ መንገዶች መፈለጓን ታመለክታለች ትጠቁማለች እንጅ ብትሞት አምሮኛልና አርገኝ አትልም፡፡ ያውም እንዲያው ደፈር ያለች ሴት ከሆነች ነው ምልክትም የምታሳይ፡፡ አምሮኛል አርገኝ ካለች ክብሯ የሚነካ ነውር የማታውቅ ባለጌ ተደርጋ የምትቆጠር ይመስላታል ትቆጠራለችም፡፡ ወደ ምዕራቡ ዓለም ሴቶች ስንሔድ ግን ይሄ ሁሉ የለም ጭራሽ እንዲያውም ፍርድ ቤት ሁሉ ልትገትረውም ትችላለች፡፡ ያውም ታማኝ ከሆነች ነው ያለዛ ግን እያወቀም ቢሆን ወደ ሌላ ትሄዳለች፡፡ መወስለቷ የመታወቅ ያለመታወቁ ጉዳይ የማያሳስባት ባል ለምን ቢል አንተ ልታሟላልኝ አልቻልክማ! የሚል ምላሽ ሰጥታ ባሏን ማሳፈር እንደምትችልና ማሟላት ካልቻለ እንደፈለገች የመሆን ነፃነት ያላት መስሎ ስለሚታሰባት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው በምዕራቡ ዓለም ፍች የሚበዛው ለሃይማኖታዊ አስተምህሮ፣ ለጸና ቤተሰባዊ ትሥሥርና ዘለቄታም ዴንታ የሌላቸው፡፡
በመቀጠል ወደ መላምቴ እሔዳለሁ፡፡ አንደኛው የአየር ንብረት ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የቀጠናው ሀገራት ያሉበት ወይም የሚገኙበት ሥፍራ ነው፡፡ መቸም እንዴት ሆኖ ማለታቹህ አይቀርምና እንዴት ሆኖማ እንዲህ ነው፡- ነገሩን ልብ ብላቹህ ተመልክታቹህ እንደሆነ በደጋና በቆላ የአየር ንብረቶች ክልሎች ወሲብ የመፈጸም ፍጆታና ድግግሞሽ የተራራቀ ወይም የተለያየ ነው፡፡ የወሲብ ፍጆታና ድግግሞሽ በደጋና ቀዝቃዛ ወይም በረዷማ በሆነ የአየር ንብረት ውስጥ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በቆላማው ያለው ግን በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በእኔ ግምት ይህ የሆነበት ምክንያት በደጋው በቀዝቃዛማው ወይም በበረዷማው አካባቢ ያሉ ሴቶች እንበል ምዕራቡ ዓለም ለምሳሌ በአማካኝ ከዓመቱ የሚበዛው ወይም 3/4ኛው ወራት ክረምት ወይም ቀዝቃዛ ጥቂቱ ወራት ብቻ በጋ በመሆኑ በዚህ አካባቢ ያሉ ሴቶች የማይገረዙበትና ስለግርዛት  እንዲያስቡ ያልተገደዱበት፤ አለመገረዛቸውም ችግር ላይሆንባቸው የቻለው፤ ባሕሉም ሊኖራቸው ያልቻለበት ምክንያት የሚገረዘው የብልት አካል ሥራ ወይም ተግባርና የአየር ንብረታቸው ተጣጥሞ ተስማምቶ በመገኘቱ ነው፡፡ እንዴት ሆኖ? ምን ማለት ነው? ብትሉኝ ያ የሚገረዘው የብልት አካል ሥራው ስሜትን ቀስቅሶ ካቀጣጠለ በኋላ ሰውነትን በሙቀት መሙላት ነው፡፡ ታዲያ የበረዷማው ወይም የቀዝቃዛው ዓለም ሴቶች በዚህ ምክንያት የሚመነጨውን ሙቀት በጣም ቀዝቃዛውን የአየር ንብረት ለመቋቋም ወይም ለመከላከልና የሰውነት የሙቀት መጠናቸውን ካለው አየር ጋር ለማስማማት ሰውነታቸው ይጠቀምበታል፡፡ በመሆኑም ከዚህ አልፎ የበዛና ትርፍ ሙቀት ስለማይኖራቸው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የወሲብ አምሮት ስካር ውስጥ የመግባት ሁኔታ አያጋጥማቸውም፡፡ ካጋጠማቸውም በአጭሩ የበጋ ወራት ነው፡፡ ነገር ግን በዚያች አጭር ወቅት ያጋጠማቸውን ነገር እንደ ችግር ቆጥረው በረዥሙና እጅግ ፈታኙ ቀዝቃዛ ወራት ባለውለታቸው ላይ እርምጃ የመውሰድ ውሳኔ ውስጥ አልገቡም፡፡ ወይም ግርዛትን ባሕል እንዲያደርጉ የሚስገድድ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ አልተገደዱም፡፡ እናም አለመገረዛቸው ወቅትን ተንተርሶ የሚጎዳበት ሁኔታ ቢኖርም ጥቅሙ ሸፍኗቸው በልጦባቸው ጉዳቱን ሊረዱ ሳይችሉ ወደዚያም ሳይመራቸው ቀርቷል፡፡
ወደ  እኛው ወደዚህ የግርዛት ቀጠና ወደተባለው አካባቢ ወዳሉ ሴቶቻችን ስመለስ ግን የአየር ንብረቱ ፀሐያማ ሞቃትና ቆላ ነው፡፡ እንዲያውም በቀጠናው ውስጥ ካሉ ሀገሮች ውስጥ ክረምት የሚባል ወቅት የሌላቸውና ዝናብን ከሰማይ ሲወርድ ዓይተው የማያውቁም አሉ፡፡ የአየር ንብረቱ እንዲህ በመሆኑም ያ የመራቢያ አካላቸው የውስጠኛ ከንፈር (ቂንጥር) የሚባለው የብልት ክፍል ስሜትን አቀጣጥሎ ቀስቅሶ የሚያመነጨው ሙቀት ቀዝቃዛውን አየር ለመከላከል ወይም ለመቋቋም ፍጆታ ወይም አገልግሎት ይውላል እንዳይባል አየሩ ሞቃታማና በረሀ እንጅ ቀዝቃዛ አይደለም፡፡ ስለሆነም ያ የመነጨ የሙቀት ኃይል አገልግሎት ላይ ወይም ፍጆታ ላይ ለመዋል በሚፈጥረው ግፊትና ጫና ሴቶቻችንን የስሜት ስካር ውስጥ ይጥላቸውና ያልተገባ ነገር ካገኙት ጋር ወሲብ እንዲያደርጉ ያስገድዳቸዋል የሚበዙትንም ያስፈጽማቸዋል፡፡ ያ የመነጨ ኃይልም አገልግሎት ላይ ወይም ፍጆታ ላይ ውሏልና፡፡ እንደገና ደሞ እስኪያመነጭ ድረስ ዕረፍት ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ ወሲብ ሊፈጽሙና ያንን ኃይል በወሲብ ሊገለገሉበት የሚችሉበትን ዕድል ካላገኙ ግን ጠባያቸው ይለወጥና ጠብ ጠብ የሚላቸው ቁጣ ብስጭትና ኃይለኝነት የማይለያቸው ሥራን በአግባቡ የማይከውኑ አልማጭ አቅል ያጡ ያደርጋቸዋል ወይም በእናቶቻችን አገላለጽ “ዕቃ ይሠብራሉ”፡፡
