ባሳለፍነው እሁድ በሊቢያ ውስጥ በአሸባሪው አይ ኤስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢተዮጵያውያን ማንነት በመለየት ላይ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በርካታ የሟች ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ሞት ተረድተው ሀዝን በመቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
ቀደም ብሎ ኢያሱ ይኩኖአምላክ እና ባልቻ በለጠ የተባሉ የጨርቆስ አካባቢ ተወላጆች የአይ ኤስ ሰለባ መሆናቸው ተለይተው ቤተሰቦቻቸው ሀዘን ላይ መሆናቸው ይታወሳል።
አሁን ደግሞ ወጣት ብሩክ እና ሌሎች ሁለት ወጣቶች የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩም የተለያዩ ምንጮች ጠቅሰዋል።
ሌላኛው በአይ ኤስ የተገደለው ወጣት በቀለ አርሴማ ይባላል ተወልዶ ያደገው በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ ካራቻ የሚባል ቦታ ሲሆን፥ በአሁን ሰዓት ቤተሰቦቹ ተረድተው የአካባቢው ነዋሪዋች ልቅሶ እየደረሱ ይገኛሉ።
የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑት እና የመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ዳዊት ሀድጉ እና ወጣት አለም ተስፋዬም የአይ ኤስ አረመኔያዊ ገድያ ሰለባ ሆነዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ እሁድ ገበያ የሚባል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ወጣት መንግስቱ ጋሼም ሌላኛው የአይ ኤስ ሰለባ መሆኑ ተለይቷል።
source : FBC

No comments:
Post a Comment