Search

Tuesday, May 21, 2013

በጣና ሃይቅ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይዎት አለፈ

ትናንት ከቁንዝላ ወደ ደልጊ 102 ሰዎችን አሳፋሮ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በመግለበጡ እስካሁን አምስት ሰዎች መሞታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ደልጊ መዳረሻ ስፍራ በግምት 150 ሜትር ርቀት ላይ  ፥ ተሳፋሪዎችን ለማውረድ ሲቃረብ  ጀልባው የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበትም ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት።
የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ለባልደረባችን ኤልያስ ተክለወልድ እንደነገሩት ፥ የአደጋው መንስኤ እስካሁን በእርግጠኝነት ባይታወቅም  ፤ ተሳፋሪዎቹ ለመውረድ እየተዘጋጁ ሰለነበር በአንድ ስፍራ መከማቸታቸው የሚዛን መዛባት አስክትሎ ለአደጋው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ፋሲለደስ በመባል የምትጠራውን ጀልባ ሲያሽከረክር  የነበረው ካፒቴን በህይወት የተረፈ ሲሆን ፥ ለፖሊስ በሰጠው ቃልም ይህኑኑ አረጋግጧል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት ምናልባትም በህይወት የተረፈ ካለ እና ተጨማሪ አስከሬኖችን የማፈላለጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ይህ አይነቱ አስከፊ አደጋ ሲያጋጥም የመጀመሪያው ነው ያሉት ኮማንደር ዘመነ ፥ በቀጣይ ትክክለኛውን መረጃ በማጣራት ምክንያቱን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።
 (ኤፍ ቢ ሲ)

Monday, May 20, 2013

ቅዳሜ ኢትዮጵያ ከ ሱዳን ጋር ለምታደርገው ጨዋታ የተጫዋቾች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ
ግንቦት 12 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ አፍሪካ ህብረት የተመሰረተበትን 50 ኛ አመት  ክብረ በአል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ከሱዳን በምታደርገው ጨዋታ ላይ የሚካፈሉ ተጫዋቾችን ስም ዝርዝር የኢትዮጵያ  ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ይፋ አደረጉ ፡፡
በዚህም መሰረት የተመረጡት ተጫዋቾች ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጉ ደበበ ፣አበባው ቡጣቆ፣ቢያድግልኝ ኤልያስ፣አሉላ ግርማ፣ሽመልስ በቀለ ፣አዳነ ግርማ ፣ያሬድ ዝናቡ፣ዮናታን ብርሀነና ተስፋዬ አለባቸው ናቸው ፡፡
ከ ደደቢት ሲሳይ ባንጫ ፣ ስዩም ተስፋዬ ፣ብርሃኑ ቦጋለ፣አይናለም ሃይሉ፣አክሊሉ አየነው ፣አዲስ ህንጻ፣በሃይሉ አሰፋ ፣ጌታነህ ከበደ ፣ምን ያህል ተሾመ ፣ዘነበ ከበደ(አዩካ) ና ዳዊት ፍቃዱ ሲሆኑ ፥
ከ ኢትዮጵያ ቡና ጀማል ጣሰው፣አስቻለው ግርማ ፣ፖክ ጅምስ እና ኤፍሬም አሻሞ፥
ከ መብራት ሃይል አስራት መገርሳ እና መስፍን ወንድሙ፥
ከ መከላከያ ጥላሁን ወልዴ ፥
ከ ኢትዮጵያ መድህን ሳለሃዲን ባርጌቾ፥
ከ ሀዋሳ ከነማ ወንድሜነህ ዘሪሁን፥
ከ ሰበታ ከነማ ደረጀ አለሙ እና ከ ሲዳማ ቡና ደግሞ ሞገስ ታደሰ  ሆነዋል ፡፡
ተጫዋቾቹ ከነገው ግንቦት 13 ማለዳ ጀምሮ በ ፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉም  አሰልጣኙ ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል፡፡