ይሄንን በአንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ምሳሌ ለማስረዳት ብሞክር ነገሩን በደንብ ግልጽ የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡ አንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ያመረተው ኃይል ፍጆታ ላይ ሳይውል አሁንም እንዲያመነጭ ብናደርገው የተመረተውን የኤሌክትሪክ ኃይል በሚቆጣጠሩና በሚያስተላልፉ ጣቢያዎች ላይ ፍንዳታና አደጋ መከሰቱ የማይቀር ይሆናል፡፡ ስለሆነም የግዴታ የመነጨውን ኃይል ከሥር ከሥር መጠቀም ወይም ፍጆታ ላይ ማዋል የግድ ይላል ማለት ነው፡፡ የእኛም ነገር እንዲሁ ነው፡፡ የመነጨውን ኃይል ለመጠቀም ወይም ፍጆታ ላይ ለማዋል የሚፈልግ ኢንዱስትሪ (ምግንባብ) በሉት ከተማ ወይም ሌላ ተጠቃሚ ከሌለ ትርፉን ኃይል የሚያመነጩትን ኃይል ማመንጫዎችን (ዩኒቶችን) ወይም ተርባይነር (መዘውር) ማጥፋት ወይም እንዳይሠሩ ማድረግ አስፈላጊና ግዴታም እንደሆነ ሁሉ ይህ ሴቶቻችንን ከልኩና ከሚፈለገው በላይ ትርፍ ስሜትና ሙቀት እያመነጨ ችግር ላይ በመጣል የሚያስቸግረውን ውስጣዊ ከንፈርም (ቂንጥር) መቀነስና መመጠን ሴቶችም ከአቅላቸው ጋር እንዲሆኑ እራሳቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ ማገዝ አስፈላጊ ሆናል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ እናት አባቶቻችንም ይህንን ሥልጡን ውሳኔ ነው የወሰዱት ምን ያህል ሳይንሳዊ (መጣቃዊ) እንደሆነ መረዳት አያዳግትም፡፡ ማስተዋል ካልተሳነን በስተቀር በዚህ ውሳኔ ላይ አለመሰልጠን ወይም ድንቁርና ጨርሶ አይታይም ምጥቀትና ልቀት እንጂ፡፡ እንዲህ ዓይነት ባሕል ስላለንም የሚያኮራን እንጅ የሚያሳፍረን አይደለም ጠልቆና አርቆ አስፍቶ የማሰብ የማየት ችሎታ ውጤት ነውና፡፡ አንደኛው መላምቴ ማለትም በአየር ንብረት ምክንያት ነው ብየ የነበረው ይህንን ሲመስል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ማለትም የቀጠናው ሀገሮች ያሉበት ኬክሮስና ኬንትሮስ (Latitude and Longitude) መልክአምድራዊ አቀማመጥ ወይም ቦታ ምክንያት ነው ያልኩትን ደግሞ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
አስተውላቹህት ከሆነ ይህ የግርዛት ቀጠና የሚባለው አካባቢ የተያያዘ ወይም ልክ እንደ አንድ ሀገር ካርታ (ሥዕለ መልክአ-ምድር) ከመሀል ሌላ ሳይካተት አንድ የራሱን የቆዳ ስፋት ይዞ ያለ ቀጠና ነው፡፡ ይህ በአጋጣሚ የሆነ እንዳይመስላቹህ ወይም ደግሞ ይህ የግርዛት ባሕል ከእነዚህ የቀጠናው ሀገሮች በአንዱ ተጀምሮ የመወራረስ ዕድል ስላገኙ እንዳይመስለን እንደዚህ ቢሆን ኖሮማ የዓለም ሕዝብ እርስ በርሱ አንዱ ከአጎራባቹ እየወሰደ እንደሚጋራቸው ብዙ የባሕል ዓይነቶች ሁሉ ይህኛውንም እንደቆየበት ረጅም ዘመንና የቀጠናው ሀገሮች የሥልጣኔና የንግድ ማዕከል እንደ መሆናቸው ሌሎቹም ከእነርሱ እንደወሰዱት እንደሌሎቹ የባሕል ዓይነቶች ሁሉ ይሄኛውንም ባሕላቸው ባደረጉት ነበር፡፡ ሌላው ይቅር ዓለም በሙሉ እንኳን ባያደርገው የቀጠናው የቅርብ አጎራባች ሀገሮች እንኳ ባሕላቸው ሳያደርጉት ባልቀሩም ነበር፡፡
አንድ ሥርዓተ ፀሐይን (solar system) የሚባለውን የሚያጠና የመጣቅ (የሳይንስ) ዘርፍ አለ በዚህ የመጣቅ ዘርፍ ውስጥ ያለ አንድ ንዑስ ዘርፍ ደሞ አለ Astrology (ሥነ ከዋክብት) ይባላል፡፡ ይህ ዘርፍ የሚያጠናው (Astrology፡- the study of the belief that the positions and movements of the stars and planets influence what people do and what happens to them) አስትሮሎጂ (ሥነ-ከዋክብት) ማለት የከዋክብትና የፕላኔቶች (ዐበይተ ከዋክብት) እንቅስቃሴና አቀማመጥ ሰዎች በሚያደርጉትና በሰዎች ላይ በሚሆነው ነገር ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የሚልን እምነት የሚያጠና ዘርፍ ነው ይላል፡፡ ይገርማቹሀል ይህ ትምህርት በእኛው በቤተክርስቲያን ባሕረ ሐሳብና ሥነ-ፈለክ በሚባሉት እንዲሁም ባሕላዊ ዕውቀት ትምህርቶች ሙሉ በሙሉ ዕውቅና ያለው ዕውቀት ነው፡፡ ነገር ግን ትምህርቱ ከቤተክርስቲያን ዓላማ አንፃር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ መሔድ የሚዳዳን ሰው የሚወስድ ወይም ጥንቆላን ለመሰለ የተወገዘ ግብር ለመፈጸም የሚያስችል ሰፊ መንገድ ስላለው በከፍተኛ ጥንቃቄ የተያዘና ብዙም የማይበረታታ ነው፡፡ ትምህርቱ የሚሰጣቸውም ለተመረጡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ላላቸው አቅለኛና ትህርምተኛ ለሆኑት ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም መጣቅያን (ሳንቲስቶች) ራሳቸው  የወሰዱትና በተቻላቸውም መጠን ለመረዳት የሞከሩት ከእኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ምክንያቱም ይህንን ዕውቀት ከመጣቅያን በፊት ገና ድሮ ቀድመን ያወቅነውና ስንሠራበት ስንጠቀምበት የዘመን አቆጣጠራችንንም ጭምር ስንቀምርበት የነበርነው እኛ እንደሆንን ይታወቃልና፡፡ መጣቅ ዕውቀትን ከየትም አያመጣም ነገር ግን ካለው ከነበረው ተነሥቶ የራሱን ጥናትና ምርምር በማድረግ ነው አዳዲስ ነገሮችን ለማግኘት የሚሞክረው፡፡ የሆነውስ ሆነ ይህ ታዲያ ከያዝነው ርእሰ ጉዳይ ጋር ምን ያገናኘዋል? ያላቹህ እንደሆነ ጨርሶ አልተከታተላቹህኝም ማለት ነው በቃ ማቆሜ ነው! አዎና እንዴ! ምን አደከመኝ? ትሰሙኝ እንደሆነ ልብ ብልቹህ ስሙኝ አለዛ ምን አደከመኝ? ‰? ምን? ገብቶናል? ጎሽ! እንዲህ ከሆነማ እንዴት ነው ታዲያ? ይሄ ኬክሮስ ኬንትሮስ የምድር አቀማመጥ ከሥነ-ከዋከብት (astrology) ጋር እያልኩ የለፈለፍኩት  ግጥምጥሞሹ አልገረማቹህም?
