ትናንት ከቁንዝላ ወደ ደልጊ 102 ሰዎችን
አሳፋሮ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በመግለበጡ እስካሁን አምስት ሰዎች መሞታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ደልጊ መዳረሻ ስፍራ በግምት 150 ሜትር ርቀት ላይ ፥ ተሳፋሪዎችን ለማውረድ ሲቃረብ ጀልባው የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበትም ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት።
የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ለባልደረባችን ኤልያስ ተክለወልድ እንደነገሩት ፥ የአደጋው
መንስኤ እስካሁን በእርግጠኝነት ባይታወቅም ፤ ተሳፋሪዎቹ ለመውረድ
እየተዘጋጁ ሰለነበር በአንድ ስፍራ መከማቸታቸው የሚዛን መዛባት አስክትሎ ለአደጋው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ፋሲለደስ በመባል የምትጠራውን ጀልባ ሲያሽከረክር የነበረው ካፒቴን በህይወት የተረፈ ሲሆን ፥ ለፖሊስ በሰጠው ቃልም ይህኑኑ አረጋግጧል
ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት ምናልባትም በህይወት የተረፈ ካለ እና ተጨማሪ አስከሬኖችን የማፈላለጉ ስራ ተጠናክሮ
ቀጥሏል።
ይህ አይነቱ አስከፊ አደጋ ሲያጋጥም የመጀመሪያው ነው ያሉት ኮማንደር ዘመነ ፥ በቀጣይ ትክክለኛውን
መረጃ በማጣራት ምክንያቱን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
No comments:
Post a Comment