የግሉን ዘርፍ በሙስና ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ አዋጅ ሊወጣ ነው

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 10 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የግሉን  ዘርፍ  በሙስና ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ አዋጅ  ለመደንገግ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከህብረተሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ መክሯል።
አዋጁ ህዝባዊ ድርጅቶች ናቸው ተብለው በሚታሰቡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች  በግል ኩባንያዎች  እና በአክሲዮን ማህበራት ውስጥ የሚፈፀሙ የሙስና የወንጀል ድርጊቶችን  ተጠያቂ የሚያደርግ አንቀፅ ተካቶበታል ።
ይህም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይንም የአክሲዮን ማህበርን ወይንም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በሚያደራጅ ሰው ወይም ኮሚቴ በድርጅቱ ውስጥ በማስፈፀም ሂደት የህዝብ ሃብት እንዳይባክን ለመከላከልም የሚያስችል  ነው ተብሏል። 
በእነዚህ የህዝብ ድርጅቶች ውስጥ የተቀጠሩ ቋሚና ጊዜያዊ ተራ ሰራተኞችም ቢሆኑ በሙስና ወንጀል ውስጥ ከተገኙ ህጉ ተፈፃሚ ይሆንባቸዋል ።
በሚስጢር ሊጠበቁ የሚገቡ የካዝና የመጋዘን ወይም ውድ እቃ የሚቀመጥባቸው የመሳሰሉ ሳጥኖችን ቁልፎች ሆን ብሎ ወይንም በቸልተኝነት ለሌላ ሰው  አሳልፎ በመስጠት ድርጅቶች እንዲመዘበሩ ያደረጉ ሰራተኞችን ለመቅጣትም  በአዋጁ ጠንካራ ድንጋጌዎች እንዲካተቱበት ተደርጓል።
የአዋጁ መውጣትም በእነዚህ የህዝብ ድርጅቶች ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በማስተካከል ህጋዊ መስመርን ተከትለው እንዲተዳደሩ ያግዛልም ተብሎ ታስቧል።
በ ታደሰ ብዙዓለም ።
       

ሶሪያውያን እናቶች በሴት ልጆቻቸው ላይ ጨክነዋል

በሶሪያ መላ የታጣለትን የእርስበርስ ጦርነት በመሸሽ ወደ ዮርዳኖስ የተሰደዱ እናቶች፣ ህይወት ፈተና ሆኖባቸው ሴት ልጆቻቸውን “ለጊዜያዊ ትዳር” እየሸጡ ነው፡፡ ስደተኛ ወላጆች በሴት ልጆቻቸው ላይ መጨከን እንደጀመሩ የዘገበው ሲኤስ፣ ኑሮን ለመግፋት የሚያስችላቸው ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ያገኙት ሴት ልጆቻቸውን በሺዎች በሚቆጠሩ ዶላሮች ለጋብቻ መሸጥ ነው፡፡ ከዮርዳኖስም ሆነ በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጋብቻ ፈላጊ ወንዶች ለሴቷ ቤተሰቦች ገንዘብ የሚሰጡበት ባህል አለ፡፡ ይሄም ሆኖ ግን የሰሞኑ የዮርዳኖስ ስደተኛ ካምፖች “የጋብቻ ገበያ”፣ እርግጥም ወንዶች ሴቶችን ለዘላቂ ትዳር የሚገዙበት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ “ትዳሮች” ከሳምንታት የዘለቀ ዕድሜ እንደማይኖራቸው የገለፀው ዘገባው፤ ይልቁንም “የወሲብ ገበያ” ሊባል የሚችል መሆኑን አስረድቷል፡፡
ይህንን የሴት ልጆች ሽያጭ ከሚያቀላጥፉትና ራሳቸውን “የጋብቻ ደላላ” ብለው ከሚጠሩት መካከል ሶሪያዊቷ ስደተኛ ኡም ማጄጅ አንዷ ናት፡፡ ኡም ማጄድ ከሰሞኑ እየጦፈ በመጣው የስደተኛ ልጃገረዶች ሽያጭ ገበያ ፋታ አጥታለች፡፡ የሞባይል ስልኳ በገዢዎች ጥሪ ተጨናንቋል፡፡ ኡም ማጄድ ከወላጆች ጋር በመነጋገር ለሽያጭ ከምታቀርባቸው ሴቶች ጠቀም ያለ ኮሚሽን ታገኛለች፡፡ ክብረ ንጽህናዋ ያልተገረሰሰ ልጃገረድ በሰሞኑ ገበያ እስከ 5ሺህ ዶላር ታወጣለች፡፡ አያ የተባለችዋ የ17 አመቷ ሶሪያዊት ስደተኛ አያ፤ ከቤተሰቦቿ ጋር በስደት ወደ ዮርዳኖስ ከመጣች አንድ አመት ያህል ሆኗታል፡፡
ይሄም ሆኖ ግን የስደት ኑሮ ለእሷም ሆነ ለቤተሰቧ አሳር ሲሆንባቸው፣ ብቸኛውን አማራጭ ለመውሰድ ተገደዱ፡፡ አያ ለ70 አመት ሳኡዲ አረቢያዊ “ትዳር ፈላጊ” ሽማግሌ በ3ሺህ 500 ዶላር ተሸጠች፡፡ ትዳር ፈላጊው ሽማግሌ ግን ከሙሽሪት አያ ጋር የመሰረተውን ትዳር ለማፍረስ የፈጀበት የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ “ከእሱ ጋር ያሳለፍኩት አንድ አመት ልክ እንደ አስፈሪ ቅዠት ነበር፡፡ ግማሹን ወር በመራር ለቅሶ ነው ያሳለፍኩት፡፡ ከቤተሰቦቼ ጋር እንድገናኝና እንዳወራ አይፈቅድልኝም ነበር፡፡ ምርጫ አልነበረኝምና በሰቀቀን ነበር የምኖረው” ብላለች - አያ ስለ ሽያጩ ትዳሯ ስትናገር፡፡
እንዲህ ለጋ ልጃገረዶችን ለገበያ አቅርባ የምታሻሽጠው ኡም ማጄድ እየሰራችው ስላለችው ነገር ሃፍረትም ሆነ ፀፀት አይሰማትም፡፡ “መኖር የምችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ “ስራ” ነው፡፡ ሶሪያውያን ስደተኞች በዮርዳኖስ ሌላ ስራ መስራትና ገቢ ማግኘት አንችልም፡፡ ስለዚህ ምን ማድረግ እንችላለን?...እንስረቅ?...እንግደል?” ትላለች ማጄድ፡፡ የሚገርመው ግን “አንቺስ የ13 አመት ልጃገረድ ልጅሽን ለመሸጥ ትፈቅጃለሽ?” ለሚለው የጋዜጠኞች ጥያቄ የሰጠችው መልስ ነው፡፡ “በፍፁም አላደርገውም!... ልጆቼን ከምሸጥ አይኖቼን አውጥቼ ብሸጣቸው እመርጣለሁ!” ነው ያለችው ማጄድ፡፡

