Search

Friday, April 17, 2015

ቢሮው በቅርቡ የተላለፉት 35 ሺህ ቤቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተድርጎባቸዋል መባሉ መሰረተ ቢስ መሆኑን ገለፀ

Over 36,000 Condos to be Transfered this Ethiopian Fiscal Year








አዲስ አበባ በቅርቡ የተላለፉት 35 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በተለያዩ መንገዶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተድርጎባቸዋል መባሉ መሰረተ ቢስ ነው አለ የአዲስ አበባ የከተማ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ።
አስተዳደሩ የቤቶቹ ዋጋ ዝቅተኛ እንዲሆን ለማድረግ ከአጠቃላይ ወጪው 43 በመቶውን መደጎሙንም ነው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያሳወቀው።
በመግለጫው ላይ እንደተጠቆመው መንግስት ለተጠቃሚ የሚተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከመሬት ዝግጅት አንስቶ እስኪተላለፉ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ድጎማ ተደርጎባቸዋል።
በቤት ግንባታ ወቅት ከፍተኛ ወጪ የሚሆነው የመሬት ይዞታ እንደመሆኑ ከ50 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን አጠቃላይ የቤት ወጪ መንግስት ለማስቀረት መቻሉም ነው የተገለፀው።
በቤቶቹ ላይ እንደየደረጃቸው ድጎማ የተደረገ ሲሆን፥ ለአብነትም በ10ኛው ዙር ለተላለፉ የስቱዲዮ ቤቶች እስከ 35 በመቶ ፣ እንዲሁም ለባለአንድ  እና ሁለት መኝታ ቤቶችም በቅደም ተከተል የ25 እና 10 በመቶ ድጎማ መደረጉን አመልክቷል ።
በመሆኑም አሁን ላይ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች በአዲስ አበባ በቅርቡ የተላለፉ 35 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ነው የተደረገው የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን እና ቤቶቹ በከፍተኛ የመንግስት ድጎማ ለተጠቃሚ መተላለፋቸው ነው የተጠቀሰው።
በበላይ ተስፋዬ
source :FBC

No comments:

Post a Comment