Search

Wednesday, May 29, 2013

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሮዳስ ተክሉ እዚህ አትላንታ ከተማ በዋለው የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርባ ጉዳይዋ ሲታይ ከቆየ በኋላ ባለፍው ሰኞ MAY 20/2013 ….. 25 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሮዳስ ተክሉ ይህ የተፈረደባት የሰው ነፍስ በማጥፋቷ ወንጀሉንም መፈጸሟን በማመኗ ነው።
የኋላ ታሪኩ እንዲህ ነው። ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2009 አመሻሽ ላይ በአትላንታ የተፈጸመው ወንጀል መላው የአትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቅርብ፣ ነገሩን የሰሙና በሌሎች ከተሞች ያሉትን ደግሞ በሩቅ ያስደነገጠ ነበር። 3754 ቢፈርድ ሃይዌይ የሚባለው የአትላንታ መንገድ ላይ የጸጉር መከርከሚያ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ላይ የነበረው ኤርሚያስ አወቀ ፣ ማምሻውን ጭምር አምሽቶ እየሰራ ነበር። ከምሽቱ 8 ፒ ኤም አካባቢ ሮዳስ ተክሉ ሱቁ ድረስ መጣች።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሮዳስ ሱቁ ድረስ ከመጣች በኋላ ጭቅጭቅ ተጀመረ። እሱ እንድትወጣለት ቢጠይቃትም አልወጣችም። ይልቁኑ በእጇ ሽጉጥ ይዛ ስለነበር ፣ ስልኩን አንስቶ 911 ደወለ፣ ስልኩን ላነሳችው ኦፕሬተር “አንዲት ሴት ሱቄ ድረስ መጥታ ልትገለኝ እያስፈራራችኝ ነው፣ መሳሪያ ይዛለች .. እያለ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ ስልኩ ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የጥይት ድምጽ መስማታቸውን ይናገራሉ።
ፖሊስ ካለበት፣ ነገሩን የሰሙም በጸጉር ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ኤርሚያስ በደም ተነክሮ ወድቋል፣ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፣ ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አለፈ። በወቅቱ አንዲት ሴት ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ አይተናል ከሚል ጥቆማ ውጪ ማን ገደለው የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆነ።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 6 ግን ፖሊስ ሮዳስ ተክሉ የተባለችና የቀድሞ ፍቅረኛው ነች የተባለች ሴት በጥርጣሬ መያዙን አስታወቀ። እሷም ወደ እስር ቤት ተወሰደች። ኤርሚያስም የፖሊስ ምርመራ ከታወቀና ዶክተሮች የሞቱን መንስኤ ካስታወቁ በኋላ ፌብሩዋሪ 11 ቀን በርካታ የአትላንታ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጸጉር ቤቱ ደጃፍ የሻማ ማብራት ሰነ ስር ዓት ተካሄደ፣ በማግስቱ ፌብሩዋሪ 12 ጸሎተ ፍትሃት ከተደረገለት በኋላ አገር ቤት ተወስዶ እንዲቀበር በተያዘለት ፕሮግራም ይሄዳል ሲባል ፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገኛል በማለቱ እስከ ፌብሩዋሪ 24 ሳይላክ ቆየ። ፌብሩዋሪ 24 ቀን ግን አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ለቀብር ተላከ።
ከዚያ በኋላ ዜናው በአድማስ ሬዲዮም ሆነ አትላንታ ባለው ድንቅ መጽሔት ከወጣ በኋላ በወቅቱ የወጣት ሮዳስ ተክሉ ቤተሰቦች “እሷ በግድያው የለችበትም፣ ይህንን ድርጊት እሷ ትፈጽማለች ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሆነም ቀረ ላለፉት አራት ዓመታት ነገሩ ከፍርድ ቤት እስር ቤት ፣ ከ እስር ቤት ፍርድ ቤት ሲንከባለል ቆየ፣ የ ኤርሚያስ አወቀ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ላቀው ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጹት በመካከል ተጠርጣሪዋ ልጅ፣ በጠበቆቿ አማካኝነት “አእምሮዋ ትክክል አይደለምና ለፍርድ ልትቀርብ አይገባም” ብለው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ዳኞቹም የ አ ዕምሮዋ ነገር በሃኪሞች እንዲታይ ፈቅደው ቆይተዋል። በኋላ ግን ችሎት መቆም እንደምትችል በመታመኑ ፣ ጉዳዩ በከሳሽ አቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ሮዳስ ተክሉ ጠበቆች መካከል ክርክሩ ቀጥሎ አራት ዓመት ከፈጀ። እንደ አቶ ላቀው ገለጻ ፣ በመጨረሻ ላይ ሮዳስ ወንጀሉን መፈጸሟን እንድታምን ተጠይቃ “አዎ ፈጽሜያለሁ፣ ነገር ግን በደም ፍላትና ሳላስበው ያደረኩት ነው” ስትል በማመኗ ዳኛዋ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርደውባታል። ምናልባት ጥፋቷን ባታምን እና ነገሩ በክርክሩ ብትሸነፍ የሞት ፍርድ ሊጠብቃት ይችልም ነበር ብለዋል።
ዳኛዋ በፍርድ ውሳኔያቸው እንደገለጹት “ ኤርሚያስ ገበየሁን በ 10 ጥይት መግደል ሳይታሰብ፣ ባጋጣሚ የተደረገ አይደለም” ሲሉ ውሳኔያቸውን አጽንተዋል።
በተያያዘ ሁኔታ ሮዳስ ተክሉ እዚያው እስር ቤት እያለች አንዲት ሴት ልጅ መውለዷም ታውቋል። የወለደችው ግሬዲ ሆስፒታል በፖሊስ ታጅባ ሄዳ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ህጻኗን አንዲት ነርስ እዚያው ግሬዲ እያሳደገቻት መሆኑ ሲታወቅ፣ የህጻኗን አባት በተመለከተ ዳኛዋ “የቀረበልኝ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ስለሌለ፣ በልጅቷ አባት ጉዳይ የምሰጠው አስተያየት የለም” ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። (ምንጭ አድማስ ሬዲዮ አትላንታ)

