Search

Tuesday, May 28, 2013

ኢትዮጵያ 290 ሚሊዮን ብር ያወጣችበትን ግዙፍ የስፖርት ማዕከል አስገንብታ ዛሬ አስመርቃለች::

የኢትዮጵያ ሁለገብ የወጣቶች  ስፖርት አካዳሚ ዛሬ  በይፋ ተመረቀ።
አካዳሚውን በይፋ የመረቁት ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት ፥ የሀገራችን ስፖርት ቀደም ሲል በአብዛኛው በግል ጥረትና ተነሳሽነት እንዲሁም በልምድ በመታገዝ ውጤት እንዲመዘገብ ረድቷል ።
ይሁንና ስፖርቱ ከሚጠይቀው ጥልቅና ሳይንሳዊ መሰረት ካለው አሰለጣጠን አንጻር የማሰልጠኛ ማእከሉ መከፈት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት።
አቶ ሀይለማርያም በንግግራቸው  የስፖርት ልማት የሰው ሀብት ልማታችን ዋናው አካል ሲሆን ፥ የአገሪቱ የስፖርት እድገትን የሚለካውም በአለም አቀፍ የስፖርት መድረክ በሚመዘገብ ውጤት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ህብረተሰቡ ስፖርትን ለአካልና ለአእምሮ ጤንነት ማረጋገጫነት በስፋት ሲጠቀምበት ነው ብለዋል።
ከስድስት ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው ይህ አካዳሚው ከ290 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።
አካዳሚው በውስጡ ስታዲየም ፣ ጂምናዚየም ፣ የመማሪና የመኝታ ክፍሎች ፣አለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ የመዋኛ ገንዳ  ያሟላ ሲሆን ፥ ለአገሪቱ የስፖርት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል ።
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም አካዳሚውን ጎብኝተዋል ።

No comments:

Post a Comment