Search

Tuesday, April 14, 2015

የቅናት መዘዝ – አርአያ ተስፋማሪያም

jealousy is evilከአርአያ ተስፋማሪያም
ሞገስና ሊያ አሜሪካ የመጡት ከ25 ዓመት በፊት ሲሆን በጊዜው ሁለቱም ወጣት ፍቅረኛሞች ነበሩ። ሊያ “ቆንጆ” የሚለው ቃል አይገልፃትም። ሞገስ “የቀማኛ አገር ነው” በሚል ፍቅረኛው ስራ እንድትሰራ አይፈልግም፤ ከቤት እንድትወጣ አይፈቅድም። ሊያ ስለምትወደው ለሶስት አመት ቃሉን በማክበር ከቤት ሳትወጣ አሳለፈች። በቅላቷ ላይ የባሰ ነጭ ሆነች። «እባክህ እስከመቼ እቤት ውስጥ ተቆልፌ ልኑር?..እየሰራሁ ላግዝህ። ለማንም ልቤ አይፈታም!» ስትል ትማፀነዋለች። ከዚያም በአንድ ትልቅ ሬስቶራንት በካሸርነት ስራ ትጀምራለች። የተመለከታት ሁሉ በውበቷ እየተማረከ የፍቅርና ጋብቻ ጥያቄ ያቀርብላት ነበር። እሷ ግን የምትታመንለት ፍቅረኛ እንዳላት ትነግራቸው ነበር። አንድ ጊዜ መኪና ተበላሽቶባት መኖሪያዋ ድረስ አንድ ሃበሻ ያደርሳታል። ፍቅረኛዋ ሞገስ ያያል። በድጋሚ በምትሰራበት ቦታ ያ ሃበሻ ባንኮኒ ተደግፎ ሲያወራት ይመለከታል። ጥርጣሬው እየጨመረ ይሄዳል። ሽጉጥ ይገዛል። ሊያ መኪናዋን እያሽከረከረች በመኖሪያቸው ፓርኪንግ ደርሳ ትቆማለች። ሞገስ ሽጉጡን መዞ ሲጠጋት «እባክህ አትግደለኝ?..እወድሃለሁ! » ቃታውን ስቦ ጭንቅላቷን በጥይት ቦዳደሰውና ለፖሊስ እጁን ሰጠ። ሊያ ወደ መቃብር ስትሸኝ፣ ሞገስም 20 አመት ተፈርዶበት ዘብጥያ ወረደ። ከ17 አመት እስር በኋላ በቅርቡ ነው የተፈታው። ለአሳዝኝ የመንፈስና አካላዊ ጉዳት ተዳርጓል። በወንድሙ በኩል አግኝቼው ሲያወራኝ « እባክህ ለምን ትገድለኛለህ?..የምታፈቅረኝ ከሆነ አንዴ ጥፋቴን ንገረኝና ግደለኝ!..ሃጢያቴን ሳላውቀው አትግደለኝ” ..እያለችኝ – እየተማፀነችኝ ገደልኳት። ለ17 አመት ማለትም ለ6ሺህ 200 ቀናት በፀፀት አልነጋ ስጠበስ ኖርኩ። አሁንም ቀሪውን እድሜዬን ስቀጣ እኖራለሁ። ውበቷ ለቅናት አጋልጦ የህሊና መዘዝ አተረፈብኝ። ሌት ተቀን እያነባሁ ፈጣሪዬን ማረኝ ብለውም አልሰማ አለኝ! የውስጤን ጉዳት እንባዬ ታጥቦ ሊያወጣልኝ አይችልም! ለአመታት እንባዬ በየቀኑ በመፍሰሱ አሁን ደርቋል።..» አንገቱን አቀርቅሮ ዝም አለ።
source:mereja.com

No comments:

Post a Comment