Racist Videos - The Funny Networks _ The Funny Networks


Tuesday, May 28, 2013

ኢትዮጵያ 290 ሚሊዮን ብር ያወጣችበትን ግዙፍ የስፖርት ማዕከል አስገንብታ ዛሬ አስመርቃለች::

የኢትዮጵያ ሁለገብ የወጣቶች  ስፖርት አካዳሚ ዛሬ  በይፋ ተመረቀ።
አካዳሚውን በይፋ የመረቁት ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት ፥ የሀገራችን ስፖርት ቀደም ሲል በአብዛኛው በግል ጥረትና ተነሳሽነት እንዲሁም በልምድ በመታገዝ ውጤት እንዲመዘገብ ረድቷል ።
ይሁንና ስፖርቱ ከሚጠይቀው ጥልቅና ሳይንሳዊ መሰረት ካለው አሰለጣጠን አንጻር የማሰልጠኛ ማእከሉ መከፈት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት።
አቶ ሀይለማርያም በንግግራቸው  የስፖርት ልማት የሰው ሀብት ልማታችን ዋናው አካል ሲሆን ፥ የአገሪቱ የስፖርት እድገትን የሚለካውም በአለም አቀፍ የስፖርት መድረክ በሚመዘገብ ውጤት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ህብረተሰቡ ስፖርትን ለአካልና ለአእምሮ ጤንነት ማረጋገጫነት በስፋት ሲጠቀምበት ነው ብለዋል።
ከስድስት ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው ይህ አካዳሚው ከ290 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።
አካዳሚው በውስጡ ስታዲየም ፣ ጂምናዚየም ፣ የመማሪና የመኝታ ክፍሎች ፣አለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ የመዋኛ ገንዳ  ያሟላ ሲሆን ፥ ለአገሪቱ የስፖርት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል ።
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም አካዳሚውን ጎብኝተዋል ።

