በደቡባዊ ቻይና ጉዋንግሺ ከተማ በቤተሰቦቹ የተጣለው ጨቅላ ህፃን ከስምንት ቀናት በኋላ በህይዎት መገኘቱ እያነጋገረ ነው።
የከተማዋ ፖሊስም ከህፃኑ መጣል ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሶስት ቤተሰቦቹን ጨምሮ አምስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ክስ መስርቶባቸዋል።
ጨቅላ ህፃኑ አፍንጫው የተሰነጠቀ ሆኖ በመወለዱ ነው ቤተሰቦቹ ከከተማዋ ራቅ ወዳለ ጫካ ወስደው በተወለደ በሶስተኛው ቀን የጣሉት።
ከስምንት ቀናት በኋላም አንዲት የባህል መድሃኒት (እፅ) ፈላጊ የህፃኑን ድምፅ በመስማቷ ህፃኑን ከተጣለበት ልታየው በመቻሏና ለፖሊስ በመጠቆሟ ህፃኑን በህይዎት ማግኘት ተችሏል።
ፖሊስም ህጻኑ በብርድ ልብስ ተጠቅልና በካርቶን ተደርጎ እንደተጣለ ደርሶ ወደ ሆስፒታል የወሰደው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።
ለህፃኑ ህክምና እያደረጉለት የሚገኙት ዶክተሮችም ህፃኑ ለስምንት ቀናት ያህል የመቆየቱ ነገር ተአምር ነው ብለውታል።
ጨቅላው ህፃን ለዚህ ያህል ቀናት በህይዎት መቆየትም የዝናብ ውሃ ማግኘቱ አስተዋጽኦ አድርጎለታል ነው ያሉት።
የተሰነጠቀ አፍንጫን በቀላል ቀዶ ጥገና ማከም እየተቻለ በአጉል አስተሳሰብ ህፃኑን የጣሉት ቤተሰቦችንም ቻይናውያን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች እያወገዟቸው ነው።
የቻይና ጤና ባለስልጣን እንደሚለው ባለፉት 15 አመታት 300 ሺህ የሚደርሱ የአፍንጫ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸውን ህፃናት የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላቸዋል።
ምንጭ፦ ሲሲቲቪ
No comments:
Post a Comment