ከላይ የግርዛት ቀጠና የተባለውን አካባቢ ልክ እንደ አንድ ሀገር ካርታ (ሥዕለ መልክአ-ምድር) ተያይዞ መገኘቱን ትይዙና የከዋከብትና የፕላኔቶች(ዐበይተ ከዋክብት) አቀማመጥና እንቅስቃሴ ሰዎች በሚሠሩት ወይም በሚያደርጉት በአስተሳሰባቸው እንዲሁም በእነርሱ ላይ በሚሆነው ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል እንደሚለው የመጣቅ እምነት የቀጠናው ሀገሮች እንደ አንድ ሀገር ካርታ ተያይዘው መገኘታቸው ያለ ነገር ወይም ያለ ምክንያት እንዳልሆነ ትረዳላቹህ ማለት ነዋ! አይደለም እንዴ? ይሄም ማለት ደሞ በዚህ ቀጠና ሰማይ ላይ ያሉ የከዋክብትና የዐበይተ ከዋክብት አቀማመጥና እንቅስቃሴ ግርዛትን በተመለከተ በዚህ ቀጠና ውስጥ ባሉ ሰዎች አስተሳሰብ ላይ ከሌላው የዓለም ክፍል የተለየ አቋምና  ሁኔታ እንዲኖረን ከሌሎቹ በተለየ ቀጥተኛ የሆነ ተጽዕኖ አሳድሯል ማለት አይደለም? አለዛማ ያለ እነዚህ መላምቶች የዚህ ቀጠና ሰዎች ከሌላው የዓለም ክፍል ካሉ ሰዎች በወሲባዊ አስተሳሰብ የተለዩ ሊያደርጋቸውና ማኅበረሰቡም ግርዛትን ዋና መፍትሔና የባሕሉ አካል አድርጎ ሊይዘው የሚችልበት አንድም ምክንያት ባልኖረም ነበር ባይ ነኝ፡፡ የከዋከብትና የዐበይተ ከዋክብት አቀማመጥና እንቅስቃሴ በቀጠናው ያሉ ሰዎች በሚያደርጉትና በእነርሱ ላይ በሚሆነው ተጽዕኖ ስላላቸው ነው የተለያዩ ሀገር ሰዎች በየሀገራቸው የጋራ ባሕርይና መገለጫ ይዘው የእንትን ሀገር ሰዎች ብስጩዎች ናቸው፣ የእንትን ሀገር ሰዎች ደጎች ናቸው፣ የእንትን ሀገር ሰዎች ጀግኖች ናቸው ወዘተ. እየተባለ የሚነገረውና የሚባለውም ሆኖም የሚገኘው፡፡ ለማንኛውም ሁለተኛው መላምቴም በዚሁ ይቋጫል፡፡
የህክምና ባለሙያዎች የሴት ልጅ ግርዛት ያስከትላል የሚሏቸው ችግሮች
1ኛ የወሲብ ፍላጎትና ስሜት ማጣት (dormancy) እና
2ኛ በወሊድ ጊዜ የብልት አለመለጠጥ ችግሮች ናቸው፡፡
ነገር ግን እነኝህ ሁለት ችግሮች እኔ እያወራሁለት ያለውና ብንቀበለው ብንቀጥልበት ጥሩ ነው እያልኩ የምደግፈው የግርዛት ዓይነት ችግሮች አይደሉም ጨርሶ አይደሉም፡፡ ነገር ግን የግርዛቱን ዓይነት የብልት ትልተላ (genital mutilation) ሲሉ የሠየሙት የግርዛት ዓይነት ችግሮች ግን ናቸው በትክክልም ናቸው፡፡ ከላይ ለገለጽኩት ዓይነት ግርዛት ግን ሊሆኑ የማይችሉባቸውና የህክምና ባለሞያዎች ገለፃ ሐሰት የሚሆንበት ምክንያት፡-
በግርዛቱ የሚሠራው ሥራ የማመጣጠን ወይም ልከኛ የማድረግ ሥራ እጅግ ጨርሶ የማስወገድ የማንሣት ሥራ የሚሠራ ባለመሆኑ፤ ስላላጋጠሙህ ነው ካላላቹህኝ በስተቀር ካነጋገርኳቸው በርካታ የተገረዙ ሴቶች የተረዳሁት ይሄንን የባለሞያዎች አባባል  ጨርሶ የሚያረጋግጥ ሆኖ ባለመገኘቱ፤ ማለትም በወንዱ ወሲብ የመከወን ችሎታ ማነስ ካልሆነ በስተቀር ያለመርካት ችግር ችግራቸው እንዳልሆነ አረጋግጠውልኛል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ችግር ያጋጠማት ካለች እንደሚታወቀው ያልተገረዙ ሆነውም በወሲብ ያለመርካት ችግር ያለባቸው ሴቶች አሉና ከዚሁ ጋር አብሮ የሚታይ ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ላይ ለተገለጸው ችግር ደግሞ አሁንም እኔ ከምለው የግርዛት ዓይነት ጋር የማይገናኙ ነገሮችን ለማገናኘት በመሞከሩ እያዘንኩ አፈማኅፀን (የማኅፀን በር) በወሊድ ጊዜ አልለጠጥም ይላል ምክንያቱም በግርዛቱ ምክንያት ግርዛቱ የተፈጸመበት አካባቢ ለምጽ ስለወጣበትና የለምጽ አካል ደግሞ የሞቱ የቆዳ ሴሎች(ሕዋሶች) ሥፍራ በመሆኑ አልለጠጥም ይላል፡፡ ሴት ለወሊድ በምትዘጋጅበት ጊዜም ሌላው የብልቷ ክፍል እየተለቀ እየሰፋ ሲሔድ የተገረዘው ቦታ ግን በዚህ የተነሣ ሳይለጠጥ ሳይሰፋ በመቅረቱ አደጋው ይከሰታል ይላሉ፡፡ እርግጥ ነው በቃጠሎ ወይም በስለት የተጎዳና ለምጽ የወጣበት ቆዳ ወይም አካል የሞተ ቆዳ ነው ሲዳስሱት አይሰማውም በአካል እያደግን ስንሔድ ያ የለምጽ አካል ግን እድገት አያሳይም ይህ እውነታ ግን በሚገርም ሁኔታ የሴት ልጅ የብልት አካል የሆነው ቂንጥርንና የወንድ ልጅ የብልት አካል የሆነውን ሸለፈት አይመለከትም፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ የወንዶች ብልት መጠን ሁሉ በሕፃንነታችን ጊዜ ስንገረዝ በነበረችበት መጠን እየተወሰነ እየተገደበ በቀረ ነበር፡፡ እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የወንድ ልጅ ብልት ሲገረዝ በግርዛቱ ምክንያት ሸለፈቱ ተቆርጦ ሲጣል የተቆረጠበት አካባቢ በመቆረጡ ምክንያት ለምፃም ሆኖ አላድግም አልሰፋም አልለጠጥም ሳይል የየወንዱ ብልት ሁሉ ተፈጥሮው በሰጠው መጠን ያድጋል፡፡ ያ የተቆረጠው አካባቢም ስሜት አልባ አይሆንም እንዲያውም ከሌላው የብልት አካል ይልቅ የወሲብ ስሜት መንሸራሸሪያ ያ ቦታ ነው፡፡ በሴቶችም በኩል ያለው ይሄው ነው ነገሩን መድገም ካልሆነ በቀር ልዩነት የለውም፡፡ እንዲህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ የወንዶችና የሴቶች ተገርዘው የሚጣሉ የብልት አካላት ሸለፈትና ቂንጥር በተፈጥሯቸው እንደሌላው የሰውነት አካላት በስለት በመቆረጥ በለምድ የሚጠቁ አለመሆናቸውና ፈጣሪ ለዚሁ ያመቻቸው በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም በወሊድ ጊዜ የማኅፀን በር ያለመለጠጥ ችግር የዚህኛው የግርዛት ዓይነት ችግር አይደለም “የብልት ትልተላ” በመባል የሚጠራው የግርዛት ዓይነት እንጅ፤ ምክንያቱም ውጫዊ የሴት ልጅ ብልት(የእምስ) አካል የሚባል አንድም ነገር ሳያስቀሩ እንዳለ ሙድድ አድርገው ስለሚያነሡትና በለምጽ ስለሚጠቃ ይህ ችግር እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ከዚህኛው የግርዛት ዓይነት ውጭ ያሉቱን ሁለት የግርዛት ዓይነቶች ግን የዚህ ችግር መንስኤ አይደሉም፡፡ ይሄም በመሆኑ ነው እናቶቻችን ከሰባት እስከ ዐሥራ ሁለት ልጆች ድረስ ለዚያውም ዘመናዊ የሕክምና እርዳታ በሌለበት ያለ ኦፕራሲዮን (ቀዶ ሕክምና) በመውለድ ትውልዳችን ቀጥሎ አሁን ያለንበት ደረጃ ልንደርስ የቻልነው ከዚያም አልፎ እንደሚሉት የሕዝባችን ቁጥር አሳሳቢ የሆነበት ደረጃ የደረሰው፡፡ የማይገረዙት የምዕራቡ ዓለም ሴቶች ግን ባለሞያዎች እንደሚሉት አለመገረዛቸው ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅን በማኅፀን በር በኩል ያለ ችግር  እንዲወልዱ ያደርጋቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ ውጤቱ ግን ከስንት አንድ ካልሆነ በስተቀር እየወለዱ ያሉት በሆድ በኩል በቀዶ ማዋለድ (በኦፕራሲዮን) ዘዴ ነው፡፡