ከረሃብ ለመዳን ጥንዚዛና ምስጥ፣ አንበጣና ጉንዳን ብሉ UN: Eat more insects to fight hunger

ተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ዩኤን) ባለፈው ሳምንት ከሮም ከተማ ለአለማችን ረሃብተኞች አንድ ምክርና የምስራች ወሬ አሰራጭቷል። የምስራች ወሬው፣ “እነ ጥንዚዛን በመመገብ ከረሃብ መገላገል ይቻላል” የሚል ነው። በደግነት የለገሰን ምክር ደግሞ፣ ከረሃብ ለመዳን “ነፍሳትን ብሉ” ይላል። ዩኤን ይህን “ምክርና የምስራች” በይፋ ለመላው አለም ያበሰረው፣ የአለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ባዘጋጀው ባለ 200 ገፅ ሰነድ አማካኝነት ነው። የሰነዱ ርዕስ እንዲህ ይላል፣ Edible insects፡ Future prospects for food and feed security። እነ ጉንዳን፣ የመጪው ዘመን የምግብ ዋስት ተስፋዎቻችን እንደሆኑ የሚሰብክ ሰነድ ነው። “ረሃብተኛ ሆኖ ለብዙ አመታት በተመፅዋችነት መቆየት፣ መጨረሻው ውርደት ሆነ? ‘ጥንዚዛ ብላ!’ የሚል የስላቅ ምላሽ የምንሰማበት ደረጃ ላይ ደረስን?” የሚል ጥያቄ የሚፈጠርባቸው የድሃ አገር ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። በእርግጥም፣ በርካታ አለማቀፍ የሚዲያ ተቋማት፣ ዜናውን የዘገቡት በስላቅ መንፈስ ነው።
“ዩኤን ለአለማችን ረሃብተኞች አንድ ምክር አለው - በራሪ ነፍሳትን መብላት…” በማለት ነው ያሁ-ኒውስ ዘገባውን የሚጀምረው። የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባም ተመሳሳይ ነው። “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ረሃብን፣ የአለም ሙቀትንና ብክለትን ለመዋጋት አዳዲስ መሳሪያዎችን ታጥቋል” በማለት የሚጀምረው የአሶሼትድ ፕሬስ ዜና፣ የዩኤን መሳሪያዎችን ለማየት ከፈለግን ሩቅ መሄድ እንደማይኖርብን ይገልፃል። አካበቢያችንን ብንቃኝ በቂ ነው። የዩኤን “ዘመናዊ” መሳሪያዎች፣ በሄድንበት ቦታ ሁሉ በዙሪያችን የሚያንዣብቡና አፍንጫችን ስር ሳይቀር “በረራ” የሚያዘወትሩ ናቸው። ይህንን የስላቅ አገላለፅ በማስቀደም አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባውን ሲቀጥል… በዩኤን እምነት፣ የአለም ረሃብተኞች የወደፊት ተስፋ በራሪ ነፍሳትን መመገብ እንደሆነ ይገልጻል።
በዩኤን ስር፣ ለረሃብተኞች የእርዳታ እህል በማጓጓዝ የሚታወቀው ፋኦ፣ በራሪ ነፍሳት ለመብል የሚስማሙ መሆናቸውን ሲያስረዳ “በራሪ ነፍሳት በፕሮቲን የበለፀጉ ናቸው” ብሏል። እናም፣ ዩኤን እና ፋኦ፣ ረሃብን ለመከላከል ተስፋቸውን የጣሉት በበራሪ ነፍሳት ላይ ነው። ግን የነፍሳት ጥቅም፣ ከምግብነትም የላቀ እንደሆነ የገለፁት ዩኤንና ፋኦ፣ ለአካባቢ ጥበቃ ግሩም መፍትሄ ይሆንልናል ብለዋል። በሬና ላም፣ በግና ፍየል ብዙ ሳር እየበሉ አካባቢን ያራቁታሉ፤ የተለያዩ የጋዝ አይነቶችን እያመነጩ አካባቢን ይበክላሉ ይላል ዩኤን። ስለዚህ፣ አካባቢን የማያራቁቱና የማይበክሉ በራሪ ነፍሳት፣ ቀለባችሁ ይሁኑ በማለት ምክሩን ለግሷል። 1900 ያህል የነፍሳት ዝርያዎች ለምግብነት ተስማሚ መሆናቸውን ዩኤን ጠቅሶ፣ ጉንዳን፣ ጥንዚዛ፣ አንበጣ፣ ዝንብ፣ ምስጥ፣ አባጨጓሬ እንዲሁም ሌሎች በራሪና ተስፈንጣሪ ነፍሳትን በምሳሌነት ዘርዝሯል። የዩኤን እና የፋኦ መግለጫ፣ በረሃብተኞች ላይ የተሰነዘረ ስላቅ ይመስላል ብለው የሚቆጡ መኖራቸው አይቀርም።

ነገር ግን ብዙም አይገርምም። እድሜ ልክ እርዳታ እየጠበቀ የሚኖር ረሃብተኛ፣ ውሎ አድሮ “ከራበህ ጥንዚዛ ብላ!” የሚል ምላሽ ማግኘቱ የማይቀር ነው። ውርደት ሊመስል ይችላል። ከሁሉም የከፋ ውርደት ግን፣ ራስን ለመቻል አለመጣርና አለመቻል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፣ “ጥንዚዛና ዝንብ ተመገቡ” የሚለው ዘመቻ፣ በየጊዜው የሚያገረሽ የዩኤን እብደት ይመስላል። እናም፣ ለጊዜው ከተወራለት በኋላ፣ ወረቱ ሲያልቅ ተረስቶ ይቀራል ብለን እንገምት ይሆናል። ግን በዋዛ አይረሳም። ባለፉት 10 አመታት ለዘመቻው በጀት ሲመደብለት ቆይቷል። አሁንም ይመደብለታል። ለምን ቢባል… ዩኤንና ፋኦ ምላሽ አላቸው -ነፍሳትን የመመገብ ልምድ እንዲስፋፋና የህዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ (awareness raising) በጀት ይመድባሉ።
ሰነዶችን ለማዘጋጀትና ለማሰራጨት፣ በአባል አገራት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማካሄድ፣ አዳዲስ ህጎችንም ለማዘጋጀት ገንዘብ ያወጣሉ። አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት፣ በራሪ ነፍሳትን የማርባት ሥራ እንዲጀምሩም ይደጉማሉ። ዩኤንና ፋኦ፣ ይሄን ሁሉ የሚያደርጉት፣ “ረሃብተኞችን ለመደገፍ” ነው። በሌላ አነጋገር፣ ዩኤንና ፋኦ፣ ብዙ ገንዘብና ሃብት ሳያባክኑበት በፊት፣ “የበራሪ ነፍሳት ፕሮጀክታቸውን” በአጭር ጊዜ እንደዘበት ይረሱታል ተብሎ አይጠበቅም።

Monday, May 27, 2013

“ሰዎች እንብላ የሚሉት ከልባቸው ነው ወይስ እንደው ለነገሩ ያህል?” የዳሰሳ ጥናት ውጤት

ሰሞኑን ማህበረሰባዊ እሴቶቻችን ከሚባሉት በአንዱ ላይ የብድግ ብድግ ናሙና ወስጄ ጥናት እካሄድኩ ነበር፡፡ የጥናቱ ትኩረት የ “እንብላ ባህላችን” ሲሆን ጥናቱን ለማካሄድ ያስፈለገበት ምክንያትም እውነት ይህ ባህል አለ ወይስ ብዙዎች እንደሚሉት “ጎጂ ባህል” ከሚባሉት ተርታ ተሰልፏል የሚለውን እና አለ ከተባለም ሰዎች እንብላ የሚሉት ለአፋቸው ያህል ነው ወይስ ከልብ የሚለውን የምርምር ጥያቄ ለመመለስ ነበር፡፡
የጥናቱ ዘዴ ደግሞ ሰዎች ምግብ በሚመገቡባቸው አካባቢዎች ላይ ማንዣበብና ማፍጠጥ ወይንም ኦብዘርቬሽን ማካሄድ ነበር፡፡ ለጥናቱ  በናሙናነት ከተወሰዱ ተመጋቢዎች መሀል ታዲያ 70 በመቶ ያህሉ “አንብላ” አላሉም፡፡ ስለዚህ አብዛኞቹ “አንብላ ጎጂ ባህል ነው”  ከሚሉት ተርታ ይመደባሉ ማለት ነው የሚል መላ ምት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡
ቀሪዎቹ 30 በመቶ ደግሞ ለአፋቸው ያህል እንብላ ቢሉም የዚህ ጥናት ባለቤት ግብዣቸውን ተቀብሎ ለተጨማሪ ምርምር ባደረገው ጥረት ያገኘው ውጤት አስደንጋጭ ነው፡፡ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት “አንብላ ባዮች” ከምግብ ሳህናቸው ላይ አንድ ሁለት ጠብደል ጠብደል ጉርሻዎች ብድግ ብድግ ሲደረጉ ከፊታቸው ላይ የነበረው ፈገግታ ሁላ በአንድ ጊዜ ድራሹ ይጠፋና በምልክቱ አይናቸው ማጉረጥረጥ ጀምሯል፡፡ አንዳንዶቹ እንዳውም “ ቀልድ አታውቅም እንዴ” የሚለውን ጥያቄ ከማንሳት ጀምሮ “ ፍሬንድ አንተም እዘዛ” በማለት የሰው በልቶ አያድሩም ተኝቶ አይነት አቋም ሲያራምዱ ተስተውሏል፡፡ እጃቸውን እንደመታጠብ ብለው በመጥፋትም የምግቡን ዋጋ አጥኚው ከፍሎ እንዲወጣ ያደረጉም አልታጡም፡፡
ይህ ጥናት ለናሙናነት የተጠቀመባቸው ሰዎች ቁጥር አናሳና አካባቢያዊ ስብጥሩም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የሀገሪቱን ገፅታ ወካይ ነው ማለት አያስደፍርም፡፡ ይሁንና ለሌሎች የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች ጥናት መነሻ ሊሆን እንደሚችል አጥኚው ይተማመናል፡፡
ጥያቄው አሁንም ክፍት ነው፤   “ሰዎች እንብላ የሚሉት ከልባቸው ነው ወይስ እንደው ለነገሩ ያህል?”

በተጠረጠሩባቸው የሙስና ወንጀሎች የታሰሩት አቶ መላኩ ፈንታ መታመማቸው ተገለጸ

46 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዘው 100 ሺሕ ብር የተሸለሙት ተጠርጣሪ ልታሰር አይገባም አሉ

‹‹እኔ በመታሰሬ መንግሥትም ፕሮጀክቶችም ይበደላሉ›› አርክቴክት በእግዚአብሔር አለበል

‹‹ለልጄ ወተት መግዣ ብቻ አንድ ሺሕ ብር ይሰጥልኝ››  የበምጫ ትራንዚት ባለቤት 
በተጠረጠሩባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት በሚኒስትርነት ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ መታመማቸውን ጠበቃቸው ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው አስታወቁ፡፡

ጠበቃው አቶ መላኩ በአስቸኳይ ሕክምና እንዲደረግላቸው ጠይቀው፣ “እኚህ ሰው በጠና ስለታመሙ የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን፤” ብለዋል፡፡

የአቶ መላኩን ጤንነት በሚመለከት ጠበቃው በዝርዝር ጠይቀው የሕመማቸው ዓይነትና ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባይረዱም፣ መልካቸው ቢጫ ሆኖ እንዳዩዋቸው ገልጸዋል፡፡ ለምን እንዳላነጋገሩዋቸው ሲጠየቁ በቂ ጊዜ እንዳልነበራቸው የገለጹት ጠበቃው ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን፣ ነገር ግን ሆስፒታል ይሂዱ ወይም አይሂዱ አለማወቃቸውንም አስረድተዋል፡፡

በአጃቢ ሆነው ሕክምና እንዲያገኙ ጠበቃው ላነሱት ጥያቄ፣ ስለመታመማቸው የሚገልጽ ማስረጃ ከክሊኒክ ወይም ከሆስፒታል እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ያለማስረጃ ትዕዛዝ መስጠት እንደማይቻል ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

አቶ መላኩ መንግሥት የሚያውቀውና በአገር ውስጥ ሕክምና የማይድን ሕመም እንዳለባቸውና በውጭ አገር እየታከሙ እንደነበር፣ ለፍርድ ቤቱ ራሳቸውና ጠበቃቸው ማስረዳታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ቀጥሮት የነበረውን የእነ አምባውሰገድ አብርሃ የምርመራ መዝገብን ተመልክቷል፡፡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የናዝሬትና ሚሌ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ 11 ተጠርጣሪዎች ቀረጥ በማጭበርበር፣ ክስ በማቋረጥ፣ የኮንትሮባንድ ዕቃ ሳይፈተሽ እንዲያልፍ በማድረግና ተገቢ ያልሆነ ሀብት በማከማቸት የሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎትና ለተጠርጣሪዎቹ አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችለውን የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን መሰብሰቡንና ቃል መቀበል መጀመሩን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ ቀሪ ሰነድ ማሰባሰብ፣ የምስክሮችን ቃል መቀበልና የተሰበሰቡ ሰነዶችን የመለየት ሥራ እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