Friday, May 17, 2013

ከሽሮ ችርቻሮ ወደ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ባለንብረትነት ተሸጋገሩ

ከ200 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተሠራው ሆቴላቸው ቅዳሜ ይመረቃል
በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ አንዲት ወይዘሮ ከሽሮ ችርቻሮ ሸያጭ ተነስተው በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የፊታችን ቅዳሜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሆቴሉ ቃል አቀባይ በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ወይዘሮ አማረች ዘለቀ የተባሉ የአምስት ወንዶች ልጆች እናት ያሠሩት ይኼው ሆቴል፣ የተለያዩ ደረጃዎች ያሉዋቸው 70 የመኝታ ክፍሎች ሲኖሩት በደቡብ ክልል በዓይነቱ የመጀመርያው ነው ተብሏል፡፡


ሆቴሉ ባለ አሥር ፎቅ መንታ ሕንፃዎች ሲኖሩት፣ ከ250 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ከቃል አቀባዩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ወይዘሮ አማረች እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ እጃቸው ላይ በነበረው የአስቤዛ ገንዘብ ሽሮ ገዝተው በችርቻሮ መሸጥ በመጀመራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ ዓይነቱ እንቅስቃሴያቸው ከጥቂት ዓመታት በኋላ እየጐለበተ መጥቶ በመሐል ሐዋሳ ላይ “ሴንትራል” የሚል መጠሪያ ያለው አንድ መለስተኛ ሆቴል አቋቁመዋል፡፡ በዚህም ሳይገቱ ይህንኑ መለስተኛ ሆቴላቸውን ወደ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ለማሳደግ መብቃታቸውን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

Uganda to learn Ethiopia’s development experience

Uganda would like to draw lessons from Ethiopia’s experience in road infrastructure development, members of parliament from that country have said.
An experience sharing forum was held on Monday in Addis Ababa between the MPs and officials of Addis Ababa Roads Authority.
On the occasion, Authority General Manager, Engineer Fekade Haile briefed the MPs on the opportunities and challenges in the sector as well as the present state of the city’s road network.
The MPs commended the Authority for the remarkable achievements it made within a short period of time. 
Source:http://www.ertagov.com/

ዩጋንዳዊው ጋዜጠኛ ስለ ኢትዮጲዊያን ጸባይ የታዘበው በጣም ቁጥቦች ተጠራጠሪዎች


ዩጋንዳዊው ጋዜጠኛ ስለ ኢትዮጲዊያን ጸባይ የታዘበው በጣም ቁጥቦች ተጠራጠሪዎች ምክኒያታዊ የመሆን እና ስሜትን የመቆጣጠር ችግር ያለባቸው ስሜታዊ ቃላትን የሚጠቀሙ, ስድብ ያለበት አገላለጽ የሚያበዙ
ኢትዮጲያ ከሌላው አለም ተለይታ በእግዚያብሔር የተሰራች የሚመስላቸው ሀገራቸውን በጣም የሚወዱ፤ ለሃገራቸው ለመሰዋት የሚሽቀዳደሙ በውበትም፤በእውቀትም ከእነሱ የሚበልጥ ያለ የማይመስላቸው
.......
በምን ያህሉ ይስማማሉ?

ሙሉውን የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ያድምጡት