እርግጥ ነው ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገሮች ውስጥ ያለውን የእናቶች ሞት (maternal mortality rate) ሀገራችንን ጨምሮ ከመቶ ሽህ ወላዶች 200-300 እናቶች በወሊድ ጊዜ የሚሞቱ ሲሆን፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ሀገሮች ከሦስት አራቱ በስተቀር ሌሎቹ ግርዛትን የማያውቁ ከመሆናቸው የተነሣ በግርዛት ምክንያት እናቶች ይጎዳሉ ሊባሉ የሚቻሉባቸው ሀገሮች አይደሉም፡፡ በዚህ ላይ እናቶች በወሊድ ምክንያት የሚሞቱባቸው ሀገሮች ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራት ብቻ አይደሉም፡፡ በአደጉት ሀገራትና ግርዛትን ጨርሶ በማያውቁት ሀገሮችም እናቶች በወሊድ ምክንያት ይሞታሉ፡፡ ለምሳሌ ጀርመንን ብናይ በጀርመን በወሊድ ምክንያት ከመቶ ሽህ ወላዶች ከ20 ያላነሱ እናቶች ይሞታሉ፡፡ በጠቅላላው አውሮፓም በአማካኝ 13 እናቶች ከመቶ ሽህ እናቶች ይሞታሉ፡፡ ይህን ቁጥር ከእኛ ጋር ስናነጻጽረው አነስተኛ ይመስላል ነገር ግን ሕክምናው እጅግ በተራቀቀበትና ለሁሉም ተደራሽ በሆነበት ሀገር መሆኑን ስናይና በእኛ ደግሞ ያለው ነገር ሁላችንም የምናውቀውን ያህል መሆኑ እጅግ አሳሳቢው የእነርሱ እንጅ የእኛ አይደለም፡፡ እንዲህ ስል በወሊድ ምክንያት እየሞቱብን ያሉ እናቶች ሞት አሳሳቢ አይደለም እያልኩ እንዳልሆነ ትረዱኛላቹህ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በእነርሱ ያለው የህክምና ጥራትና ተደራሽነት ለእኛ ቢሆን ኖሮ አንዲትም እናት አትሞትም ነበር ማለት ባይቻልም እንኳ አኀዙ ግን ከእነሱ በእጅጉ የተሻለ በሆነ ነበር፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰተውን ይህንን አደጋ አጋጣሚውን በመጠቀም ከግርዛት ጋር ማለትም እያወራሁለት ካለሁት ዓይነት ግርዛት ጋር እያያያዙ የተሳሳተ መረጃ መስጠት በጣም ስሕተት ነው፡፡ በሀገራችን በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች በምጥ ጊዜ የባለሙያ እገዛና ተገቢ የሆነ የህክምና ማዕከላት ባለማግኘት እንደሆነ ያሉት መረጃዎች የሚያሳዩት እውነታ ነው፡፡ የዚህ አደጋ መንስኤም በአብዛኛው በተለይ በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ከመድረሳቸው በፊት እንዲያገቡ ስለሚደረጉና አካለመጠን ሳያደርሱም እርግዝና ስለሚከሰት አካላቸውም ጽንስን ተሸክሞ ለመውለድ ብቁ ወይም ዝግጁ ካለመሆኑና ከዚሁ ጋር ተያይዘው በሚፈጠሩ ችግሮች ለህልፈት እንደሚዳረጉ ይታወቃል፡፡ እናም ያልኩት ዓይነት ግርዛት ያስከትላቸዋል ተብሎ ለማስተው ስለተፈለገ ብቻ እያምታቱ የሚናገሩት ነገር ሀቅን ያልተመረኮዘና በስመ ግርዛት ሁሉንም በአንድ በማጠቃለል የተደረገ ፍረጃ ተገቢ አለመሆኑን አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
እንግዲህ ያለው እውነታ ይሄው ነው፡፡ ይሄም ሆኖ ግን ምናልባት እንዴ! ጥቂትም ቢሆን በግርዛቱ ወቅት ለምን ይመመኝ? ለምን ደም ይፍሰሰኝ? ለምንስ የብልቴ አካል (ቂንጥሬ) ይቆርመምብኝ? ሙሉው ሳይነካ ይቀመጥልኝ እምብየው በቃ! አልፈልግም! እንኳን አበጀሁ! እሰየሁ ይሁን! የምትል ሴት ብትኖር አይ ይሄውልሽ እኅታችን እንዴት መሰለሽ በቃ ይሄ ሴቶቻችን እንደ ዜጋ ሁሉ የሀገራችንንና የኅብረተሰባችንን ህልውና ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ልትከፍሉት የሚገባ ጥቂት መሥዋዕትነት ስለሆነ በዘመናችን ያላቹህ ሴቶቻችን ምናልባት ባትፈልጉም የግድ ልትቀበሉት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ምነው? የሀገራችንንና የሕዝባችንን ነጻነት አንድነትና ህልውና ለማስጠበቅ ሲሉ ጀግኖች እናት አባቶቻችን ድንበሯ ላይ አላለፉም እንዴ? እነሱ ምን ይበሉ? ለማንስ ሲሉ ነው የመጨረሻውን መስዋዕትነት መተኪያ የሌላትን አንድ ነፍሳቸውን በመስጠት ዋጋ የከፈሉት? አንች ጭራሽ እንትኔ አይቆርመምብኝ ትያለሽ? አንችን እራስሽንም ሕይዎትሽን የሚጎዳ ሆኖ ከተገኘስ እንዴት ይደረግ? ባለመገረዝሽ በሚመጣ ጦስ እናት አባቶቻችን የከፈሉትን መስዋዕትነት ከንቱ ማድረግ ትፈልጊያለሽን? ወይስ ሀገርንና ሕዝብን ከትርፍ የወሲብ ስሜት አሳንሰሽ ታያለሽ? ነገር ግን ‰ረ ለምን? ብለሽ ለሀገር ለሕዝብ ሲሉ ሕይወታቸውን የከፈሉ አሉ እኔ ለዛውም ለገዛ ጥቅሜ ክብሬና ለሰብእናየ ለተረጋጋ ለጤናማና ለተገቢ ማንነቴ ሲባል ለሚደረግ ለዚህች ቀላሏ ነገር! ካልሽ ደግሞ ይህን በማድረግሽ ብቻ ጀግኖች እናት አባቶቻችን ለሀገራችን የከፈሉትን መስዋዕትነት ያህል ከከፈልሽ ይቆጠራል፡፡ ለራስሽ ለሀገርና ለሕዝብም ጀግና ባለውለታ ነሽ፡፡
ይሄ ከሆነ ታዲያ እንደ ወንዶቹ ሁሉ የሴቶቹ ግርዛት ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ አልታዘዘም ወይም ለምን ሃይማኖታዊ ተቀባይነትና ዕውቅና አላገኘም?