አቶ አምባውሰገድ የልብ ሕመምተኛ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፣ መርማሪ ቡድኑ በብርበራ የሚፈልገውን ማስረጃ በመውሰዱና እሳቸውም ሊያጠፉት የሚችሉት ማስረጃ ስለሌለ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ አቶ ቃለአብ ዘርአብሩክም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ የናዝሬት ጉምሩክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዴሳ ሚደቅሳ ሥራ ከማስተባበር ውጭ ጣልቃ ገብተው የተጠረጠሩበትን ወንጀል እንዳልፈጸሙና ከተያዙ ሰባት ቀናት እንዳለፋቸው በማሳወቅ፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜን ተቃውመው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡

በሕገወጥ መንገድ በሕገወጦች ተይዞ የነበረን 46 ኪሎ ግራም ወርቅ በመያዝ ከመንግሥት ምስጋናና 100 ሺሕ ብር ሽልማት ማግኘታቸውን የገለጹት የባለሥልጣኑ ባልደረባ አቶ እሸቱ ግረፍ ናቸው፡፡ በተመሰገኑበት ሥራ ሌላ ነገር ሊሠሩ እንደማይችሉ፣ መርማሪዎችም አሉ የተባሉ ሰነዶችን በብርበራ የወሰዱ በመሆናቸውና የሚቀር ነገር የሌለ በመሆኑ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ጌታሁን ቱጂ፣ አቶ መላኩ ግርማ፣ አቶ አስፋው ሥዩም፣ አቶ ጌታነህ ግደይና አቶ ዮሴፍ አዳዊ የተባሉ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች የተጠረጠሩበት ጉዳይ መርማሪ ቡድኑ ካለው ጋር የማይገናኝና የሥራ ድርሻቸውም የማይገናኝ መሆኑን በማስረዳት፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

አርክቴክት በእግዚአብሔር አለበል መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው የመጠርጠሪያ ድርጊት ከእሳቸው ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ የመንግሥትና የግል የሆኑ ከ60 በላይ ፕሮጀክቶች እንዳሏቸው በማስረዳት፣ ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ ችግር እያጋጠማቸው በመሆኑ ዋስትና እንዲከበርላቸው ደጋግመው ጠይቀዋል፡፡

የባህር ዳርና የጎንደር ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶችን እንደሚያማክሩ የተናገሩት አቶ በእግዚአብሔር፣ ከ131 በላይ ደረጃ አንድ ተቋራጮችን ከማማከራቸውም በተጨማሪ፣ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው እሳቸው የሥራውን ጥራት ማረጋገጥ ስላለባቸው ሥራ እየቆመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ መንግሥትም ሆነ ሠራተኞች እንደሚበደሉ የገለጹት አርክቴክቱ፣ ሰነዶችን በሚመለከት ሁሉም ሰነዶች በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ በመሆናቸው ሊሰውሩና ሊያጠፉ የሚችሉበት አጋጣሚ ስለሌለ፣ እሳቸውን አስሮ ማቆየቱ ምንም ጥቅም እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

ሥራ ከሚበላሽና ሠራተኛ ከሚበተን ፍርድ ቤቱ ውክልና ለሌላ ሰው የሚሰጡበትን መንገድ እንዲያመቻችላቸው የጠየቁት አቶ በእግዚአብሔር፣ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰነዶች እንደተያዙባቸው በመግለጽ እንዲለቀቁላቸው ጠይቀዋል፡፡ ክፍያ የሚፈጽሙት በየዕለቱ ቢሆንም ማህተምና ቼክ ስለተወሰደባቸው የሠራተኞች ደመወዝ፣ የገቢ ግብርና የጡረታ ክፍያ መክፈል አለመቻላቸውንም አስረድተዋል፡፡ አገር እያለሙ መሆኑን በመናገር በዋስ ሆነው ሥራቸውን እየሠሩ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የጠየቁት አቶ በእግዚአብሔር፣ በመርማሪዎች እንደተነገራቸው ‹‹ሰው ታውቃለህ›› በሚል ብቻ መታሰራቸውን አስረድተዋል፡፡

