በዛሬው ዋዛ እና ቁምነገራችን ዜና ዋዛን ጨምሮ ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዓል በዓል የሚሸቱ የስልክ ልውውጦ ከወዳጆች ጋር አድርገናል። የበዓል ሙዚቃዎችንም ተገባብዘናል። ስልካችሁን አስቀምጣችሁልን ያልደወልንላችሁ ወዳጆች ወይ ቴሌ አስቸግሮን ነው፣ ወይ ካርዳችን አልቃ ነው፣ ወይ ደግሞ ሰዓታችን አጥራ ነው። ደውለንላችሁ አውርተን ተነጋግረን በዝግጅቱ ያልተካተታችሁ ወዳጆቻችን ወይ ድምጹ አልሰማ ብሎ ነው ወይ ደግሞ ኔትዎርኩ ተቆራርጦ ነው። እና ይቅርታ እየጠየቅን፤ ለተሳታፊዎች በሙሉ ግን የከበረ ምስጋና እናቀርባለን!
በዜና ዋዛ ያቀረብናትን ዜና ቅንጫቢ እንደሚከተለው አስቀምጠን ቀሪውን ዝግጅት በማስፈንጠሪያው ተፈናጥራችሁ እንድትመለከቱት ጋብዘናል፡፡
ዜና ዋዛ.... (ቅንጫቢ)
በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኢህአዴግ ደጋፊ የቤት እንስሳት የኢህአዴግን ምረጡ የምርጫ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆኑ ተሰማ። ከነዚህ ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆኑት በማህበር የተደራጁ ፍየሎች ሲሆኑ ለሌሎች የቤት እንስሳት አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ የኢህአዴግ ጽፈት ቤትን ጠቅሶ ዘጋቢያችን ዘግቧል።
ፍየሎቹ ባለፉት ጨካኝ ስርዓቶች ማንነታቸው ተዋርዶ እና አንገታቸው ታርዶ ለፋሲካ ለአረፋ እና ለኢሬቻ እየተባሉ.... ሲታረዱ እና ሲበሉ መክረማቸውን ተናገረው አሁን ግን ጸሀዩ መንግስታቸን ባመቻቸልን ምቹ የኑሮ ሁኔታ ማንም ደፍሮ ሊገዛንም ሆነ ጨክኖ ሊያርደን ስለማይቻለው ያለ ስጋት መኖር ችለናል ሲሉ ተናገረዋል።
ፍየሎⶩ ቀጣይነት ላለው የተመቻቸ የፍየሎች ኑሮ ኢህአዴግን መምረጥ ተገቢ መሆኑን አስመርውበታል። ይሄንን የምርጫ ቅስቀሳ በጎች በሬዎች እና ዶሮዎችም እንዲቀላቀሉት የጠየቁት ፍየሎቹ ኢህአዴግ ከገባችልን ወዲህ እንደዋዛ እየተያዙ መታረድ ቀርቷል። በግም ሆነች በሬ እንኳን ሌላው ቀርቶ ዶሮ ራሷ ሳትቀር ያለ ስጋት አደባባይ መታየት ጀምራለች ሲሉ አክለውበታል።
ፍየሎቹ አያይዘውም፤ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አራጁን እና አሳራጁን ስርዓት መልሰው ሊያመጡብን እና ሊያስበሉን መሆኑን ተገንዝበን ኢህአዴግን በመምረጥ ሳንታረድ የምንኖርበትን ስርዓት ማስቀጠል የሁሉም የቤት እንስሳ ሃላፊነት ነው ብለዋል።
በድጋሚ መልካም በዓል.... ይመቻችሁ፤ እነሆ ዋዛ እና ቁምነገራችን!
No comments:
Post a Comment