እውነት ነው ተገቢ ጥያቄም ነው ይህ ያልሆነበት ምክንያት እንደሚታወቀው አንድ ሃይማኖታዊ ትእዛዝ ወይም ድንጋጌ በመጽሐፍ ቅዱስም ይሁን በሌሎች የሃይማኖት መጻሕፍት ሰዎች ወይም አማኞች እንዲፈጽሙት ከታዘዘ በየትኛዉም የዓለም ክፍል ያለ ሁሉ በግድ መፈጸም ሊኖርበት ነው፤ ይሄም በመሆኑ የሴት ልጅ ግርዛት ሃይማኖታዊ ግዴታ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ምክንያቱም መገረዙ ወይም አለመገረዙ የሚጠቅማቸው እንዳሉ ሁሉ የሚጎዳቸውም ወይም የሚያጎልባቸውም አሉና የሚጎዳቸው እንዳሉ ሁሉ የሚጠቅማቸውም አሉና እንዲህ በሆነበት ሁኔታ የሴት ልጅን ግርዛት ሃይማኖታዊ ግዴታ እንዲሆን ማድረግ አይቻልም፡፡ አንድ ድንጋጌ ሃይማኖታዊ ትእዛዝ  የሚሆነው በሁሉም የዓለም ክፍል ያሉ ሰዎችን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር የሴት ልጅን ግርዛት ሃይማኖታዊ ግዴታ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡ ነገር ግን የሴት ልጅ ግርዛት ለሁሉም ትክክል አይደለም ማለቱ ግን አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሴት ልጅ ግርዛት የተነሣበት አንድም ቦታ የለም መገረዟ ተገቢ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ አልተጻፈም፡፡ ለዚህ ነው ትክክል ነውም አይደለምም የሚል ቃል በሃይማኖት መጻሕፍት ውስጥ ማስፈር ያላስፈለገው፡፡ እናም ውሳኔው ለሰዎች እንደየሚኖሩበት አካባቢና ሁኔታ የተተወ ነው ማለት ነው፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ነገሩ በይፋ ሃይማኖታዊ ተቀባይነት አይኑረው እንጅ ውስጥ ውስጡን ግን እንደሚሠራበት ይታወቃል፡፡ ሃይማኖት በተዘዋዋሪም ቢሆን ይህ እንዲሆን የራሱን ተጽዕኖ እንዳሳደረ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ቀደም ሲል እናት አባቶቻችንን ግርዛት ለምን እንደሚፈጽሙ ስንጠይቃቸው የሰጡንን ምላሽ አድምጠናል፡፡ ያልተገረዘች ሴት ያጋጥማታል በማለት የዘረዘሯቸው ነገሮች ሁሉ በሃይማኖት  አስተምህሮ አንፃር ሲታዩ ኃጢአት በደል ወይም ርኩሰት የሚባሉ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ሃይማኖቱ  በተዘዋዋሪ ግርዛት እንዲኖር ይሰብካል ወይም ያበረታታል ማለት ነው፡፡ ሴቶች እንዲህ እንዳይሆኑ ሃይማኖት የሚፈልግ ከሆነ እንዲያ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸውን መፍትሔ ወይም መላ መኖሩን መደገፉ የማይቀር ይሆናል፡፡ በይፋ አያረጋግጥ እንጅ፡፡
በሀገር ቤት ምን እንደሚደረግ አውቃለሁ መሰላቹህ? ለካህን ሚስት ሲመረጥ ድንግል መሆኗ እንዳለ ሆኖ የተገረዘች መሆኗ ይመረጣል፡፡ ለምን ሲባልም እህ! ደግሞ ወስላታ ወይም ወደ ሌላ ወንድ ሔዳ ክህነቱን ታስፈርሰው እንዴ? ይላሉ፡፡ እሷ ከሌላ ወንድ ደርሳ ይሄንን ቄሱ ባሏ ሳያውቅም እንኳን ቢሆን ከዚያ በኋላ እሱ ቢደርስባት ወዲያውኑ ክህነቱ ይፈርሳል፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ የመቅደስ አገልግሎትን መስጠት የማይችል ይሆናል፡፡ በመሆኑም ለዛ ደረጃ ለመድረስ ስንት የደከመውና የተንከራተተው ካህን ሚስቱ በሠራችው በአንዲት ቅጽበታዊ ስሕተት እንዲህ ዓይነት ሕይወቱን የእድሜ ልክ ልፋቱንና ሰማያዊ ተስፋውን ከመሠረቱ ለሚነቅል ችግር እንዳይዳረግ አስቀድመው ሚስት የሚያጩለት ወላጆቹ ወይም ዘመድ ጎረቤቶቹ ከባድ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ የተገረዘች መሆኗንም ሥጋት ከመቀነስ አኳያ በጣም ጠቃሚ አድርገው ያዩታል፡፡ ስለዚህ ሃይማኖት በባሕል ባሕልም በሃይማኖት ላይ ተጽዕኖአቸውን አሳድረዋል ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ሁኔታ ግን ሊኖር የሚችለውና የሚጎላው ከየግርዛት ቀናጣ ሀገሮች ውስጥ በሀገራችን ነው ማለትም ግርዛትን ባሕል አድርጎ ለመቀጠል ሃይማኖት ተጽዕኖ ከማድረጉ አንፃር ማለቴ ነው፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አባባል ወይም መረጃነት ከጌታ ልደት በፊት እግዚአብሔርን ያመልኩ የነበሩት ሀገሮች ሁለት ብቻ ናቸውና ኢትዮጵያና እስራኤል፡፡ በእርግጥ ሮም፣ ግሪክ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ፣ ፋርስ፣ ባቢሎን ሌሎችም የተጠቀሱበት ሁኔታ አለ ነገር ግን እነሱ የተጠቀሱት ዜጎቻቸው እግዚአብሔርን በማምለካቸው ሳይሆን ከሀገራቸው ከእስራኤል በንግድና በስደት ሔደው መኖሪያቸውንም በነዚያው ሀገሮች አድርገው ምኩራቦቻቸውንም በዚያው ሠርተው እግዚአብሔርን ያመልኩ ከነበሩት አይሁዶች የተነሣ ወይም አማካኝነት ነው፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን እንደ ሀገርና ሕዝብ እግዚአብሔርን አምላኪ እንደሆንን ከዚያም ባሻገር እግዚአብሔር በትን. አሞጽ 9÷7 ላይ ከክርስቶስ መወለድ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት እንደተናገረው ከእስራኤላዊያንም ወይም ከአይሁዳዊያንም በልጠን ታይተናል፡፡ ‹‹የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን?›› ይላል እግዚአብሔር እንግዲህ ከጥቅሱ እንደምንረዳው እግዚአብሔር እነሱን ከእኛ አሳንሶ የሚያያቸው እንዳይመስላቸው እንደኛ አድርጎ እንደሚያያቸው በማጽናናት የተናገረው ቃል ነው፡፡ ስለሆነም ምን ለማለት ነው ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት የተቀበልነው አታመንዝር የሚለው የኦሪቱ ሕግ ግርዛትን ባሕላችን አድርገን እንድንቀጥል ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ምክንቱም ግርዛትን የምንፈጽምበት ምክንያት ሴቶቻችን ንጽሕናቸውን ቅድስናቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ወይም ኃጢአት እንዳይሠሩ ለማድረግ ነውና፡፡ በመሆኑም ነው ከቀጠናው ሀገሮች ግርዛትን ባሕላችን አድርገን እንድንቀጥል ካበቁን ምክንያቶች ይሄኛው የተለየን ያደርገናል ማለቴ፡፡
ምዕራባዊያን እኛን ግርዛትን እንድናስቀር መገፋፋታቸው መጫናቸው ከምን በመነጨ መንፈስ ነው?    