የችሎቱን ታዳሚዎች ያሳዘነና ከንፈር ከማስመጠጥ አልፎ እንባ እስከ ማፍሰስ ያደረሳቸው የበምጫ ትራንዚት ባለቤት አቶ ዘለቀ ልየው ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡ አቶ ዘለቀ የጉምሩክ አስተላላፊ ትራንዚተር መሆናቸውን በጠበቃቸው በኩል ገልጸው፣ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ስድስት ቀናት ቢሆናቸውም እስከ ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ቃላቸውን አለመስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19 (4) መሠረት አንድ በቁጥጥር ሥር የዋለ ዜጋ ቃሉን እንዴት መስጠት እንዳለበት የተቀመጠው ድንጋጌም መጣሱን አመልክተዋል፡፡

ቢሯቸው መታሸጉንና በቢሯቸው ውስጥ ያለው ሰነድ ሳይለይ የሚያስፈልገውም ሆነ የማያስፈልገው ሰነድ አንድ ላይ በመታሸጉ፣ በእሳቸውም ላይ ሆነ በመንግሥት ላይ ጉዳት እንደሚያመጣ ተናግረዋል፡፡ ኤልሲ የተከፈተባቸው፣ ሥራ የተጀመረላቸውና ያልተጀመረላቸው ነጋዴዎች ብሔራዊ ባንክ ሄደው እንዳይጠይቁ መቸገራቸውን፣ ወደ አገር ውስጥ ያልገቡ ዕቃዎች ሰነዶች በሙሉ ስለተቆለፈባቸው ለወደብ የሚከፈለው በዶላር መሆኑንና ተጎጂው አገር ጭምር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የታሸገባቸው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥ መሆኑን በመጠቆም እንዲከፈትላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠበቃቸው ጠይቀዋል፡፡

ሕፃን ልጃቸው እሳቸው ሲያዙ ተመልክቶ እስካሁን በመሳቀቅ ላይ በመሆኑ እንዲያገኛቸው እንዲታዘዝላቸውም አመልክተዋል፡፡ ተጠርጣሪው እንዲናገሩ ጠይቀው ሲፈቀድላቸው እምባ እየተናነቃቸው፣ ‹‹እቤቴ አንድም ብር እንኳን ሳይተው መርማሪዎቹ ሁሉንም ገንዘብ ወስደውታል፡፡ የምጠይቀው ለልጄ ወተት መግዣ ብቻ አንድ ሺሕ ብር እንዲሰጡልኝ ነው፤›› ካሉ በኋላ መናገር አልቻሉም፡፡ የችሎቱ ታዳሚዎችም በተጠርጣሪው ንግግር የተወሰኑት ሲያለቅሱ የተወሰኑት ተክዘው ተስተውሏል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከተናገሩ በኋላ ምላሽ እንዲሰጥ በፍርድ ቤቱ የታዘዘው መርማሪ ቡድኑ፣ አንዳንድ ጥያቄዎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች በመሆናቸው በቢሮ በኩል እንደሚፈቱ ተናግሯል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄን በሚመለከት ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን በመጥቀስ ቢለቀቁ ሰነድ፣ ምስክርና ሌሎች ማስረጃዎችን ሊያጠፉበት እንደሚችሉ በመግለጽ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግና የ14 ቀናት ጊዜ ምርመራ እንደፈቀድለት በድጋሚ ጠይቋል፡፡

ሌላው ፍርድ ቤቱ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ለመርማሪ ቡድኑ ያነሳው ጥያቄ፣ ተጠርጣሪዎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር ያዘዘውን ትዕዛዝ ኮሚሽኑ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ቢታዘዝም፣ ለምን ሳይፈጽም እንደቀረ እንዲያብራራ ነበር፡፡ ኮሚሽኑ የተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት መከበር አለመከበር የመከታተል ግዴታ እንዳለበትም ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው ተጠርጣሪዎች በስድስት መዝገብ ተከፋፍለው የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ሥራው ውስብስብ በመሆኑና ለብርበራ ተጠርጣሪው ጭምር የሚወጣበት ጊዜ በመኖሩ፣ ከሕግ አማካሪ ጋር የሚገናኙበትን ጊዜ ረቡዕና ዓርብ መደረጉን፣ የጊዜ ቀጠሮ ያላቸውንም በመለየት ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር እያገናኘ መሆኑን ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መርማሪ ቡድኑ እንዳብራራው ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን ፍርድ ቤቱ መገንዘቡን ገልጾ፣ የተመርማሪዎች ዋስትና ጥያቄን ውድቅ ማድረጉን በማስረዳት ለመርማሪ ቡድኑ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ ለግንቦት 26 ቀን 2005 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ማለትም በቤተሰብ፣ በሕግ አማካሪና በሐኪም የመጎብኘትና የማግኘት መብታቸውን በሚመለከት የማዕከላዊ እስረኛ ኃላፊ ኮማንደር ብርሃኑ አበበ ቀርበው እንዲያስረዱ በታዘዘው መሠረት ኮማንደሩ ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. አስረድተዋል፡፡

