Monday, May 4, 2015

አንገት ቆራጮቹ አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) የሚለብሱት “ጥቁር” ልብስ እንዲሁም “ብርቱካናማ” ልብስ አልብሶ የሚያርዳቸው ሰዎች የልብሶቹ ከለሮች ሚስጥር ምን እንደሆነ ያውቃሉ?


አንገት ቆራጮቹ አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) የሚለብሱት “ጥቁር” ልብስ እንዲሁም “ብርቱካናማ” ልብስ አልብሶ የሚያርዳቸው ሰዎች የልብሶቹ ከለሮች ሚስጥር ምን እንደሆነ ያውቃሉ?
ቢንያም መንገሻ " ማራናታ " !
በቅርቡ የአክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) አንገት ቆራጮች ብዙ ሰዎች የማይጠይቁት አንድ ጥያቄ አለ እርሱም ምንድ ነው? ለምንድ ነው የኢስላም ጂሀዲስት የሆነው አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) አንገታቸውን የሚቆርጣቸውን ሰዎች ብርቱካናማ ልብስ የሚያለብሳቸው? እንዲሁም አክራሪዎቹ የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) አንገት ቆራጮች ጥቁር ልብስ የሚለብሱት? የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ ያስፈልጋል:: በአብዛኛው በአለም ላይ ኦሬንጅ ከለር ያለው ልብስ በብዙ ሰዎች መካከል ይመረጣል:: በተጨማሪም ከሌሎች ከለሮችም ደምቆም ይታያል:: ስለሆነም በሁለቱ ከለሮች ማለትም በኦሬንጅ እና በጥቁር ቀለም ውስጥ የተደበቀ የሚስጥር ፍቺ አለ:: በመጀመሪያ የሚቀድመው ብርቱካናማው ቀለም ሲሆን የሚቀጥለው ደግሞ ጥቁር ቀለም ነው:: ይህ ቀለም እየኖርን ያለንበትን አለም ያመለክታል:: ይህ ማለት ምንድ ነው አለማችን በመጀመሪያ ለመብላት እንደ ሚያስጎመዥ እንደ በሰለ ብርቱካን ስትመስል ፍጻሜዋ ግን ጥቁር ድቅድቅ ጨለማ ነው:: ለዚህ ነው አንገት ቆራጮቹ አክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ሚኒሻዎች የሚለብሱት ጥቁር ልብስ የሚወክለው የመጨረሻውን የዚህን አለም የሰይጣን መንግስትን ሲሆን ብርቱካናማ ልብስ አልብሰው የሚያርዷቸው ሰዎች ደግሞ የሚወክሉት ደግሞ ለሰይጣን የሚቀርብ የደም መስዋእት ግብር ነው:
“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፤ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል። ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥ በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው። በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፤ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል። በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።” ሰፎ 1 : 14-18
ብርቱካናማውን ቀለም ያለበትን ልብስ የሚያዘወትሩ የአለማችን አያሌ ታዋቂ የቲቪ እና የሚዲያ አክተሮችን ብንጠቅስ ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ ኬቲ ፔሪ ፣ ሪሃና እና ቢዮንሴ ላውረንስ እንዲሁም አለም አቀፍ ፓለቲከኞች መካከል ሂላሪ ክሊንተን እና ሚችል ኦባማ በተጨማሪም ከታዋቂ ቴሌቨዥን ፕሮግራም Orenge Black በተጨማሪም የተራውና የብሄራዊው የፓለቲካ እስር ቤት የታራሚዎች እና የወንጀለኞች ደንብ ልብስ እንዲሁም አለም አቀፉ እስር ቤት “ጓንታናማው” የታራሚዎች የደንብ ልብስ በመጨረሻውም የታሪከኛው አንገት ቆራጩ የአክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) የታራጆቹ ልብሶች የብርቱካናማው ቀለም ሚስጥራዊ ልብሶች ናቸው::
በኦሬንጅ እና በጥቁር ቀለም ውስጥ በሰይጣን የተገለጡት ሚስጥሮች በማቀናጀት የሰዎችን አይምሮ ማግዛት እና ማስጨነቅ ዋናው አላማ ነው::
የብርቱካናማው ቀለም የሚስጥር ቁልፍ ሲገለጥ
ORANGE የሚለው ቃል ፊደሎች በቁጥር ሲለወጡ የሚሰጡት የቁጥር ድምር ውጤት
O-15 Orange 666 code ፊደሎቹን ወደቁጥር ይለውጣቸዋል። R-18=33 o-15 R-18=33=6
