Search

Saturday, May 11, 2013

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 12 ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ ግንቦት 03/2005 የፌዴራል የሥነ ምግባር ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚገኙባቸውን በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ ኮሚሽኑ ከሕዝብ የተቀበላቸውን ጥቆማዎች መሠረት በማድረግ ከብሄራዊ ደህንነነትና የመረጃ አገልግሎት ጋር በመተባበር በጥናት ተሰማርቶ ከቆየ በኋላ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ 12 ባለሥልጣናትን ነው። በተጠርጣሪዎች ላይ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በመሰባሰቡ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሠረት ትናንት ግንቦት 2/2005 ከፍርድ ቤት ህጋዊ የብርበራና የእስር ትዕዛዝ በማውጣት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታ እንዲሁም የኢትዮጵያ የባሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ የሚገኙባቸው 12 ያህል ተጠርጣሪዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሥር ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዓዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን መነሻ በማድረግ ተጨማሪ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ ሕጋዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹን ከነሙሉ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቹ ለመደበኛው ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment