Search

Saturday, February 16, 2013

ኢትዮጵያ በፊፋ ወርሀዊ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ አራት ደረጃዎች ዝቅ አለች

በፊፋ ወርሀዊ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ አራት ደረጃዎች ዝቅ አለች።
ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎው ያስመዘገብው ውጤት ለደረጃ መውረዱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።
በውድድሩ ላይ ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታወች በሁለቱ ተሸንፎ አንዱን አቻ ከወጣ በኋላ ፥ የየካቲት ወር ደረጃው ቀድሞ ከነበረነት 110ኛ ወደ 114ኛ አሽቆልቁሏል።
በአንድ ወር ልዩነት ከፍተኛ መሻሻል ያሳየችው ሀገር ሞሪታኒያ ስትሆን ፥ ቀድሞ ከነበረችበት 206ኛ ደረጃ በ38 ከፍ ብላ 168ኛ ላይ ተቀምጣለች።
በአፍሪካ ዋንጫው ሳትጠበቅ ለፍፃሜ የደረሰችው ቡርኪናፋሶ 37 ደረጃዎችን ስታሻሽል ፥ የውድደሩ አዘጋጅ ደቡብ አፍሪካ 25 ደረጃዎችን ወደ ላይ ተስፈንጥራለች።
የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ናይጄሪያ ባለፈው ወር ከነበረችበት 52ኛ ደረጃ ወደ 30 መጥታለች።
ሆኖም የአፍሪካን ደረጃ የሚመሩት እንደየቅደም ተከተላቸው ከአለም 12 እና 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ፥ ኮትዲቯርና ጋና ናቸው።
የፊፋን ወርሀዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ስፔን ፣ ጀርመንና አርጀንቲና ከፊት ሲመሩ ፥ እንግሊዝም ሁለት ደረጃዎችን አሻሽላ 4ኛ መሆን ችላለች ፣ ፈረንሳይና ብራዚል አሁንም 17ኛ እና 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በአንተነህ ጌታሁን

No comments:

Post a Comment