Search

Friday, April 24, 2015

1 ሺህ 292 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመጪው ሰኔ ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ

1 ሺህ 292 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመጪው ሰኔ ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ
በአዲስ አበባ ከተማ በ40/60 የቤት ፕሮግራም በግንባታ ላይ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ የመስክ ጉብኝት ተካሂዶባቸዋል።
ጉብኝት ከተካሄደባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከልም የሰንጋ ተራ እና ክራውን መንደሮች ይጠቀሳሉ።
በክራውን መንደር እስከ 12 ፎቅ የሚደርስሱ 540 ቤቶች ያሉ ሲሆን፥ ቤቶቹ ሊፍት የተገጠመላቸው፣ የእሳት አደጋ መከላከያ እና የአደጋ ጊዜ መውጫን ያካተቱ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የስልክ መስመሮችም ገብተውላቸዋል።
ለሁሉም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መብራት ቢጠፋ ጀኔሬተር ተዘጋጅቶላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከ14 ሺህ 300 በላይ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 292 ያህሉ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተጠናቀዋል።
ሰኔ 2007 ዓ.ም ላይም ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
በ2006 ዓ.ም ግንባታቸው የተጀመሩት ከ12 ሺህ በላይ ቤቶችም የግንባታ አፈፃማቸውምከ20 እስከ 45 በመቶ ደርሷል ።
በዚህ ዓመትም የ15 ሺህ አዳዲስ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል።
በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም በመጀመሪያ 165 ሺህ ያሀል ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበው የነበር ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት 158 ሺህ ያህል የሚጠበቅባቸውን በመቆጠብ ላይ ይገኛሉ፣ 7 ሺህ ተመዝጋቢዎችም ቁጠባውን አቋርጠው ወጥተዋል።
የቤቶቹን ዋጋ 40 በመቶ የቆጠቡ 20 ሺህ 673 ተመዝጋቢዎች ሲኖሩ፥ እስከ መጋቢት 30፣ 2007 መቶ በመቶ የቤቶቹን ዋጋ የቆጠቡም 8 ሺህ 329 ተመዝጋቢዎች መኖራቸውም ተጠቅሷል።
ሴቶች እና የመንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ እስካሁን በመርሃግብሩ የተላለፈ ውሳኔ የለም፣ ውሳኔው ተግባራዊ ቢደረግ እንኳን ሙሉ በሙሉ ከቆጠቡት ነው የሚጀመረው ነው የተባለው።
የቤት ማስተላለፍን በተመለከተም መቶ በመቶ የቤቶቹን ሂሳብ የቆጠቡ ቅድሚያ ቤቶቹን የሚያገኙ ሲሆን፥ በምዝገባ ወቅት ከተጠቀሰው የቤቶች ዋጋ መጠነኛ ሊኖር እንደሚችልም ተመልክቷል።
የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በስምንት የጋራ መኖሪያ መንደሮች የግንባታው ሂደት በመፋጠን ላይ ይገኛል።
የቤቶች ግንባታ የደረሰበት ደረጃና በቀጣይም ግንባታዎቹ የሚጀመርባቸው አካባቢዎች የመስክ ጉብኝት ላይ ሁሉም የመንግስት እና የግል ሚዲያ ተቋማት ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል።
ቡልቡላ፣ ቦሌ አያተ ሰሚት፣ ገርጂ እና ቱሪስት ንግድም አዳዲስ የ40/60 ቤቶች የሚገነቡባቸው አካባቢዎች ይሆናሉ።
በባሃሩ ይድነቃቸው

No comments:

Post a Comment