ነጮቹ ሳይገባቸው ይሁን ገብቷቸው ነገሩን ሳያውቁት ይሁን ሆን ብለው በጣም እያሳሳቱን ነው፡፡ በሚያውቁትና በገባቸው ጉዳይ ላይ በሆነ ባልከፋ፡፡ ነገር ግን የሴት ልጅ ግርዛት ገና ለእኛ ባዕድ ነገር ነው ወይም አናውቀውምና ብለው የአንድ አካባቢ ሕዝብ ባሕል ነው በሚል ብቻ እናውቅላቹሀለን ብለው ማስገደዳቸው እኔ እንዲያው ይቅርታ አድርጉልኝና ሸርና ተንኮል ያለበት መስሎ ይሰማኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ይሄን ካላደረጋቹህ ብለው መወትወታቸው፣ ወጥረው መያዛቸው እኔ የጤና አይመስለኝም፡፡ እኛ እንደተጎዳን አስበውልንና አሳዝነናቸው ነው እንዳልል ይሄን ያህል ሰብአዊነቱ ካላቸው ምነዋ ታዲያ ከዚህ ይልቅ ሽህ ጊዜ እጥፍ ለእኛ የከፋና የከበደ የጎዳንና እያሰቃየን ያለ እርዳታቸውን ድጋፋቸውን ትብብራቸውን የሚያሻ ዋና ጉዳይ እንዳለ እያወቁ ምነዋ ታዲያ በዚያ ላይ ድጋፍ ሰጥተውን ከድህነትና ከረሀብ አዙሪት እንድንወጣ እራሳችንን እንድንችል አላማድረጋቸው? የእውነት እኛን የመርዳት ቅን ልብ ካላቸውስ ሁሉም ነገር አቅሙ ገንዘቡ ዕውቀቱ ወዘተ. አላቸውና ሳይቸገሩ ከችግር ሊያወጡን በገደዳቸው ነበር፤ ልክ አሜሪካ አውሮፓን እንደታደጉ ሁሉ ማለት ነው፤ እዚህ ላይ ግን ማተኮርና ገንዘብ መርዳት አይፈልጉም ለዚህ ጉዳይ ከተባለ እንኳን እርዳታ ብድር እንኳን መስጠት አይፈልጉን፡፡ እነሱ ገንዘብ የሚመድቡለት ብድርም እርዳታም የሚሰጡበት ጉዳይ ላይ ላዩን ደግ በሚያስመስላቸውና የዕለት ምሥጋና በሚያሰጣቸው ቦታ ላይ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እነሱ ለአፍሪካ ይሄንን ዓይነት ድጋፍ የማድረጋቸው አስፈላጊነት የሰብአዊነት ጉዳይ አይደለም ሊከፍሉት ከሚገባ ዕዳ አንፃር እንጅ፡፡ ምክንያቱም ከአፍሪካ በዘረፉት አንጡራ ሀብቷና በባሪያ ፍንገላ ባጋዙት የውድ ልጆቿ ኃይል ለዚህ በቅተዋልና፤ እርግጥ ነው ተርበን በተቸገርንበት ጊዜ ረድተውናል ነፍሳችንንም አትርፈውልናል፡፡ ያኔ እንባ እየተናነቀን አመስግነናቸዋል፡፡ ነገር ግን ምን ነው በቀረብን ኖሮ የምንልበት ጊዜ ደግሞ ይመጣል፡፡
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ወደ ታች ትረዱታላቹህ፡፡ ሲራቡ ረዳናቸው አተረፍናቸው ይላሉ ቀድሞውኑ ግን እንድንራብ እንድንደኸይ ወይም ከድህነት እንዳንወጣ እንዳንሠራ ያደረገንና እያደረገን ያለው ማን ሆነና? ዛሬም ቢሆን ነገሮች ለገቡት ሰው በእያንዳንዱ  ቸርነት በሚመስለው ሥራቸው ውስጥ ሰይጣናዊ ተንኮላቸውና ክፋታቸው ይታየዋል፡፡ ከዐሥር ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ሬድዮ (ነጋሪተ-ወግ) እና ቴሌቪዥን (ምርዓየ-ኩነት) በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ የተለቀቀ አንድን ዜና ላስታውሳቹህ፡፡ ዜናው በአጭሩ ፓርቲኒየም ስለሚባል አደገኛ አረም የሚያወራ ዜና ነው፡፡ ይህ አደገኛ አረም ከእርዳታ እህል ጋር እንደገባም ዜናው ጨምሮ ይናገራል፡፡ አረሙ በቀላሉ በከብቶች ኮቴና በመኪና ጎማም ከቦታ ወደ ቦታ የመዛመት የተለየ ባሕርይ በመያዙ ምክንያት መላ ሀገራችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያዳርስ ችሏል፡፡ ይህ አረም አደገኛ መርዝ ስላለው ሊነቅለው የሞከረውን ሰው እጅና ሰውነት ያቆሳስላል፣ዓይን ያጠፋል፣ ከብቶች ሲመገቡት አፋቸውን ያቆሳስላል ወተታቸውን እንደ እሬት አምርሮ ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል፡፡ ከሁሉም ጉዳቱ ደግሞ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ እንዲያሽቆለቁል ማድረጉ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ክፋቱ ተነግሮ የማያልቅለትና ለሀገር መዓት የሆነን አረም ነጮቹ አዝነውልን ከረሀባችን እንዲታደገንና ነፍሳችንን እንዲያተርፍልን ከላኩልን የእርዳታ እህል ጋር ቀላቅለው ላኩልን፡፡
እኔ ነጮቹ ይህንን አውቀው ወይም ሆን ብለው እንዳደረጉት አረጋግጥላቹሀለሁ፡፡ ጠንቁየ፣ ሰልየ ወይም መረጃ ያቀበለኝ ኖሮ አይደለም ያለውን ነገር በመመርመር እንጅ፤ እንዴት? እንደዚህ፡-
እንደሚታወቀው የምዕራባዊያኑ የእርሻ ምርት ሒደት (Agro processing) አረም ከሰብሉ ጋር አድጎ ጭራሽም የራሱን ፍሬ እንዲያፈራ አይደለም እንዲበቅል እንኳን የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ቢበቅልም እንኳ እንዲያድግ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ይሄንን አንድ በሉልኝ ሌላው ደግሞ በጣም የሚገርማቹህ በእርዳታ የመጣን እህል ብትዘሩት አይበቅልም፡፡ ለምን መሰላቹህ ነጮቹ እህሉን እንድንበላው እንጅ እንድንዘራው ስለማይፈቅዱ ስለማይፈልጉ ብንዘራው እንዳይበቅል ቀቅለው ነው የሚልኩት፡፡ በመሆኑም ያ ክፉ አረም እንዲያው ግድ የለም ተጠራጣሪ አንሁን እንበልና እያወቁ ሳይሆን ሳያውቁ አብሮ በቅሎ አብሮ ታጭዶና ተወቅቶ ብንል እንኳ እህሉን ሲቀቅሉት አብሮ ይቀቀልና እንደ እህሉ ሁሉ እሱም የመብቀል ዕድል ሳያገኝ በቀረ ነበርና፡፡ ይሄንን ሁለት በሉ ሦስተኛው ደግሞ ለእኛ በጣም ያዝናሉ ብለን እናስብና እናም እነኝህ ለእኛ በጣም አዛኝ ሰዎች የዚህን ፓርቲኒየም የሚባል አረምን አደገኛነት ዕያወቁ ይህ አረም የሞላበትን እህል እንዳለበት እያወቁ መላካቸው ከምንጠቀመው ይልቅ የምንጎዳው እጅግ የሚበዛ መሆኑን እያወቁ እነዚህ ሰብአዊነት የሚሰማቸው ደጋግ ሰዎች ይሄን በመገንዘብ ሊልኩት አይችሉም ነበርና፡፡ ነገር ግን ያደረጉት ሆን ብለው ነውና የክፋታቸው ክፋት እህሉን እንዳይበቅል ከቀቀሉት በኋላ ይሄንን  አደገኛ አረም ቀላቅለው ላኩት፡፡ ይሄው ዛሬ የሀገራችንን ደካማና ኋላቀር ግብርና በዚህ ችግሩ ላይ እንዲህ ዓይነት ፈተና ጋርጠውበት ከድጡ ወደ ማጡ አድርገው ዓይተነው ለማናውቀው ዓይነት አረንጓዴ እረሀብና እልቂት ዋዜማ አድርሰውናል፡፡ ግን ለምን? ምንስ አደረግን? ምን ያህልስ ሰይጣን ቢሆኑ ነው?