A-1 A-1 N-14=15=6 N-14=15
G-7 G-7 E-5=12 E-5=12=3
+=15=6 total666
33+1=34=አይምሮን መቆጣጠር
የጥቁር ቀለም የሚስጥር ቁልፍ ሲገለጥ
Black የሚለው ቃል ፊደሎች በቁጥር ሲለወጡ የሚሰጡት የቁጥር ድምር ውጤት
B-2 L-12=14 A-1= c-3 k-11=14=29=11=119/911
የብሩትካናማው ቀለም ያለበትን ልብስ የሚለብሱ ታዋቂ ያለማችን ሰዎች የመንግስት ተቋማቶች እንዲሁም ለተለያዩ ክብረ በአል ላይ የሚለበሱ እና ለክብረ በአሉ ስነስርአት የሚውሉ ብርቱካናማውን ቀለም የያዙ ማናቸውም ቁሳቁሶች የልጆች መጫወቻዎችን ጨምሮ በተጨማሪም የአክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ጨምሮ ብርቱካናማውን ቀለም ለብሰውና አስለብሰው ሲታዩ እና ሲያሳዩ ከክፋት አምላክ እና አባት ከሆነው ከዲያብሎስ መንግስት ጋር ህብረት ማድረጋቸውን ያመለክታሉ::
ብርቱካናማውን ቀለም በአሁን ግዜ በመጨረሻው ዘመን በይፋ የተፈጠረውን አዲሱ የአለም መንግስት ስርአትን ( NEW WORLD ORDER ) ወይንም የኢልሚናቲ 666 መንግስት የሚስጥር ቀለም ነው:: አንድ ብርቱካናማውን ቀለም ያለበት ልብስ ላይ የሰው ደም ከነካው ለሰይጣን መስዋእት ተደርጎ በትክክል ተፈጽሞዋል ተብሎ ይታመናል:: እንዲሁም ጓንታናማው አሰቃቂ እስር ቤትን ጨምሮ አብዛኛው በአለም ላይ ያሉ እስር ቤቶች ብርቱካናማውን ቀለም ልብስ ታሳሪዎቹ ካስለበሱዋቸው ቡኋላ አሰቃቂ ቅጣት በሁሉም ላይ ያደርሱባቸዋል በተጨማሪም ብዙዎቹ እስር ቤት ወስጥ Guillotine በተባለ መሳሪያ አንገታቸው እዛው እስር ቤት ውስጥ ተቀልቶዋል:: ወደ ፊትም ይቀላል::
ዛሬ በአለማችን ላይ የብሩትካናማው ቀለም አብዮት ያስጀመሩት ምእራባውያን በዬክሬን ውስጥ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር 2004 ላይ “ብርቱካናማው አብዮት” በሚል መጠሪያ የመጀመሪያው ህዝባዊ አመጽ በዩክሬን አስጀመሩት ከዛ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ዩክሬን በብሩትካናማው እሳት እየነደደች ትገኛለች:: የአክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) ከጊዜ ወደ ግዜ የሚያርዳቸውን ሰዎች በብሩትካናማው ልብስ አስለብሶ አንገታቸውን በካራ ይበጥሳቸዋል:: ስለዚህ ብሩትካናማው ቀለም የሚወክለው ሰይጣንን 666 ሲሆን ጥቁሩ ቀለም ያለው ልብስ የሚወክለው የዚህ አለም ገዥዎች የሚጠቀሙበት ድንገተኛ የስልክ አደጋ ጥሪ ቁጥር የሆነውን 119/911 ያመለክታል:: በተጨማሪም የአክራሪው የኢስላም ጂሀዲስት አይ ኤስ አይ ኤስ (ISIS) የፈጠሩት እና በተለያዩ ቁሳቁስ የሚረዱት ታላላቆች የምእራባውያኖቹ መንግስታት ለሁሉም ነገር መፈጠር ዋናዎቹ ባለድርሻ አካላት ናቸው:: ለዚህም ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለመጨረሻው ዘመን ስለምትገለጠው እና በሰዎች ደም ሰክራ የምትታየው “ታላቂቱ ጋለሞታ” የምድር እርኩሰት ይህ የመጨረሻው ዘመን ታላላቆቹን የምድር ነገስታትና እና መንግስትን የብሩትካናማው ቀለም ድብቅ ሰይጣናዊ ሴራቸውን ያመለክታል::
“ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ። በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤ በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም። ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ። ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ። መልአኩም አለኝ። የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ። ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ። ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥ ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ። እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።” ራዕ 17: 1:13

No comments:

Post a Comment