Search

Friday, April 3, 2015

ከሞት የተመለሰው ህፃን

የ32 አመቷ ካትሪን
የ32 አመቷ እንግሊዛዊቷ ካትሪን ነፍሰጡር በመሆኗ ወደ ሳልፎድ ሮያል ሆስፒታል ታመራለች። በመሆኑም የጤና ምርመራ ሲደረግላት በማህፀኗ ያለው ፅንስ መሞቱ ይነገራታል። እናም ፅንሱን ማስወረድ ይኖርብሻል ያሉት ሀኪሞች ለዚሁ ይረዳት ዘንድ የሚዋጥ መድሀኒት ይሰጧትና ወደቤቷ ትመለሳለች።
ይሁንና ካትሪን የደም መፍሰስ ችግር ለሁለት ቀናት ያጋትማታል፤ ጤንነቷም ይታወካል። ስለሁኔታው ባለሙያ ለማማከር ወደ ሆስፒታሉ ታቀናለች። ይሄኔ ነው ያልተጠበቀ ነገር የተከሰተው። በማህፀን ያለው ፅንስ መላወስ ላይ እንዳለ እና እየወሰደች ባለው መድሀኒት ምክንያት ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ሀኪሞቹ ያረጋገጡት።
በሁኔታው ግራ የተጋቡት የጤና ባለሙያውችቹ ሁኔታውን ለመቀልበስ ያለ የሌለ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ከሆስፒታሉ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ሆስፒታሉ ስለተፈጠረው የህክምና ስህተት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ሁኔታው እንዴት ሊከሰት እንደቻለ እናጣራለን ብሏል።
 ሳልፎድ ሮያል ሆስፒታል
ሳልፎድ ሮያል ሆስፒታል
ካትሪን እና ባሏ አንድሪን ስለሁኔታው ሲገልፁ ሁለተኛ ልጃችንን ለመውለድ አስበን ተገቢውን የጤና ክትትል ማድረግ ችለን ሳለ ሆስፒታሉ ይህን መሰል ስህተት እንዴት ሊፈፅምብን እንደቻለ ያስረዳን ሲሉ ገልፀዋል።
ሁኔታውን የበለጠ አሳዛኝ ያደረገው የካትሪን የደም መፍሰስ በማህፀን ያለው ፅንስ መንትያ ሊሆን ይችል የነበረን ያከሸፈ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ሀኪሞች በምርመራ ውጤታችው ማስፈራቸውና አሁንም በህይወት እንዲገኝ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገለት ያለው ፅንስ ዘላቂ የጤና ችግር ያልደረሰበት ስለመሆኑ በሙሉ እምነት መናገር አለመቻላቸው ነው።
ምንጭ፥ ዴይሊ ሜይል

No comments:

Post a Comment