Search

Tuesday, April 7, 2015

ባሳለፍነው ሐሙስ በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ሰቅጣጭ ዜና የሰማንበትን ድርጊት የመራው የቀድሞው የናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ የነበረው የ24 ዓመቱ ሞሀመድ አብድራሂም አብዱላሂ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ባሳለፍነው ሐሙስ በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ሰቅጣጭ ዜና የሰማንበትን ድርጊት የመራው የቀድሞው የናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ የነበረው የ24 ዓመቱ ሞሀመድ አብድራሂም አብዱላሂ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
የሙሀመድ ወላጅ አባት አብዱላሂ ዳቃሪ የመንግስት ከፍተኛ ስልጣን የያዙና በጃምሁሪ አካባቢ የሚገኘውን ማንዴራ የተሰኘ ክልል የሚያስተዳድሩ መሆናቸውም ነገሩን አወዛጋቢ አድርጎታል፡፡
በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የህግ ዲፓርትመንት ቆይታው በጓደኞቹ አባብሞ እየተባለ ይጠራ የነበረው ሞሀመድ ዘናጭ ውድ ሱፎችን የሚያዘወትርና ፑል መጫወት የሚያዝናናው ነበር፡፡
በዩኒቨርስቲው የሚተኛበት ክፍል ቢኖረውም ዶርሙን የተጠቀመው በጣት ለሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ ነበር፡፡ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ጋዝ በኢስትሌይ አካባቢ በመሸጥ ይተዳደር ስለነበርም በዶርም ለማይቆይባቸው ጊዜያቶች ስራውን እንደምክንያት ያቀርብ ነበር፡፡የክፍል ጓደኞቹም ከእነርሱ የተሻለ ገንዘብ የሚያገኘው ከስራው የተነሳ እንደሆነ ያምናሉ፡፡
በዩኒቨርስቲው ከሙሃመድ ጋ ፑል የተጫወተው ዴዳን ዋቼራ ‹‹በአንድ ወቅት ጠይቄው ነበር፡፡ነገር ግን የምሩን ይሁን እየቀለደ ባይገባኝም የሚለብሳቸው ሱፎች ዋጋ 16.000የኬንያ ሽልንግ (160ዶላር)መሆናቸውን ነግሮኝ ነበር፡፡ነገር ግን ሱፎቹ በጣም ውድ ይመስሉ ነበር፡፡በእርግጥ የእኔን ሱፍ አዘጋጅ ለመጀመሪያ ግዜ ያስተዋወቀኝ እርሱ ነው፡፡››
ዋቼራ የቀድሞ ጓደኛውን ሲገልጸው ‹‹ጥሩ ተናጋሪ፣በህግ ክፍል በሚደረጉ ክርክሮች የሚሰማውን ለመናገር የማይፈራ ››ብሎታል፡፡ነገር ግን ከሚለብሰው ሱፍ ስር የሚገኘው ልቡ በጥላቻ የተሞላና በሃይማኖት አክራሪነት የናወዘ መሆኑን ማንም ሳያውቅለት እስከ ሀሙሱ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ድረስ ቆይቷል፡፡
አይ ሲ አይ ሲን የመቀላቀል ህልሙ
ጦማሪና ጋዜጠኛ የሆነው ያሲን ጁማ በግል ድረ ገጹ አብዲራሂም መኖሪያ ቀዬውን ከለቀቀ በእርግጠኝነት አል ሻባብን ወይም አይ ሲ አይ ሲን ለመቀላቀል እንደሚሆን አትቷል፡፡እንደ ጦማሪው ከሆነ የአብዲራሂም የመጀመሪያ ፍላጎት አይ ሲ አይ ሲን መቀላቀል ነበር፡፡ነገር ግን ፓስፖርት ስላልነበረው ወደ ኢራቅ ወይም ሶሪያ ማምራት አልቻለም፡፡
ጦማሪው የአብዲራሂም ከየሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ የክፍል ጓደኛ የነበረው ዋሚ ወደ ቱርክ በማምራት ወደ ሶሪያ በመሻገር አይ ሲ አይ ሲን ተቀላቅሏል፡፡ነገር ግን ልክ እንደ አብዲራሂም ሁሉ ዋሚም በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ በዲግሪ መርሐ ግብር የጀመረውን የህግ ትምህርት ሳያጠናቅቅ ቀርቷል፡፡
ሁለቱ ወጣቶች የከፍተኛ ትምህርት መርሐ ግብራቸውን ሳያጠናቅቁ የቀሩት ሽብርተኛ ለመሆን ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ ሳይሆን እንዳልቀረ አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛቸው ለዴይሊ ኔሽን ተናግሯል፡፡
የማንዴራ ካውንቲ ኮሚሽነር አሌክስ ኮዮ ለኔሽን እንዳስረዱት ከሆነ የአብዲራሂም ወላጅ አባት ልጃቸው በተለየ የስልክ ቁጥር ሲደውልላቸው የት እንደሆነ ሲጠይቁት ስልኩን እንደሚዘጋው ለፖሊስ ሪፖርት አድርገው ነበር፡፡
ከጋሪሳ የተማሪዎች ጥቃት በኋላ ፖሊስ የገደላቸውን አራት የአል ሻባብ ታጣቂዎች ማንነት በቲዊተር አማካኝነት ለእይታ ሲያቀርብ ዋቼራ ከሟቾቹ መካከል የቀድሞው የዩኒቨርስቲ ጓደኛው መኖሩን ለመለየት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ በጋሪሳ የተገደሉትን የአልሻባብ ታጣቂዎች የሚያሳይ ፎቶ ፖሊስ ለአካባቢው ነዋሪ ሲያቀርብ ብዙዎች አብዲራሂምን ለይተውታል፡፡

No comments:

Post a Comment