Search

Thursday, April 2, 2015

ቨርጂኒያን ያስጨነቃት አቶ ወሰኔ አሳየ ተያዘ!

ላለፉት 15ወራት በዲሲና አካባቢው ባንክ ሲዘረፍ ቆይቷል። ‘ባለ ሳይክሉ ሽፍታ’ የሚል ስም የተሰጠው አቶ ወሰኔ አሳየ ሰን ትረስት፣ዋሽንግተን ፈርስት እና ቢቢ እና ቲን ጨምሮ 12 ባንኮችን እንደዘረፈ ታምኖበታል። የቨርጂኒያ ፖሊስ ሲከታተለው የቆየውን ወሰኔ አሰፋ የተያዘው ባለፈው ሳምንት የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ቢሮ የስውር ካሜራዎች ላይ በተገጠሙ የስልክ ዳታ ልውውጥ መከታተያ ቴክኖሎጅን ከመረመረ በኋላ ነበር። በዚሁ ምርመራም በሁሉም ዘረፋዎች ላይ የአቶ ወሰኔ አሰፋ የስልክ መረጃ ባንኩ በተዘረፈበት ሰዓት እና ቀን በካሜራው ተመዝግቧል።በስውር በተቀረፀው ቪዲዮ ብቻ ሲፈለግ የቆየው ወሰኔ አሰፋ በስልክ ቁጥሩ በተደረገበት ክትትል ባለፈው ሳምንት ተይዞ አሌክሳንድሪያ ከተማ ወህኒ ወርዶ ነበር። በእስር ቤት ውስጥ ራሱን ለመጉዳት በመሞከሩ ሌሊቱን ወደ ሆስፒታል ቢመጣም ንጋት ላይ ጠባቂውን ባሃይል መሳሪያ ቀምቶ በማምለጡ ላለፉት ዘጠኝ ሰዓታት በፖሊስ ሲፈለግ ቆይቷል።
ከኢኖቫ ፌርፋክስ ሆስፒታል ያመለጠው ወሰኔ ታርጋ ቁጥሯ XZP-8513 የሆነች ቶዮታ ካምሪ መኪና ሰርቆ ለመሰወር ሞክሯል። ፖሊስ ሊደርስበት ሲልም በእግሩ ሮጦ በማምለጥ ሌላ ሃዩንዳይ መኪና ሰርቆ ፖሊስን እና ነዋሪዎችን ሽብር ፈጥሮባቸው ቆይቷል። በመጨረሻም ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ፔንሲልቫኒያ ጎዳና ላይ ፖሊስ እንደያዘው ተረጋግጧል። ፖሊስ ‘አደገኛ ሰው!’ ያለው አቶ ወሰኔ አሳየ ተመልሶ ወደ ዘብጥያ ወርዷል። ሁለተኛው ላይ የፈፀመው ወንጀል መጀመሪያ ላይ ከታሰረበት እጅግ የከፋ ነው።

No comments:

Post a Comment