ዛሬ በኢንግሊዝ በተካሄደው ታላቁ የማንቸስተር ሩጫ ላይ የተሳተፈው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በውድድሩ ማብቂያ ላይ የሩጫ ውድድር ማቆሙን ይፋ አደረገ።
ሀይሌ የዛሬውን ሩጫ ካጠናቀቀ በኋላ ለ25 ዓመታት የቆየበትን የሩጫ ውድድር ማቆሙን ቢገልፅም፥ ሩጫን ግን አላቆምም ነው ያለው።
አትሌት ሀይሌ ከአምስት ዓመት በፊት የሩጫ ውድድርን ሊያቆም እንደሚችል ተናግሮ እንደነበር እናስታውሳለን።
የ42 ዓመቱ አትሌት ሀይሌ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን፥ 25 ጊዜ የዓለም ክብረወሰኖችን በተለያዩ ርቀቶች ሰብሯል።
በአሁኑ ወቀትም የ20 ሺህ ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ባለቤት ነው።
አትሌቱ በአሁኑ ወቅት በአገሩ በተለያዩ የኢንቨሰትመንት ዘርፎች ተሰማርቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment