(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
ምግቦችን በማቀዝቅዣ ዉስጥ ማስቀመጥ ተገቢ የሆነ ምግብን የማቆያ መንገድ ነዉ። የሙቀት መጠን በቀነሰ ቁጥር የባክቴሪያ የመራባት አቅምም እንደዚሁ ይቀንሳል። ይህም ምግቦች በጤናማ ሁኔታ እንዲቀመጡም ይረዳል። ነገር ግን ሁሉም አይነት ምግቦች በማቀዝቀዣ ዉስጥ አይቀመጡም ከተቀመጡ ግን ጣዕማቸዉና ሳይበላሽ የመቆየት እድላቸው ይቀንሳል።
በማቀዝቀዣ ዉስጥ መቀመጥ የሌለባቸው ምግቦች
ድንች
ድንች በደረቅና ባልሞቀ ወይንም ባልቀዘቀዘ ቦታ በቤትዎ ውስጥ ያስቀምጡ። ማቀዝቀዣ ዉስጥ ማስቀምጥ ድንቹን ጣዕም ያሳጣዋል።
ሽንኩርት
ሽንኩርትን በቤት ውስጥ አየር በሚያስገባ መያዣ ውስጥ ማስቀመጥ ይገባል።
ነጭ ሽንኩርት
ልክ እንደ ሽንኩርት ነጭ ሽንኩርትም በተመሳሳይ ሁኔታ ያስቀምጡ።
ቲማቲም
በአብዛኛው ቲማቲምን በማቀዝቀዣ ዉስጥ እናስቀምጥ ይሆናል ነገር ግን ቲማቲሙን እንደነበረ አያቆይልንም ስለዚህም በላስቲክ ውስጥ ማስቀምጥ ይመከራል።
ማር
ማር ለአመታት ሳይበላሽ የመቆየት አቅም ያለው ሲሆን ማርንም እንዲሁ በንፁህ እቃ ውስጥ ባልሞቀ ወይንም ባልቀዘቀዘ ቦታ ማስቀመጥ ይመከራል።
ጤና ይስጥልኝ
No comments:
Post a Comment