ይሄ ብቻ አይደለም አሁንም በተደጋጋሚ በዜና ላይ የተሰማ ጉዳይ ነው የማስታውሳቹህ አንድ በከተሞች ላይ ‰ረ አሁንስ በገጠርም እየተስፋፋ ነው:: ነገርየው ዛፍ ነው ዛፉ የሚያምር ቀይ አበባ አለው፡፡ ለአበባውና ቶሎም ስለሚያድግ ለጥላው እያለ ሰው እየወሰደ እየተከለው በአጭር ጊዜ በተለይ በከተሞች በስፋት ለመታየት በቅቷል፡፡ ይህ ዛፍ የገባው ከውጭ ሲሆን ሕዝቡ ያገኘውም ከችግኝ ጣቢያዎች ነው ችግኝ ጣቢያዎች ደግሞ ያስገቡት በእርዳታ ከውጭ ነው፡፡ አደገኛነቱ ታዲያ ምንድን ነው? ካላቹህ በዚህ ዛፍ አበባ ላይ አበባውን ለመቅሰም ያረፈች ንብ ካረፈችበት አበባ ላይ አትነሣም ወዲያውኑ ትሞታለች አበባው መርዛማ በመሆኑ፡፡ ይህ ዛፍ አበባ በሚያወጣበት ወይም በሚያብብበት ወቅት ወደ ዛፉ ሥር ብትመለከቱ መዓት የንቦች አስከሬን ታገኛላቹህ፡፡ ሀገራችን በንብ ሀብቷ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ዐሥረኛ ደረጃ እንዳላት ይነገራል ከዚህ አደገኛ ወይም መርዛማ ዛፍ አደጋ በኋላ ግን ጥናት ቢደረግ በእርግጠኝነት ይህ ደረጃዋ ወደታች ሊያሽቆለቁል እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ እነርሱም የፈለጉት ይሄንን ነውና፡፡
ሀገራችንንና ሕዝባችንን ለመጉዳት ያበቃልናል ብለው ከፈጸሟቸው ሌላኛው ክፋታቸው ደግሞ ሃይማኖት እያሉ አዲስ እግዚአብሔር ወይም ፈጣሪ የመጣና አዲስ ሃይማኖት የሰጠ ይመስል የሌላቸውን ያልተመሰከረላቸውን የማይኖሩበትንም ሃይማኖታዊነት ለሥውር ሰይጣናዊ ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሲሉ በየቀኑ በሚፈጥሩት ሃይማኖት መሰል ድርጅቶች ስንት የዋሀን እኅት ወንድሞቻችንን ማንነታቸውን እንዲጠሉ ከማንነታቸው እንዲኮበልሉ ከቆዳቸው በስተቀር ኢትዮጵያዊነት እንዲከዳቸው እንዳይሰማቸው ጭራሽም የራሳቸው ለነበረው ማንነታቸው ጠላቶች እንዲሆኑ ከማድረጋቸው ባሻገር አብዛኞቹን ለሥነ-ልቡናና ሥነ-አእምሮ እክል የተዳረጉ ንኮች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ እንዳያያዛቸውም ብዙዎችን ሌላው ቀርቶ ለራሳቸው እንኳን የማይጠቅሙ ከተለምዷዊው (normal) አስተሳሰብ የወጡ ሥራ በሚያስጠላ የሥነ-ልቡና ችግር የተጠቁ “ዜጎችን” ያመርቱልናል፡፡ እንግዲህ የክፋትና ጭካኔያቸው ደረጃ እዚህ ድረስ ነው፡፡ ሲበዛ ርኩሶች ናቸው፡፡ የሚገርመኝ ነገር ግን በዚች በዚች የቀኑብን ሌላ ሌላ ቢኖረን እንዴት ሊሆኑ ነበር? ምንስ ያደርጉን ነበር? ደግሞም እግዚአብሔር ይመስገንና አለን፡፡ ደህይተን እንድንቀር የሚታገሉት ይሄንን ሀብት እንዳንጠቀም ለማድረግም ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች እንግዲህ የተደረሰባቸው ናቸው፡፡ ይታያቹህ የጭካኔያቸው ጭካኔ በዚህ ሊናገሩት በሚያስቸግር ድህነታችን ላይ እንዲህ ዓይነት የክፋት ዓይነት በእኛ ላይ መፈጸም ምን ሊባል ይችላል?፡፡ ያልደረስንባቸውስ ምን ያህል ሰይጣናዊ ክፋት አድርገውብን ይሆን? በተለይም ዛሬ ዓለም በኪስ ተይዛ በምትገባ በካይ የባዮ ቴክኖሎጂ (የሥነ-ሕይዎት ኪነ-ብጀታ) ብክል ቅንጣት የአንድን ሀገር ሥነ-ምኅዳር(Ecology) እንዳልነበረ ማድረግ በሚቻልበት ዘመን በእንደነዚህ ዓይነቶች አረመኔዎች ሥነ-ምኅዳራችን ምን ያህል ሊጎዳ እንደሚችን መገመት ይቻላል፡፡ እንግዲህ ይሄን ያህል ናቸው፡፡ ዓይኖቻቸውን እያቅለሰለሱ አጃቸውን ሲዘረጉልን የደጎች መጨረሻ ይመስላሉ፡፡ እናመሰግናቸዋለንም በፈገግታቸውና በኃዘን በሰመጠ ስሜታቸው የደበቁትን ሰይጣናዊ ክፋት ባለማወቅ፡፡
በመሆኑም እንግዲህ ከዚህ እርሱሳዊ ሰብእናቸውና አስቀድሞ በጥልቀት ካየነው ከሴት ልጅ ግርዛት ጋራ ከተያያዙት ሐቆች አንፃር በሀገራችን ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ግርዛትን ለማስቀረት ሕገ ወጥ ድርጊት ተደርጎ እንዲቆጠር ያደረጉትን ሩጫና ጥድፊያ እኔ በበጎ ዓይን ላየው አልቻልኩም፡፡ ምን ይታየኛል መሰላቹህ ሰዓት የተሞላ ፈንጅ (Time bomb)ላይ ያስቀመጡን መስሎ ይሰማኛል፡፡ መግቢያዬ ላይ የሴት ልጅ ግርዛት መቅረት ጉዳይ ጊዜ ጠብቆ እንዴት ባለ ሁኔታ ማኅበራዊ ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል መግለጼን ታስተውሳላቹህ? ስለሆነም እንዲያው ነጮቹ ስላሉ ብቻ አቅማችን የፈቀደውን ያህል እንኳ ጥቅምና ጉዳቱን ሳንመረምር ተቀብለን መተግበሩ በኋላ ልንመልሰው ልናስተካክለው ልንቀለብሰው የማንችለውን ችግር ይፈጥራልና እዚህ ላይ ወገን እጅግ ልንጠነቀቅ ይገባል ማለትን እፈልጋለሁ፡፡ ከምዕራቡ ዓለም የምንዋሰውንና የምንቀስመውን የምንወስደውን ልናደርገው የሚገባንን ለይተን እስካላወቅን ድረስ እያለማን ቢመስለንም እያጠፋን መሆኑን የምንረዳው የማይካስ የማይመለስ ኪሳራ ከደረሰብን በኋላ በመሆኑ ይህ ከመሆኑ በፊት ዓይናችንን እንግለጥ፡፡ ነጭን ማመን ቀብሮ ነውና፡፡ ይህንን ስል ግን ጭፍን የሆነ የባዕዳን ጥላቻ (xenophoba) ይኑራቹህ እያልኩ እንዳልሆነ ግን ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ንቁ ጥንቃቄ አይለያቹህ ጠርጥሩ ለማለት እንጅ፡፡
