Search

Wednesday, August 7, 2013

ፍርድ ቤቱ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴልን ጨምሮ ለሙስና ተጠርጣሪ ንብረቶች ጠባቂ በመሰየሙ ላይ ብይን ሰጠ

ፍርድ ቤቱ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴልን ጨምሮ ለሙስና ተጠርጣሪ ንብረቶች ጠባቂ በመሰየሙ ላይ ብይን ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ 30 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ሁለተኛ የወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች የኩባንያዎቻቸውን ንብረት ጠባቂ ለመሰየም በቀረበለት አቤቱታ ላይ ብይን ሰጠ።

ንብረታቸውን እንዲጠብቅ ወይም እንዲያስተዳድር ገለልተኛ ወገን ይሰየምላቸው የተባሉ ኩባንያዎች ንብረትነቱ የአቶ ስማቸው ከበደ የሆነው የኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል እና ዲ ኤች ሲሜክስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም የአቶ ከተማ ከበደ ንብረት የሆነው ኬኬ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፣ የአቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ንብረት የሆኑት ነፃ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ባሳፋ ትሬዲንግ ናቸው።
የፌደራሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቢ ህግና የተጠርጣሪ ጠበቆች በጋራ ተሰማምተው የሚያቀርቧቸው አስተዳዳሪዎችን ፍርድ ቤቱ ለመቀበል ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ፥ ሁለቱም ወገኖች ተስማምተው አስተዳዳሪ ባለማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ዛሬ በሰጠው ብይን ተስማምተው እስከሚያቀርቡ እስከ መስከረም 22 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ንብረቱ በነበረበት ሁኔታ ይቆይ በማለት አዟል።

የተጠርጣሪ ተወካዮች እስከ መስከረም 22 ቀን 2006 ዓ.ም ንብረቶች ይባክናሉ ሰራተኞችም ደሞዝ አልተከፈላቸውም የሚሉ ምክንያቶችን አቅርበዋል ለችሎቱ ።

ፍርድ ቤቱ ሁለቱ ወገኖች ተስማምተው ሃሳባቸውን በማመልከቻ ፍርድ ቤቱ በሚፈቅደው አሰራር መሰረት ካመለከቱ ፥ ብይኑ ተሰብሮ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብሏል።

No comments:

Post a Comment