ኮማንደር ብርሃኑ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ሁሉም የሕግ አማካሪዎች ደንበኞቻቸውን አግኝተዋል፡፡ በችሎት የተገኙም የሕግ አማካሪዎች ከአቶ ከተማ ከበደ ጠበቃ በስተቀር ሁሉም መገኘታቸውን መስክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎችና የሕግ አማካሪዎች የተገናኙበት ቀን ሪፖርት እንዲደረግና አቶ ከተማ ከበደን በሚመለከትም ጥብቅ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ለግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ሪፖርት እንዲያደርጉ በድጋሚ አዟል፡፡     


Ethiopian Reporter
 

Wednesday, May 22, 2013

ለ 40 ቀን 40 ለሊት እንጾማለን ብለው ሚስትን ለሞት ዳረጉ ልጆቹም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

ያለምንም እህል እና ውሃ ጾምን ለ 40 ቀን 40 ለሊት እንጾማለን ብለው ጾማቸውን የጀመሩት የቤተሰብ አባላት ለከፍተኛ ጉዳት እና ለሞት መዳረጋቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
በጎተራ ኮንደሚኒየም ውስጥ ይኖሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች በሃገራችን እምነት አንጻር ጾም ጸሎትን እያደረግን አምላክን በጸሎት እናስባለን በማለት ጾማቸውን መጀመራቸው ተገልጾአል ።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ያለው ባል እና ከጂማ ዩኒቨርሲቲ በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀች ሲሆን ።

ባል በባህርዳር በክሊኒክ ይሰራ የነበር ሲሆን ሚስትም በዚሁ የሙያ ስራ ተሰማርታ ወደ  ባህርዳር ማቅናቷ እና የልጆቿን አባት በፍቅር ግንኙነት ጀምራ ወደ ትዳር አለም አብራው እንደዘለቀች እና ሁለት ልጆችን አፍርተው የ9 አመት እና የስድስት አመት ልጆችንም ማፍራታቸው  የሪፖርተራችን ያጠናቅራል ።

ከምግብ እና ከውሃ ተለይተው ለልጆቻቸው ብቻ በጣም ጥቂት ምግብን በመያዝ በቤታቸው ዘግተው ለቀናቶች ሰንብተዋል ።

ሂደቱ ለ25 ቀናት የተጓዘ ሲሆን ባለቤቷ እያበሰለ ለልጆቹ ከሚያቀርበው ምግብ ለራሱ በጥቂቱ የሚቀምስ ሲሆን ለባለቤቱ ሲሰጣት ግን ምንም አይነት ነገር መመገብ አለመቻሏን እና ምንም አያገባህም በማለት ምላሽ ታክል እንደነበር ዘገባው ያመለክታ.

ሆኖም ግን 40ኛ ቀኑ ከመድረሱ አራት ቀን በፊት የእናት የአፍጠረን መለወጥ ያየችው ህጻን ከወላጅ እናቷ ተለይታ  ከታናሽ እህቷ ጋር በሶፋ ላይ መተኛት መጀመሯን እና ከዚያም በመስኮት እራበን ድረሱልን እያለች መጮኋን እና የጎረቤት ልጅ መጥታ በበር ቀዳዳ በተሰጣት ቁልፍ ከፍታ በመግባት ፣ሁለቱ ህጻናቶች ቆዳቸው ተጣብቆ በምግብ ጉዳት ምክንያት ከስተው የተገኙ ሲሆን ባል እራሳቸውን በመሳት በሆስፒታል በህክምና ክትትል ላይ ናቸው ሚስትዬዋ ግን በህይወት ሊተርፉ አለመቻላቸውን ዘገባው አክሎ ጠቁሞአል.