በሉ እንግዲህ አሁን ጨርሻለሁ ከዚያ በፊት ግን ይሄንን የግርዛት ጉዳይ ሳጠና የገጠሙኝንና እክል ፈጥረውብን ከነበሩትን ጉዳዮች ልጥቀስላቹህ፡-
  1. “መንግሥት” አቋም የያዘበት ጉዳይ ነው መባሉና የጥናቱ ውጤት “የመንግሥትን” አቋም የሚፃረር ቢሆን እንደምን ባለ መንገድ ለውጤት ማብቃት ይቻላል? የሚለው ተስፋ አስቆራጭ ስሜት፡፡
  2. ጉዳዩ ነውር ተብሎ በነውር አጥር የተከለለ በመሆኑና ክብረ-ነክ ከመሆኑ የተነሣ ከግለሰቦች ጋር በቀጥታ ሊያቀያይም ስለሚችል በቤተሰብ አካባቢ ይሄንን ጥናት እንዳጠና አለ መፈለጉ፡፡
  3. ጥናቱን ያደረኩት በጀት የመደበልኝ ተቋም ሳይኖር በግል ተነሳሽነት እንደመሆኑ መጠን ጥናቱን በብቃትና በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የወጪ (finance) ውስንነትና እጥረት ማጋጠሙ፡፡
  4. ከርእሰ ጉዳዩ ክብደት የተነሣ ጥናቱን የተሟላ ለማድረግ ስለሴቶች የመራቢያ አካል (ብልት) ክፍሎችና አገልግሎታቸው በአካል ዓይቸም መረዳት የምችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ ማግኘት አለመቻሉ፡፡
  5. ይሄንን በቁጥር 4 ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ስልም የሚበቃኝን መረጃ  እስካገኝ ድረስ የተለያዩ ዓይነቶችን በርካታ የወሲብ ፊልሞችንና ቪዲዮዎችን (ምትርኢቶችንና ትዕይንተ-ኩነቶችን) ለማየት መገደዴ የምፈልገውን መረጃ ካገኘሁ በኋላም ከጭንቅላት ፍቆ ሰርዞ ሊያጠፉት ለማይችሉት የሕሊናን ንጽሕና ለሚያረክስና ለሚያጎድፍ ጸያፍ ጉድፈት መዳረጌ፡፡ እንደሰውም በማየው ነገር መፈተኔ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በሉ እንግዲህ አስቂኝም አሳዛኝም አስገራሚም አስደንጋጭም ሁኔታዎችን እያስተናገድኩ ያጠናሁትን ጥናት ለእናንተ አቅርቤ ጨርሻለሁ፡፡ ስላገኘኋቹህ ደስ ብሎኛል ስለተነፈስኩትም ቀሎኛል ሥጋቴን ትጋሩታላቹህ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሞያዊ ችሎታው ወይም ትምህርቱና ዕድሉ ያላቹህ ወንድም እኅቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በጠለቀና በሰፋ እውነታን በተመረኮዘ በተለይ በተለይ ደግሞ ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አኳያ ትርፍና ኪሳራን ባወራረደ ባመዛዘነና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ጥናትና ምርምር ታደርጉ ዘንድ አደራየ ጥብቅ ነው፡፡ አጥፍቸ ተሳስቸ እንደሆነም ፈጥኘ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ በተብራራና ግልጽ በሆነ መልኩ በዚህ በዚህ ምክንያት ትክክል አይደለም የሚለኝ ካገኘሁ፤ እንደኔ እነደኔ ግን ሁሉም ሰው ሊገባው ሊረዳው በሚችል አገላለጽ ምንም ነገር ሳልደብቅ ሳልሸፋፍን ሳላስቀር ብትንትን አድርጌ እንዳቀረብኩት አምናለሁ፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
በመሆኑም ጽሑፉን ለመረዳት ከላመቻል አንጻር የተቋውሞ ጥያቄና አስተያየት ቢቀርብልኝ እጅግ እጅግ ሳልገረም ሳልደነቅ ሳላዝን እንደማልቀር ከወዲሁ ልነግራቹህ እወዳለሁ፡፡ “መንግሥት” በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የወሰደውን የሕገወጥነት ውሳኔና አቋም በተቻለ ፍጥነት መልሶ እንዲያጤነው ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ ነገር ግን “መንግሥት” የሴት ልጅ ግርዛትን መከላከል በሚል እንቅስቃሴ ከምዕራባዊያን ጋር በመስማማት ጉዳዩን እርዳታ ለማግኘት እንደጥሩ የገቢ ማስገኛ ምንጭ አድርጎ እንደቆጠረው ከባድ ሥጋት አለኝ፡፡ ሥጋቴ እውነት ከሆነ እጅግ የጅልነት ተግባር እየፈጸመ እንደሆነ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ “መንግሥት” ልክ አንድ ቤቱን በብዙ ገንዘብና ድካም የገነባን ሰው ያንን እጅግ ብዙ የሆነ ገንዘብ የፈጀህበትን ቤትህን ይህችን ጥቂት ብር እንካና አፍርስልኝ ተብሎ በመስማማት ያችን የተቀበላትን ገንዘብ ውድ ቤቱን ለማፍረስ እንደሚጠቀምበት ጅል ሰው መስሎ ይታየኛል፡፡ አሁን ይሄን ሰው በምን ሒሳብ በምን ስሌት ነው አተረፈ ተጠቀመ ልንለው የምንችለው?
“የሴት ልጅ ግርዛት የጎጅ ልማድ ጉዳይ ሳይሆን የብሔራዊ ደኅንነታችንና የህልውናችን ቁልፍ ጉዳይ ነው!!”
አመሰግናለሁ!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

No comments:

Post a Comment