ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡
ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ውስጥ በተደረገው ምርጫ
ብፁዕ አቡነ ማትያስ አራቱን ተመራጮች በከፍተኛ ልዩነት አሸንፈዋል፡፡
አቡነ ማትያስ ከአጠቃላዩ 806 ድምፅ 500 ሲያገኙ፣ በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዝቅተኛውን 39 ድምፅ እንዳገኙ በሥፍራው ተገኝተን ለመረዳት ችለናል፡፡
እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 98፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ፣ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ 70፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
98 ድምፅ ሲያገኙ፣ አንድ የድምፅ መስጫ ፎርም ምልክት ሳይደረግበት ተገኝቷል፡፡
የብፁዕ አቡነ ማትያስ በዓለ ሲመት የፊታችን እሑድ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈጸም ሲሆን፣ ሥነ ሥርዓቱም ከተለያዩ
አገሮች የሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ በዓለ ሲመቱ በኮፕቲክ ቴሌቪዥን በቀጥታ
ሥርጭት እንደሚተላለፍ ለማወቅ ተችሏል፡፡