ከብዙ ዘመናት በፊት ጫማ የሚባለው የእግር ልባስ ከመሰራቱ በፊት ሰዎች እግራቸውን ባዶ ነበር የሚሄዱት።
በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በገጠራማ አካባቢ ያሉ ሰዎች ያለ ጫማ በባዶ እግር ሲጓዙ ይስተዋላል።
ታዲያ በባዶ እግር መጓዝ ለጤናቸን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተመራማሪዎች ያስታወቁ ሲሆን፥ ከነዚህም ውስጥ እግራችን የተስተካከለ እና ጤናማ የመንካት ስሜት እንዲሁም ከተፈጥሮ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል።
በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ያክል በባዶ እግር በመሄድ ወይም በመንቀሳቀስም ሰውነታችንን ተገቢውን ሀይል እንዲያገኝ እንደሚረዳንም ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
በተጨማሪም በባዶ እግር መንቀሳቀስ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እንደሚያደርግም ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል።
በባዶ እግራችን በምንራመድበት ጊዜም የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን የሚያደርግ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ከደም ዝውውሩ ጋር ሰውነታቸን በቂ ሀይል በማግኘት የሰውነታችን ክፍሎች እንዲነቃቁ ያደርጋል።
በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ያከል በባዶ እግራችን መጓዝ ለልብ ህመህ እንዳንጋለጥ የሚረዳን መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ በተጨማሪም የምግብ መፈጨትን ለማስተካከል፣ የጭንቀት ስሜትን ለማሰወገድ እና የሰውነታችንን አቅም ማጣት ለመከላከል ይረዳናል።
በባዶ እግር ለመሄድ ጊዜ የማናገኝ ከሆነ ወይም የማንቸል ከሆነ ደግሞ እግራችንን እና እጃችንን ጠዋት እና ማታ በደንብ መታሸት /ማሳጅ/ መደረግ ይመከራል።
በዚህ መንገድ በመጠቀምም እግራችንን ባዶ በመሄድ የምናገኘውን የጤና ጠቀሜታዎች ማግኘት ይቻላል።
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በሙለታ መንገሻ
Tran : FBC
No comments:
Post a Comment