Search

Wednesday, August 7, 2013

የ40/ 60 የጋራ መኖሮያ ቤት ምዝገባ ነሃሴ 6 ይጀመራል

የ40/ 60 የጋራ መኖሪያ ቤት ምዝገባ ነሃሴ 6 የሚጀመር ሲሆን ፥ ምዝገባው  እና የቁጠባ ደብተሩ  እንደ 10/90 እና 20/80  በባንክ ሳይሆን ፤ በአዲስ አበበባ ከተማ በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ገለጸ።
አገልግሎቱ በባንክ እንዳይሆን መደረጉ   የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን  ተሰልፈው ጊዜያቸውን እና  ጉልበታቸውን  የሚያባክኑ ተጠቃሚዎችን  ያግዛል ብሏል ባንኩ።
በዚህ በ 40/ 60 የቤት ፕሮግራም ተጠቃሚ  የቤቱን 40 በመቶ  መቆጠቡ በማረጋገጥ ፥  ቀሪውንና 60 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከባንክ በሚያገኘው ብድር አማካኝነት  የቤት ባለቤት ይሆናል ።
መቆጠቡ ብቻ ሳይሆን ቤት ፈላጊው  በመመሪያው መሰረት ሌሎች መስፈርፈቶችንም ማሟላት የሚጠበቅበት ሲሆን ፥ ከሁለት አመት በላይ በዚሁ በአዲስ  አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ፣ እድሜው ከ 18 አመት በላይ ሊሆን ይገባል የሚለው ደግሞ ቀዳሚው መስፈርት ነው።
ፕሮግራሙ የመንግስት ቋሚ ሰራተኞች ሆነው  በከተማው በሚገኙ በማናቸውም ተቋማት ፣ በፌደራል የመንግስት  መስሪያ ቤቶች እና ልማት ድርጅቶች እንዲሁም ፤ በኦሮሚያ ክልልየተለያዩ ቢሮዎች የሚሰሩ ሆነው በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩትንም ያጠቃልላል።
ከ 18 አመት በላይ ሆነው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ወይም የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያንም   ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚከለክላቸው አሰራር እንደሌለም ተመልክቷል።
 የአዲስ አበበባ ነዋሪ ሆነው ለሁለት ተከታታይ አመታት በስራ ምክንያትም ይሁን በህክምና እና በሌሎች ሁኔታዎች ከከተማዋ ውጭ የኖሩበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉትም መመዝገብ እንደሚችሉ ባንኩ ለንባብ ያበቃው በራሪ ጽሁፍ ይጠቁማል።
ከነሃሴ 6 እስከ 17,   2005 ለሚካሄደው ለዚህ ፕሮግራም ባንኩ ካለፈው ከ10/90 እና 20/80 ልምድ በመቀመር ፥ አዲስ አሰራር በመዘርጋቱ ፤ ለተሳታፊዎች ቀድሞ ቅጾች እንዲደርሱ ይደረጋል ፤ለዚህም ሲባል ከ8 መቶ ሺህ በላይ ቅጾች መዘጋጀታቸውን ነው የባንኩ የብድር ግምገማ ፖርትፎሊዮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ የኋላ ገሰሰ የገለጹት ።
በ40/ 60 የጋራ መኖሪያ ቤት ለመመዝገብም ለአንድ መኝታ 1 ሺህ 33 ብር የቁጠባ ደብተሩ ሲከፈት የሚከፈል ሲሆን ፥ ከዚያ በላይ እከፍላለለሁ የሚል ደንበኛም መክፈል ይችላል ተብሏል ፤ ባለሁለት መኝታ ቤት እንዲሁ 1 ሺህ 575 ብር ፣ ባለ ሶስት መኝታ ቤት 2 ሺህ 453 ብር ለመጀመሪያ ወር መቆጠብ ግድ ይላል።
ደንበኞች  በየወሩ ለተከታታየ 5 አመታት ለመቆጠብ የሚገደዱ  ሲሆን ፥  ቤቱን ከመረከባቸው በፊት ያሉት  ሁለት አመታት እንደ እፎይታ ጊዜ ተቆጥሮላቸው ፤  በቤቱ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የሁለት አመት ወለድ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ፤ በዚህ ፕሮግራም 6 መቶ ሺህ የሚጠጉቤት ፈላጊዎች ይሳተፉበታል ተብሎም ተገምቷል።
Source - FanaBC

No comments:

Post a Comment