ግለሰቡ የፕሮፋይል ምስሉ የአሜሪካ መንትያ ህንጻዎች ሲጋዩ የሚያሰይ ፎቶ ግራፍ ካደረገም ረዘም ያሉ ግዜያት ተቆጥረው ነበር፡፡
ወንድሞቻችን በሜድትራንያን ባህር አካባቢ በአይ ኤስ አይ ኤሶች ግድያ ከተፈጸመባቸው በኋላም በታጣቂዎቹ እየተጎተቱ ሲወሰዱ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፉበት ‹‹በኦሮምኛ ከአገራችን ውጡ››የሚል ጽሁፍ አስፍሮበታል፡፡
ታላቁን ህዝብ ኦሮሞን እወክላለሁ እያለ በሌሎች ላይ ሞትን የሚሰብከው ግለሰቡ በጣም በቅርቡ የፈረንሳይና የመካከለኛው… ምስራቅ ወታደሮች የሚጫሙትን ቡትስ ጫማ መጫማቱን የሚያሳይ ፎቶም ለጥፎ ነበር፡፡ወንድሞቻችንን በሊቢያ ያረዱ አረመኔዎችም ይህንኑ ጫማ ተጫምተው እንደነበር መመልከት ይቻላል፡፡
በሪያድ ሳዑዲ እንደሚኖር በገጹ የሚናገረው ግለሰብ ምናልባት አይ ኤስ አይ ኤስን የተቀላቀለ ሊሆን እንደሚችል በደንብ እንድንጠረጥር የሚያደርገን ሶስት ወጣቶች መሳሪያ በመያዝና ወታደራዊ ልብስ በመልበስ ፊታቸውን በጭምብል በመሸፈን የቪዲዮ ምስል መልቀቃቸው አይዘነጋም፡፡ይህንን የቪዲዩ ምስል መጀመሪያ የለቀቀው ግለሰብም እርሱ መሆኑን ብዝዎች የሚያስታውሱ ይመስለኛል፡፡
በቪዲዩው የሚታዩት ኢትዩጵያዊያን ወጣቶች የለበሱትን አይነት ወታደራዊ ልብስ በሊቢያ ወንድሞቻችንን ሲቀጥፉ የተመለከትናቸው ሽብርተኞችም መልበሳቸው መቼም የግጥምጥሞሽ ብቻ አይሆንም፡፡
ሌላኛው አስገራሚ ነገር በአሁኑ ሰዓት Ahamab muhamad oromo የፌስ ቡክ አካውንቱን ዲአክትቬት ማድረጉ ነው፡፡መረጃው እርሱን የማይመለከት ከሆነ ስለምን አካውንቱን ሳይዘጋ ምላሽ መስጠት አልተቻለውም?
እንግዲህ የተቃዋሚዎችን አካውንት እየሰበራችሁና ስልኮቻችሁን እየጠለፋችሁ አልያም ከሰላማዊ ትግል እየገፋችሁ ወደ ጫካው እየመራችሁ መልሳችሁ ደግሞ ‹‹ሽብርተኛ››በማለት ከጎረቤት አገር ሳይቀር የምታስመጡ እናንተ ከወዴት አላችሁ?
posted by Aseged Tamene
No comments:
Post a Comment